Get Mystery Box with random crypto!

ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gasha_tube — ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gasha_tube — ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ
የሰርጥ አድራሻ: @gasha_tube
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.79K
የሰርጥ መግለጫ

News & Entertainment Channel
⭕️በቅርቡ በethio sat የቴሌቪዥን ስርጭታችንን ልንጀምር ዝግጁነታችንን ጨርሰናል⭐️
#በዚ_ቻናል_ያዘጋጀንላቹ_ፕሮግራሞች ።
➠ ዜናዎች ➠ መዝናኛዎች
➠ አስገራሚ ታሪኮች ➠ ስለ ጤናዎ አዳዲስ መረጃዎች
➠ የቢዝነስ አሳቦች ➠ አነቃቂ ምክሮች
➠የቴክኖሎጂ ዜናዎች
➠ ኢትዮጵያዊ የሆኑ እሴቶች በየቀኑ ለእናንተ
እናቀርባለን

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-12-03 11:23:21
በጣም አስተማሪ ታሪክ
__
አንድ በጣም ሌባ እና ብዙ ሴቶችን ደፍሮ የታሰረ ወጣት ነበረ ። ከእስር እንደተፈታ ወደ አያቶቹ ቤት ለጥየቃ እየተጓዘ እያለ ይመሽበትና ሰው ቤት ለማደር ፈልጎ የኣንድን ሰው ቤት ያንኳኳል

ሰውየው ሲከፍት ልጁ እባካቹ ተጓዥ መንገደኛ ነኝ እንድታሳድሩኝ ስል በፈጣሪ ስም እለምናልው ሲል ጠየቀ ሰውየው በለሰለሰ ድምፅ ይቅርታ አምኜ ላሳድርህ አልችልም ሴት ልጅ አለችኝ ይለውና በሩን ይዘጋል ።

ሁለተኛውም ቤት ሄዶ ጠየቀው ተመሳሳይ መልስ ሰጠው እና በሩን ዘጋ። ሶስተኛው ቤት አንኳኩቶ ሲጠይቅ ግባ ብለው አስገብተው እራት አበሉት ልጁ ማሰብ ጀመረ ወንድ ልጅ ቢኖራቸው ነው ብሎ አሰበ ግን ወደ ማደሪያው ሲሄድ ቆንጂዬ ሴት ልጅ ተኝታለች። ሰውየው ያረገውን ኮፍያ አውልቆ መሃላቸው ላይ አስቀምጦ ማንም ወደ ማንም እንዳይጠጋ አለና ልጁን አምንሀለው ብሎ ኩራዙን አጥፍቶላቸው ይተኛሉ። ልጁ በመደነቅ ምንም ሳያቀኝ አንዴት አመነኝ ብሎ እንቅልፍ ሳይወስደው አደረ በጠዋት ሊሄድ ሲወጣ ምግብ ቋጥረው ሰጡት።

ልጁ ከግቢው እንደወጣ ልጂትዋ በረንዳ ላይ ሆና ስታየው ተመለከተ ። ገብቶ ሰላም እንዳይላት በሩ ተዘግቷል አጥሩ ላይ ሆኖ ቆይ መጥቼ ሰላም ልበልሽ ሲል
ልጂቱ ያባቴን ኮፍያ ያልዘለልክ ልጅ አሁን አጥር ልትዘል ነው ብላ አሾፈችበትና ሄዳ በሩን ከፈተችለት።

ልጁም ፀጉርዋን እየዳበሰ እምነት ትልቅ እስር ቤት ነው እምነትን ስትቀበይ መንቀሳቀስ አትችይም እኔ ብዙ ጊዜ ታስሬ አቃለው ግን ምንም አይመስለኝም የእምነት እስር ቤት ግን ከምንም በላይ ትልቅ ነው አላት ይባላል።

እና አምነሀት ወይም አምነሺው ከጎዳሽ አትበሳጪ(ጭ) የጎዳህ ሰው እድሜ ልክ ፀፀት ይሆንበታል።

@gasha_tube
400 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 21:38:41
**ዛሬ ምን አነበቡ?**
*********
"ቱትሲ የሆናችሁ ሁሉ ከመቀመጫቹህ አንዴ ብድግ በሉ" መምህር ቡሆሮ ጮክ ብሎ ተናገረ፡፡ በእጁ ላይ የክፍል ተማሪዎች ስም ዝርዝር ይዟል፡፡ በትኩረት እያጠናው ነው፡፡ ድንገት የኔስምን ሲያይ ወደኔ ማፍጠጥ ጀመረ፡፡

"ኢማኩኤሌ ኢሊባጊዛ..ለምንድን ነው የማትነሺው? ሁቱዎች ተነሱ ስል አልተነሳሽም፡፡ ትዋም ስል ቁጭ ብለሻል አሁን ቱትሲዎችም ብድግ በሉ ስል ንቅንቅ አላልሽም..ለምንድን ነው?" አለኝ ፈገግታ ፊቱ ላይ ቢታይም በድምፁ ግን ማስፈራራት ይነበባል፡፡
"አላውቅም መምህር" መለስኩለት
"እንዴ..ምኑን ነው የማታውቂው..ጎሳሽ ምንድን ነው እኮ ነው ያልኩሽ?"
"እኮ.እኔ እንጃ አላወቅም?"
"ሁቱ ነሽ ወይስ ቱትሲ?"
"እ..አላ..አ..ላውቅም መምህር"
"ውጪ....ጎሳሽን ካላወቅሽ ሁለተኛ እዚች ክፍል እንዳትረግጪ" በጩኸት አባረረኝ፡፡
ደብተሮቼን ሰብስቤ በሀፍረት ከክፍሌ ወጣው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሬ ሩዋንዳ ያለው የጎሳ ክፍፍል ጉዳይ በመጥፎ ሁኔታ አነቃኝ፡፡
*****
Left to Tell
ታሪካዊው የሩዋንዳ ጭፍጨፋ ላይ ተመስርቶ የተፃፈ እውነተኛ ታሪክ፡፡
ከጎሰኝነት የተነሳ ስር የሰደደ ጥላቻ፣ ቂም እና በቀል፣ እምነትና ይቅርባይነት መልኮችን ኩልል አድርጎ የሚያሳይ.
ከአሰቃቂ የዘር ፍጅት ለወሬ ነጋሪ የቀረች አንዲት ወጣት አስገራሚ ህይወት የሚተርክ፡፡

"Left to tell"(ሁቱትሲ ተብሎም በአማርኛ ተተርጉሟል) .ቀላል የሚመስሉ ማህበራዊ ሁኔታዎች በግዜ ካልታከሙ ምን ያህል እልቂት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ በግልፅ የሚያስተምር ነው፡፡
መፅሀፉ በ100 ቀናት ውስጥ ከ 800,000 በላይ ቱትሲ ሩዋንዳውያን አሳዛኝ እልቂት ይተርካል፡፡ እኛም በጊዜ ባይባልም ብዙ ሳይረፍድ የምንማርበት ነውና.
አንብቡት!
@gasha_tube
539 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 10:11:43
#ስለምታስበው_አስብ


ለመሆኑ በቀን ከ12 ሺ እስከ 60 ሺ ሀሳቦች በአእምሯችን እንደሚመላለሱና ከ80 እስከ 95 ፐርሰንት የሚሆኑት ሀሳቦች አሉታዊና የተደጋገሙ እንደሆኑ ያውቃሉ?

#ስለምታስበው_አስብ የተሰኙት መጽሐፍ አላስፈላጊ ሀሳቦቻችንን ተቆጣጥረን እንዴት ጥርት ባለ ሁኔታ ማሰብ እንዳለብን የሚያሳዩ፣ አሉታዊና ትርኪምርኪ የሆኑ ሀሳቦቻችንን ለማጽዳት የሚረዱና ለደስተኛ ሕይወት እጅግ አስፈላጊ መጽሐፍት ናቸው!

#ለነዚህ_ድንቅ_መጽሐፍት_ከተሰጡ_አስተያየቶች፡-

“አዕምሯችን እንዴት እንደሚሰራ እንደ ርችት ፍንትው ባለ ህብረቀለም የሚያሳዩ መጽሐፍት ናቸው፡፡ ትንሽም ቢሆን የአስተሳሰብ እክል አለብኝ ብለው ካሰቡ እነዚህ አስገራሚ መጽሐፍት #እንደ_መድሃኒት_ቢታዘዙልዎት_አይከፋም፡፡”
#ፕሮፌሰር_አይሪስ_ቦኔት
ሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ

“… ይህ አስደማሚ መጽሃፍ እንዴት ደስተኛ እንደምንሆን ብቻ ሳይሆን ራሳችን በራሳችን ደስታችንን የምናበላሽበትን መንገድ እንዴት መዝጋት እንደምንችል ያሳዩናል፡፡ #ቡክሊስት_የመጽሃፍ_ዳሰሳ

“እንደውሃ የሚፈስ አጻጻፍ ነው… ጸሐፊው በግልና በድርጅት ደረጃ ከፍተኛ ዋጋ በሚያስከፍል ሁኔታ አስተሳሰባችንና የውሳኔ አሰጣጥ ፈሊጦቻችንን የሚወስኑ ጉዳዮችን እርቃናቸውን አስቀርቷቸዋል፡፡”
#ፋይናንሺያል_ታይምስ

#የምናስብ_ከሆነ እነዚህ መጽሐፍት የግድ ያስፈልጉናል!!!

@gasha_tube
200 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-26 17:39:58 የማይጠየቁ 15 ጥያቄዎች part 1


1. እርቦኝ; ጠምቶኝ; ደክሞኝ ልክ ቤት ስገባ "መጣህ እንዴ ?" አትበሉኝ:: እንግዲህ እኔ እስከማውቀው ድረስ ስለመጣሁ ነው የታየኋችሁ ! ይልቅ የሚበላ የሚጠጣውን አቅርባችሁ ፈውሱኝ::
.
2.". ሰዓት ስንት ነው?" ስልህ "አሁን?" አትበለኝ::.ታዲያ መቼ
ሊሆን ይችላል?
ወይስ አቆጣጠሩን ስለማታውቅበት ጊዜ ለመፍጀት ነው!
.
3. 'Password'ህን ንገረኝ? አይባልም::
ከነገርኩህማ ምኑን password ሆነው ታዲያ?

.
4. ምን ልጋብዝህ? አይባልም::
ግብዣ በጋባዥ እንጂ በተጋባዥ ውሳኔ አይካሄድም! ሼም
ይዞኝ የወረደ ነገር እንዳዝ ፈልገህ ካልሆነ በስተቀር!
.
5. ለቅሶ ቤት ሄደህ የአሟሟቱን detail አትጠይቅ!
ማስተዛዘን እኮ ሀዘን ማረሳሳት እንጂ ማባባስ አይደለም::

6· ጀለስሽ በታክሲ እየመጣ "የት ደርሰሀል" ብላቹት እየመጣው ነው አንድ 30 ደቂቃ… …… ሲል አናንተ "ቶሎ በል… ኧረ አፍጥነው " አይባልም ።ታከሲውን አይነዳው!! ወይስ ውስጥ እያለ ይሩጥ… ካላቹም ለታክሲው ሹፌር ነው ።
.
7. "አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?" ብለህ አትጠይቅ! 'አንድ' ካልክ
እኮ በቃ "አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?" ስትል ጥያቄህን
ጨረስክ::

part 2... ይቀጥላል

 @gasha_tube
#ሼር ምርጦቼ
259 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 15:23:38
#የፀጉሮ_መነቃቀል_መጥፋት_አሳስቦዎታል?       0928025669

#DISAAR ANTI #HAIR LOSS OIL

        ፀጉር በብዙ ምክንያቶች ሊነቃቀል ሊጠፋ ይችላል እነሱም :-

በፀጉር አስተካካዮች ፣ በቀለም ምርቶች ፣ በፔርሞች ፣ወቅታዊ የፀጉር መርገፍ ፣ ሚዛናዊ ያልሆነ ሕይወት ፣ ማጨስ ፣ በጣም ቅመም ያላቸውን ምግቦች መመገብ ፣ የሥራ ጫና ፣ የትርፍ ሰዓት ሥራ ፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና በሌሎች ምክንያቶች ሊረግፍ እና ሊጠፋ ይችላል ።

ከእንግዲህ ለፀጉር መጥፋት አይጨነቁ Disaar ant hair loss oil ከእነኚህ የፀጉር መጥፋት ችግሮች ሊገላግሎት ለወንዶች እና ለሴቶች እንዲሆን ተደረጎ ቀረበልዎት።

ከስሩ የፀጉር መርገፍን ይከላከላል

አዲስ ጤናማ ፀጉር ማደግ ይችል ዘንድ ኤስዲኤፍ የተጠናከረ ይዘት ወደ ቆዳው ውስጥ ዘልቆ follicle ን ይጠግናል ፡፡ ለስላሳ እና ጤናማ ፀጉርን ይሰጥዎታል።

ይህንን የዳይሳር ፀጉር እንክብካቤ ዘይት እንዴት ይጠቀሙታል፦
1, በየቀኑ ከታጠብ በኋላ ትክክለኛውን መጠን በእኩልነት ይጠቀሙ እና ቆዳዎት እስኪመጠው ድረስ ሙሉ በሙሉ በደምብ ይሹት ፡፡
ዋጋ = 3000ብር
price = 3000birr

Phone:0928025668
0928025668
0928025668
@SinaMarket_Manager
@SinaMarket_Manager
102 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 10:29:46
#ጀርባ

ከቤትሽ ግድግዳ ከሳሎንሽ መሀል
መስታወት ተሰቅሏል ፥
ስትስቂ ሳቅሽን፣ስታነቢ እንባሽን
ገልብጦ ያሳይሻል ፥
እንዲህ ነው መስታወት የብርጭቆ ግብሩ ፥
ሲከፋሽ የከፋው ፣ስትሰክሪ ሰካራም
የዛሬ አንቺነትሽ ነፀብራቅ ማኖሩ ።

ስለዚህ የኔ ውድ .....!!
ከተሰባሪ እቃ ብርጭቆ ፊት ቆመሽ
<እኔ ማን ነኝ !?> እያልሽ እንዳት ጠይቂ..
መጀመሪያ ውዴ....
የዛሬ አንቺነትሽን ፣ ከነገው ምኞትሽ ፣
........ ከትላንት አስታርቂ ፤


በትዝታ ማዕበል የኋሊት ሂጂና
ከህይወት ፊት ቆመሽ ጀርባሽን እወቂ ።
........//......
ዳኙ

https://t.me/gasha_tube
339 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 15:49:27
Website ጥቆማ
classcentral የሚባል በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎች የግድ ማወቅ ያለባቸው Website ኘው

በዚህ Website ውስጥ
100ሺ በላይ Course በውስጡ እንዲሁም Harvard University ጨምሮ ከ 1000 በላይ University ያለበት ሲሆን  Website ውስጥ ከገባችሁ በኋላ Search ማረጊያው ላይ የፈለጋችሁትን ከፃፋችሁ በኋላ በPdf በ video እና በተለያዩ አቀራረቦች ያመጣላችኋል

ሌላው Website ውስጥ ከገባችሁ በኋላ Free Certificate, የሚለውን ስትነኩት ከተለዩ ዩዩንቨርስቲ የተወጣጡ ትምህሮቶቾን ከወሰዳችሁ በኋላ በነፃ ሰርተፍኬት ማግኘት ትችላላችሁ

በጣም ብዙ አማራ
ጮች በውስጡ ስለያዘ አሁኑኑ ጎብኙት
223 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 19:11:01
ሊዎ ቴልስቶይ በማስታወሻ ደብተሩ ላይ ይህንን ቁምነገር ጽፏል። ላካፍላችሁ፦

በልጅነቴ ከእናቴ ጋር ዘወትር ትያትር ቤት እንሄድ ነበር። ቤተሰቦቼ ቢጠሯቸው የማይሰሙ ሃብታም ነበሩ። ሞስኮ ውስጥ በክረምት በረዶ ያለማቋረጥ ይወርዳል። ያኔ እናትና ልጅ ትያትር ቤት ውስጥ ነን።

ትያትር ቤቱ የትራጄዲ ተውኔት የሚያሳይ ከሆነ እናቴ ታለቅሳለች። እንባ በአይኖቿ ግጥም ብሎ በጉንጮቿ ያለማቋረጥ ይወርዳል። እኔ በልቤ 'እናቴ ምን አይነት ሩህሩህ ሴት ናት!' ብዬ አስባለሁ።

ተውኔቱ አልቆ ከትያትር ቤት ስንወጣ ሹፌራችንን መኪናው ውስጥ በቅዝቃዜ ተኮራምቶ እናገኘዋለን። እንግዲህ ሹፌራችን መኪናውን ጥሎ መሄድ አይችልም። መቼ ከትያትር ቤቱ እንደምንወጣ አይታወቅም። ሁሌም ዝግጁ እና ንቁ ሆኖ መጠበቅ አለበት። እንደዚያ ተጨብጦ፣ ተኮራምቶ እናቴ ዘወር ብላ እንኳን አታየውም። አንዳንዴ ሹፌራችን በቅዝቃዜ ሞቶ በሌላ ሹፌር የሚተካበት ግዜ ነበር። እናቴ አንድ ዘለላ እንባ እንኳን አታፈስም። በመጨረሻ የእናቴ እንባ የማስመሰልና የሃሰት መሆኑን ተረዳሁ።
441 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-21 19:47:32
ማህበራዊ ገፆችን በመጠቀም በትንሽ ወጪ ብዙ ደንበኞች ጋር ይድረሱ፣ምርቶትን ያስተዋዉቁ፣ሽያጮን ይጨምሩ።


𝗥𝗲𝗮𝗰𝗵 𝗺𝗼𝗿𝗲 𝗰𝘂𝘀𝘁𝗼𝗺𝗲𝗿𝘀 𝗮𝘁 𝗮 𝗹𝗼𝘄 𝗯𝘂𝗱𝗴𝗲𝘁 𝘂𝘀𝗶𝗻𝗴 𝘀𝗼𝗰𝗶𝗮𝗹 𝗺𝗲𝗱𝗶𝗮.


ለድርጅትዎ፣ ለቢዝነስዎ፣ ለቻናልዎ እንዲሁም ለማንኛውም አይነት ምርት እና አገልግሎት አድቨርታይዚንግ ወይንም የማስተዋወቅ ስራ እንሰራለን።

ምርት ወይም አገልግሎትዎ ከብዙሀን ዘንድ እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ቻናልዎ እንዲያድግ ከፈለጉ፣ በብዙሀን ዘንድ በማንኛዉም ነገር እውቅና ከፈለጉ ትክክለኛዉ አማራጭዎ እኛ ነን።


የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

𝗙𝗮𝗰𝗲𝗯𝗼𝗼𝗸 𝗯𝗼𝗼𝘀𝘁
𝗧𝗲𝗹𝗲𝗴𝗿𝗮𝗺 𝗮𝗱𝘃𝗲𝗿𝘁𝗶𝘀𝗶𝗻𝗴

𝑩𝒓𝒂𝒏𝒅𝒆𝒅 𝒔𝒕𝒓𝒂𝒕𝒆𝒈𝒚
𝑫𝒊𝒈𝒊𝒕𝒂𝒍 𝑴𝒂𝒓𝒌𝒆𝒕𝒊𝒏𝒈 𝑺𝒕𝒓𝒂𝒕𝒆𝒈𝒚
𝒔𝒐𝒄𝒊𝒂𝒍 𝒎𝒆𝒅𝒊𝒂 𝒎𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕

𝗪𝗲𝗯𝘀𝗶𝘁𝗲 𝗗𝗲𝘀𝗶𝗴𝗻
𝗚𝗿𝗮𝗽𝗵𝗶𝗰 𝗗𝗲𝘀𝗶𝗴𝗻
𝗟𝗼𝗴𝗼 𝗗𝗲𝘀𝗶𝗴𝗻
𝗧𝗲𝗹𝗲𝗴𝗿𝗮𝗺 𝗕𝗼𝘁 𝗱𝗲𝘃𝗲𝗹𝗼𝗽𝗺𝗲𝗻𝘁
𝗽𝗼𝘀𝘁𝗲𝗿


𝘍𝘖𝘓𝘓𝘖𝘞 𝑼𝑺 𝑶𝑵 𝑺𝑶𝑪𝑰𝑨𝑳 𝑴𝑬𝑫𝑰𝑨 -----
𝗧𝗲𝗹𝗲𝗴𝗿𝗮𝗺 Channel:https://t.me/Sina_market_channel
𝗙𝗮𝗰𝗲𝗯𝗼𝗼𝗸: https://www.facebook.com/Snia.Market.Facebook
𝗜𝗻𝘀𝘁𝗮𝗴𝗿𝗮𝗺: https://www.instagram.com/Sina_Market_ethiopia



ያናግሩን

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
          𝐂𝐀𝐋𝐋 𝐓𝐄𝐗𝐓     
     𝗣𝗵𝗼𝗻𝗲 ☞ 0928025669
𝗧𝗲𝗹𝗲𝗴𝗿𝗮𝗺 ☞@SinaMarket_Manager
928 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-19 20:56:32 #10_ምርጥ_አባባሎች_ከ_ዘ_አልኬሚስት_መጽሐፍ_ጸሐፊ

#1_ፍርሃት_እንቅፋት_ነው።

ፍርሃት ከሚያጋጥምህ ማንኛውም እንቅፋት የበለጠ ትልቅ እንቅፋት ነው።

~ ፍርሃትህን አትፍራው ብትፈራውም ከማድረግ አታፈግፍግ!

#2_እውነት_ሁልጊዜ_ጸንቶ_ይኖራል

~ እውነትን በጭስ እና በመስታወት መሸፈን አይቻልም - ሁልጊዜ ጸንቶ ይቆማል።

#3_አሰልቺውን_ተመሳሳይ_ህይወት_ስበረው

እያንዳንዱ ቀን ከቀጣዩ ቀን ጋር ተመሳሳይ በሚሆንበት ጊዜ ሰዎች በየቀኑ በሕይወታቸው ውስጥ የሚከናወኑትን መልካም ነገሮች ለይተው ማወቅ ስለሚያቅታቸው ነው።

~ ምስጋና በእያንዳንዱ ቀን ውስጥ ጥሩውን የማግኘት ልምምድ ነው።

#4_አሁንን_ተቀበል

ሁልጊዜ አሁን ባለህ ነገር ላይ ማተኮር ከቻልክ ደስተኛ ሰው ትሆናለህ።

~ ባለፈው መኖር እና ያለፈው ህይወትህ አንተን እንዲገልፅ መፍቀድ ወይም ስለወደፊቱ መጨነቅ ምንም ፋይዳ የለውም። 

#5_ስኬትህ_የምታደርገው_ነገር_ነፀብራቅ_ነው።

ከቀደመው ማንነታችን የተሻልን ለመሆን ጥረት ባደረግን ቁጥር በዙሪያችን ያሉ ነገሮች ሁሉ የተሻሉ መሆን ይጀምራሉ።

~ የተሻለ ሰው መሆንህ በዙሪያህ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ማለትም የአኗኗር ዘይቤህን፣ ቤተሰብህን፣ ጓደኞችህን፣ ማህበረሰብህን የሚጠቅም ተዘዋዋሪ ተጽእኖ ይፈጥራል።

#6_ወስን

አንድ ሰው ሲወስን፣ መጀመሪያ ውሳኔውን ሲወስን አያውቃቸው ወደነበሩ ቦታዎች የሚወስደው ኃይለኛ ፍሰት ውስጥ እየገባ ነው።

~ ድርጊት በውሳኔህ ላይ ከመተማመን የሚመነጭ ነው።  አጥር ላይ መቀመጥ የትም አያደርስም። ስለዚህ ወስን! የውሳኔ ሰው ሁን!

#7_የምናብ_ሰው_ሁን

" አለምን የማየው እንዲከሰት ከምፈልገው ነገር አንፃር እንጂ ከሚታየው ነገር አንፃር አይደለም።"

~ ሰዎች ዓለምን እንዳለች መቀበልን ቢመርጡ ኖሮ ታላላቅ ፈጠራዎች አይከሰቱም ነበር።

~ ታላላቅ ስኬቶች እና ፈጠራዎች ‘አይቻልም’ የሚል አስተሳሰብን ችላ በማለት ይጀምራሉ።

#8_እንደገና_መነሳትህን_ቀጥል

" የሕይወት ምስጢር ሰባት ጊዜ ወድቆ ስምንት ጊዜ መነሳት ነው።"
ምክንያቱም ስምንተኛው ጊዜ የአንተ ግኝት ሊሆን ይችላል።

#9_በራስህ_መንገድ_ላይ_አተኩር

ሌሎች ሰዎች ተጽእኖ ሊያሳድሩብህ ይችላሉ፤  ነገር ግን የሌላ ሰው ህይወት መኖር ከጀመርክ ግራ የተጋባ ሰው ትሆናለህ።

~ ምክር መቀበል እና ከሌሎች መማር ምንም ችግር የለውም፤ ነገር ግን የምትሄድበት መንገድ ከአንተ ፍላጎት እና ዝንባሌ ጋር የሚስማማ መሆኑን አረጋግጥ።

#10_ሁልጊዜ_እርምጃ_ውሰድ

" ለመማር አንድ መንገድ ብቻ ነው ያለው፤  ይህም ተግባር ብቻ ነው""

ከስኬት አካደሚ ገፅ የተገኘ

#ዘ_አልኬሚስት መጽሐፍ
@gasha_tube

t.me/gasha_tube
1.7K views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, edited  17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ