Get Mystery Box with random crypto!

ተራ ተራራነት ስሜት አለ ውስጤ ትልቅ፣ .የሚያፍን የሚያስጨንቅ፣ ..ህመም አለ የማያመኝ፣ በመብሰ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

ተራ ተራራነት

ስሜት አለ ውስጤ ትልቅ፣
.የሚያፍን የሚያስጨንቅ፣
..ህመም አለ የማያመኝ፣
በመብሰልሰል የሚገድለኝ፣
..የመገለ መጥፎ ቁስል፣
ሲታይ ደህና የሚመስል።
        
 ይሰማኛል ግራ ስሜት፣
የማቅለሽለሽ መውደቅ አይነት፣
.................ደሞ የመሞት!

ምወድቅ ምወድቅ ምወድቅ ይመስለኛል፣
ሰው አያውቅልኝም እኔን ግን ያመኛል፣
አለማወቃቸው ብሶ ይገድለኛል፣
ፍርሃት ፍርሃት ፍ_ር_ሃ_ት ይሰማኛል፣
ደርሶ ልቤን......... ያፍነኛል፣
የፊት ደመና የት ይዘንብልኛል፣
የውስጤ ገሞራስ ወዴት ይፈነዳል?
እዚያው ተደባልቆ ውስጤኑ ይፋጃል።

በውስጤ ገሞራ ላልበስል እያረርኩ፣
የፊቴን መዳመ'ን ትልቅ ጠባሳዬን፣
...............ለመሸሸግ በጣርኩ ፣
ካለኝ ተራራነት ወደ ጠጠር ፈረስኩ።

                      Hami
@gasha_tube
@gasha_tube