Get Mystery Box with random crypto!

አታውቅም ! ሳልፈልግ የመራቅ ወኔዬን እርቀት ፤ ይሉኝታ ቢስ ፊቴን ፤ ካልፈለኩ አካሌ እንዴት እ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

አታውቅም !

ሳልፈልግ የመራቅ ወኔዬን እርቀት ፤ ይሉኝታ ቢስ ፊቴን ፤ ካልፈለኩ አካሌ እንዴት እንደሚያምፅ፣ የሚጣፍጥ እንዴት እንደሚመረኝ፣ ሰከንድ አልሄድም እንደሚለኝ፤

አታቅም ! አታቀኝም !

ፍቅርህ ነው ያለሰለሰኝ ። ሲከፋኝ የማላንባረቀው፣
አሁን ወሰኜ መልሼ የምከልሰው፣ አቋም አልባ ያደረገኝ፣ በግዜ ብዛት የገዛኝ ለኔ ያሳየኸኝ ስሜትህ ነው ።

ደመነብሴ እንደሚታዘዝህ ፤ መነጫነጬ ከፍቅር እንደመነጨ ፤ የማላነሳውን ስልክህን እንደምጠብቀው ፤

ሳማክ እንኳ እንዳይጠሉብኝ ብዬ አንዳንዱን እውነት ቆርጬ እንደማስቀርው ።

አስሬ እንደ ልጅ ስትመክረኝ ፤ ሳጠፋ እንባዬ አይኔ ላይ አቆጥቁጦ የምሰማህ፤ ንዴትህ ውስጥ ፍቅር ስለሚታየኝ ነው ።

አንተ ጋ ሌላ ነኝ፤ አንተ ጋ በምሆነው እንዳትመዝነኝ !!
@gasha_tube
@gasha_tube