Get Mystery Box with random crypto!

**ዛሬ ምን አነበቡ?** ********* 'ቱትሲ የሆናችሁ ሁሉ ከመቀመጫቹህ አንዴ ብድግ በሉ' መም | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

**ዛሬ ምን አነበቡ?**
*********
"ቱትሲ የሆናችሁ ሁሉ ከመቀመጫቹህ አንዴ ብድግ በሉ" መምህር ቡሆሮ ጮክ ብሎ ተናገረ፡፡ በእጁ ላይ የክፍል ተማሪዎች ስም ዝርዝር ይዟል፡፡ በትኩረት እያጠናው ነው፡፡ ድንገት የኔስምን ሲያይ ወደኔ ማፍጠጥ ጀመረ፡፡

"ኢማኩኤሌ ኢሊባጊዛ..ለምንድን ነው የማትነሺው? ሁቱዎች ተነሱ ስል አልተነሳሽም፡፡ ትዋም ስል ቁጭ ብለሻል አሁን ቱትሲዎችም ብድግ በሉ ስል ንቅንቅ አላልሽም..ለምንድን ነው?" አለኝ ፈገግታ ፊቱ ላይ ቢታይም በድምፁ ግን ማስፈራራት ይነበባል፡፡
"አላውቅም መምህር" መለስኩለት
"እንዴ..ምኑን ነው የማታውቂው..ጎሳሽ ምንድን ነው እኮ ነው ያልኩሽ?"
"እኮ.እኔ እንጃ አላወቅም?"
"ሁቱ ነሽ ወይስ ቱትሲ?"
"እ..አላ..አ..ላውቅም መምህር"
"ውጪ....ጎሳሽን ካላወቅሽ ሁለተኛ እዚች ክፍል እንዳትረግጪ" በጩኸት አባረረኝ፡፡
ደብተሮቼን ሰብስቤ በሀፍረት ከክፍሌ ወጣው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሬ ሩዋንዳ ያለው የጎሳ ክፍፍል ጉዳይ በመጥፎ ሁኔታ አነቃኝ፡፡
*****
Left to Tell
ታሪካዊው የሩዋንዳ ጭፍጨፋ ላይ ተመስርቶ የተፃፈ እውነተኛ ታሪክ፡፡
ከጎሰኝነት የተነሳ ስር የሰደደ ጥላቻ፣ ቂም እና በቀል፣ እምነትና ይቅርባይነት መልኮችን ኩልል አድርጎ የሚያሳይ.
ከአሰቃቂ የዘር ፍጅት ለወሬ ነጋሪ የቀረች አንዲት ወጣት አስገራሚ ህይወት የሚተርክ፡፡

"Left to tell"(ሁቱትሲ ተብሎም በአማርኛ ተተርጉሟል) .ቀላል የሚመስሉ ማህበራዊ ሁኔታዎች በግዜ ካልታከሙ ምን ያህል እልቂት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ በግልፅ የሚያስተምር ነው፡፡
መፅሀፉ በ100 ቀናት ውስጥ ከ 800,000 በላይ ቱትሲ ሩዋንዳውያን አሳዛኝ እልቂት ይተርካል፡፡ እኛም በጊዜ ባይባልም ብዙ ሳይረፍድ የምንማርበት ነውና.
አንብቡት!
@gasha_tube