Get Mystery Box with random crypto!

ሊዎ ቴልስቶይ በማስታወሻ ደብተሩ ላይ ይህንን ቁምነገር ጽፏል። ላካፍላችሁ፦ በልጅነቴ ከእናቴ ጋር | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

ሊዎ ቴልስቶይ በማስታወሻ ደብተሩ ላይ ይህንን ቁምነገር ጽፏል። ላካፍላችሁ፦

በልጅነቴ ከእናቴ ጋር ዘወትር ትያትር ቤት እንሄድ ነበር። ቤተሰቦቼ ቢጠሯቸው የማይሰሙ ሃብታም ነበሩ። ሞስኮ ውስጥ በክረምት በረዶ ያለማቋረጥ ይወርዳል። ያኔ እናትና ልጅ ትያትር ቤት ውስጥ ነን።

ትያትር ቤቱ የትራጄዲ ተውኔት የሚያሳይ ከሆነ እናቴ ታለቅሳለች። እንባ በአይኖቿ ግጥም ብሎ በጉንጮቿ ያለማቋረጥ ይወርዳል። እኔ በልቤ 'እናቴ ምን አይነት ሩህሩህ ሴት ናት!' ብዬ አስባለሁ።

ተውኔቱ አልቆ ከትያትር ቤት ስንወጣ ሹፌራችንን መኪናው ውስጥ በቅዝቃዜ ተኮራምቶ እናገኘዋለን። እንግዲህ ሹፌራችን መኪናውን ጥሎ መሄድ አይችልም። መቼ ከትያትር ቤቱ እንደምንወጣ አይታወቅም። ሁሌም ዝግጁ እና ንቁ ሆኖ መጠበቅ አለበት። እንደዚያ ተጨብጦ፣ ተኮራምቶ እናቴ ዘወር ብላ እንኳን አታየውም። አንዳንዴ ሹፌራችን በቅዝቃዜ ሞቶ በሌላ ሹፌር የሚተካበት ግዜ ነበር። እናቴ አንድ ዘለላ እንባ እንኳን አታፈስም። በመጨረሻ የእናቴ እንባ የማስመሰልና የሃሰት መሆኑን ተረዳሁ።