Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ የመኖሪያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለስድስት ወራት | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

በመዲናዋ የመኖሪያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለስድስት ወራት ተራዘመ

የከተማ አስተዳደሩ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በመኖሪያ ቤት ተከራዮች ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራይን ማስለቀቅን የሚከለክል ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረጉን አስታውሷል፡፡

ደንቡ በተለያየ ጊዜ እየተራዘመ ላለፈው አንድ አመት ተግባራዊ ተደርጎ ቆይቷልም ነው ያለው።

የከተማ አስተዳደሩ በመግለጫው "አሁን ያለውን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ እና የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ከግምት ባስገባ ወቅቱን በአብሮነትና በመተሳሰብ ለማለፍ ይረዳ ዘንድ ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም ተወስኗል ብሏል።

በመሆኑም ይህንን ክለከላ በመተላለፍ ተከራዮችን የሚያስወጡ እና የኪራይ ዋጋን የሚጨምሩ አካላት ላይ ማህበረሰቡ እንዲጠቁም መጠየቁን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@gasha_tube