Get Mystery Box with random crypto!

በጣም አስተማሪ ታሪክ __ አንድ በጣም ሌባ እና ብዙ ሴቶችን ደፍሮ የታሰረ ወጣት ነበረ ። ከእስር | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

በጣም አስተማሪ ታሪክ
__
አንድ በጣም ሌባ እና ብዙ ሴቶችን ደፍሮ የታሰረ ወጣት ነበረ ። ከእስር እንደተፈታ ወደ አያቶቹ ቤት ለጥየቃ እየተጓዘ እያለ ይመሽበትና ሰው ቤት ለማደር ፈልጎ የኣንድን ሰው ቤት ያንኳኳል

ሰውየው ሲከፍት ልጁ እባካቹ ተጓዥ መንገደኛ ነኝ እንድታሳድሩኝ ስል በፈጣሪ ስም እለምናልው ሲል ጠየቀ ሰውየው በለሰለሰ ድምፅ ይቅርታ አምኜ ላሳድርህ አልችልም ሴት ልጅ አለችኝ ይለውና በሩን ይዘጋል ።

ሁለተኛውም ቤት ሄዶ ጠየቀው ተመሳሳይ መልስ ሰጠው እና በሩን ዘጋ። ሶስተኛው ቤት አንኳኩቶ ሲጠይቅ ግባ ብለው አስገብተው እራት አበሉት ልጁ ማሰብ ጀመረ ወንድ ልጅ ቢኖራቸው ነው ብሎ አሰበ ግን ወደ ማደሪያው ሲሄድ ቆንጂዬ ሴት ልጅ ተኝታለች። ሰውየው ያረገውን ኮፍያ አውልቆ መሃላቸው ላይ አስቀምጦ ማንም ወደ ማንም እንዳይጠጋ አለና ልጁን አምንሀለው ብሎ ኩራዙን አጥፍቶላቸው ይተኛሉ። ልጁ በመደነቅ ምንም ሳያቀኝ አንዴት አመነኝ ብሎ እንቅልፍ ሳይወስደው አደረ በጠዋት ሊሄድ ሲወጣ ምግብ ቋጥረው ሰጡት።

ልጁ ከግቢው እንደወጣ ልጂትዋ በረንዳ ላይ ሆና ስታየው ተመለከተ ። ገብቶ ሰላም እንዳይላት በሩ ተዘግቷል አጥሩ ላይ ሆኖ ቆይ መጥቼ ሰላም ልበልሽ ሲል
ልጂቱ ያባቴን ኮፍያ ያልዘለልክ ልጅ አሁን አጥር ልትዘል ነው ብላ አሾፈችበትና ሄዳ በሩን ከፈተችለት።

ልጁም ፀጉርዋን እየዳበሰ እምነት ትልቅ እስር ቤት ነው እምነትን ስትቀበይ መንቀሳቀስ አትችይም እኔ ብዙ ጊዜ ታስሬ አቃለው ግን ምንም አይመስለኝም የእምነት እስር ቤት ግን ከምንም በላይ ትልቅ ነው አላት ይባላል።

እና አምነሀት ወይም አምነሺው ከጎዳሽ አትበሳጪ(ጭ) የጎዳህ ሰው እድሜ ልክ ፀፀት ይሆንበታል።

@gasha_tube