Get Mystery Box with random crypto!

ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gasha_tube — ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gasha_tube — ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ
የሰርጥ አድራሻ: @gasha_tube
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.79K
የሰርጥ መግለጫ

News & Entertainment Channel
⭕️በቅርቡ በethio sat የቴሌቪዥን ስርጭታችንን ልንጀምር ዝግጁነታችንን ጨርሰናል⭐️
#በዚ_ቻናል_ያዘጋጀንላቹ_ፕሮግራሞች ።
➠ ዜናዎች ➠ መዝናኛዎች
➠ አስገራሚ ታሪኮች ➠ ስለ ጤናዎ አዳዲስ መረጃዎች
➠ የቢዝነስ አሳቦች ➠ አነቃቂ ምክሮች
➠የቴክኖሎጂ ዜናዎች
➠ ኢትዮጵያዊ የሆኑ እሴቶች በየቀኑ ለእናንተ
እናቀርባለን

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-01-18 09:19:08
ከዚህ በኋላ ወንድ ሆኖ ሴት ወይም ህፃን ፊት መምሰል ቀረ
                  0928025669
ፀጉሬ ገባ ብሎ መሳቀቅም ቀረ

ስለ minoxidil ዝና ከሰማሁ እንኳን ቆየት ብዬ ነበር ነገር ግን አብዛኛዉ የፀጉር እና የፂም ምርቶች ውጤታማነታቸው ያን ያህልም ስለነበር አቅራቢያዬ ያሉ 2 ጓደኞቼ minoxidil ለፂማቸው ተጠቅመው ለውጡን ገና በ1 ወር ከ10 ቀን አካባቢ ሳይ ነበር ሲወራለት የነበረው ልክ እንደነበር በደንብ ያረጋገጥኩት

ከዛም ነው እኔም ተጠቅሜ ተደስቼበት ከ Israel እና USA ሀገር minoxidil Kirkland እያስመጣን በአጭር ጊዜ ብዙ ደንበኞችን ማፍራት የቻልነው አሁንም ለደንበኞቻችን ተደራሽነታችንን ለማስፋት በተለያዩ ማህበራዊ ድረገፃች መተናል።

      ምርታችን  minoxidil
በFDA እውቅና ያገኘ
amazon , ebay እና የመሳሰሉት መገበያያ ስፍራ ላይ 5 star ያገኘ
በdermatologist የተረጋገጠ

በተጨማሪም በምርታችን ውጤታማነት እርግጠኛ ስለሆንን ከgurantee(ዋስትና) ጋር መተናል

ባሁኑ ዙር ካስገባነው ትንሽ ምርት ስለሆነ የቀረን ሳያልቅ ይደውሉ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
          𝐂𝐀𝐋𝐋 𝐓𝐄𝐗𝐓     
     𝗣𝗵𝗼𝗻𝗲 ☞ 0928025669
𝗧𝗲𝗹𝗲𝗴𝗿𝗮𝗺 ☞ @SinaMarket_Manager
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
213 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 21:59:24
የሰርክ ፀሎት

የማያረጅ ፣ የማይቀጭ ፣ ወረት አልባ ፍቅር ስጠኝ ፤ ማግኘቴ ውስጥ የምሰጠው ፣ የማግዘው ፣ የሚደሰት ይኖረኝ ዘንድ ቸር ልብ ስጠኝ ፦

የምችለውን ችግር ስጠኝ ፣ መኖሬ በሰው ቸርነት ይቀጥል ዘንድ የምለምን አልሁን ፦

ሳጠፋ ይቅርታ የሚጠይቅ ልቦና ስበደል ይቅርታ አድራጊ ልብ ስጠኝ፦

ገመና የምሸሸግ ፣ ብልግናን የማላጎላ ፣ ዘመዴ የሆነውን የሰው ልጅ የምወድ እና የምረዳ አድርገኝ ፦

እንግዳ እንደሆንኩ ስኖር በዚች አለም ይገባኝ ዘንድ ልቦናዬን አብራልኝ !

ስለ
ሆነልኝ ፣ ስለምታረግልኝ ነገር እኔ ባሪያህ አመሰግንሃለሁ



አሜን

@gasha_tube
149 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-08 13:37:24
#ሄፕኖሲስ (አፍዝ አደንግዝ)
ሄፕኖሲስ ይባላል ሰዎችን የማደንዘዝ ጥበብ።ይህ ጥንቆላ ወይም ድግምት
አይደለም…በሳይንስ የተረጋገጠ ነገር እንጂ። ሄፕኖሲስ አድራጊው ሰው
በሰዎች ህቡዕ ህሊና ውስጥ ሃሳብን ይቀብራል። እነዚህ ሰዎች አንዴ ሄፕኖታይዝ ከተደረጉ በኋላ እርሱ (ሄፕኖታይዝ አድራጊው) የነገራቸውን ሁሉ ያምናሉ።ይህ የሚነድ ከሰል ነው ብሎ በረዶ በእጃቸው ላይ ቢያደርግ፤ አቃጠለን ብለው ይጮሃሉ።በረዶ የሚያቃጥላቸው በአእምሯቸው ላይ ብቻ አይደለም፤ የምርም ልክ ከሰል እንደጠበሰው ሆኖ እጃቸው ላይ የቃጠሎ ጠባሳ ይቀራል።

#ይህ_እንዴት_ይሆናል ?
ሄፕኖሲስ መሰረቱን ያደረገው Suggestion (ቅድመ ነገራ) ላይ ነው። ለምሳሌ ሙዚቃን ስታዳምጥ በሃሳብ ወደሌላ ቦታ ተጉዘህ አታውቅም? ወደ ልጅነትህ ተመልሰህ…የኩበት ሽታ፣ የአበቦች መዓዛ፣ የሰዎች ጫጫታን ሁሉ በአንድ ሙዚቃ ምክንያት ታስታውሳቸዋለህ።ይህ ሙዚቃም አንተን ሄፕኖታይዝ አድርጎ ወደ ሌላ አለም ይወስድሃል።በተመሳሳይም ሄፕኖሲስ አድራጊውም ቃላትን ለህቡዕ ህሊናህ ይነግረዋል።ለምሳሌ ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ስምህን አታስታውስውም ካለህ…ስምህን ትረሳዋልለውህ። እግርህን ማንቀሳቀስ አትችልም ካለህ… እግሮችህ ከመሬት ጋር ይጣበቃሉ የእርሱ ቃላት የአንተን አእምሮ ይቆጣጠሩታል።

ይህ እንዲሆን ግን አንድ ቅድመ ሁኔታ ያስፈልጋል…ይህም አእምሮህ አሁን
ካለበት የአልፋ ሁነት…ወደ ስክነት (ቴታ ሁነት) መግባት ይኖርበታል።
እንዴት ወደ ቴታ ሁነት መግባት ይቻላል? እንዴትስ ራሳችንን ሄፕኖታይዝ አድርገን
የሚደንቅ ለውጥን በህወታችን ላይ ማምጣት እንችላለን? #ተአምረኛው_አእምሮህ መጽሐፍ ራሳችንን ሄፕኖታይዝ አድርገን በህይወታችን ለውጥ የምናመጣበትን ጥበብ ያስተምረናል።


@gasha_tube
8 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 22:41:50
**"አንዳንድ ጊዜ ብዙም ማህበራዊ መስተጋብር የሌላቸው ከሰው መሀል ወጥተው ዳር የሚይዙ ሰዎች ማህበራዊ ኑሮ የሚጠሉ አይደለም ፤ ከዚህ ይልቅ የውሸት ድራማን ፣ ድድብናንና አስመሳይነትን መቋቋም ስለሚከብዳቸው ነው።"**

#Osho /ኦሾ
267 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 19:45:07
ለሴቶች የሚሆን የገና አሪፍ ስጦታ

haino teko Germany RW15

የሴቶች ስማርት ሰዓት
ውሀ የማያበላሸው
በብሉቱዝ ከስልክ ጋር የሚገናኝ
ስልክ መደወል እና መልክት መላክ የሚያስችል
ስፖርት ስንሰራ ይቆጥርልናል
ስልካችን ሲጠፋ ለመፈለጊያ ያግዘናል
የልብ ምት እና ደም ግፊት ይለካል

specification
Model RW-15 2022
Brand Haino Teko
Wireless charger,
1 charge 2 to 3 days
Call option, loudspeakers
Ip 68 Waterproof
WhatsApp, Facebook, Message, Gmail, other App Notifications
Heart rate monitor , ECG, BPM
Step counting
Bluetooth connection
Anti Lost Option
Android and iOS
Color White
Connectivity Bluetooth
Screen Size 46 mm
Stirp 3Strap ,Leather, Ceramic, Silicone
Steel Battery Capacity 45days Standby

ዋጋ፦ 4,500 ብር ብቻ


የመረጡትን እቃ ይዘዙ፤ ያሉበት እናደርሳለን!!
ስልክ:
229 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 14:20:30
ለወንዶች እና ለሴቶች የፀጉር መርገፍን ይከላከላል ፣ መላጣነትን ለመቀነስ ፣ በጭንቅላቱ ላይ     

የደም ዝውውርን ለማገዝ ይረዳሉ ፀጉር ጥቁር እና ወፍራም ያደርጋል።

Call +251928025669

★ ከዕፅዋት የተቀመሙ ንጥረ ነገሮች ሲሆኑ ። ካንታሎፕ ፣ ነጭ ጊንሰንግ ፣

የዘንባባ ቅጠል ፣ የተሰራ።

,, ፀጉር የሸሸበትን እና ማብቀል ያቆመበትን ቦታ ከንደገና በአጭር ጊዜ ውስጥ

ያንሰራራል እና ያበቅላል።

„ Cantaloupe extract ፀጉር ተነቃቅሎ መውደቅን ለመግታት የጥቁር ፀጉር ርዝመት እና ጥንካሬን እንዲኖር ያደርጋል፣

> ፀጉርን ለስላሳ እና አንጸባራቂ ያደርገዋል

„ Ginseng extract የራስ ቅል ውስጥ ያሉትን ሕዋሳት ስርጭት ያነቃቃል

> ለፀጉር ሥሮች ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዘ፡

የፀጉር እድገትን ያፋጥናል እና የፀጉር ሥሮችን ይመግባል።

- የፀጉር መጥፋትን ይቀንሳል።

> የዘንባባ የከርነል የተፈጥሮ ዕፅዋት ሲሆን።

➢ በጄኔቲክ ምክንያት የፀጉር መርገፍ እንዲሁ ይከላከላል ፡

በፀሐይ ጨረር ምክንያት ለሚፈጠሩ የፀጉር ችግሮችን ይገታል የስሮች መበላሸት እና ከውጭ ብክለት ይከላከላል። ደረቅ እና የተከፈለ ጫፎችን ለማቆየት ይረዳል

Price

1st quality 3000 birr

Order now

Call +251928025669
326 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-19 21:56:23
አንድ ፈረስ ብቻ የነበረው አንድ ገበሬ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን፥ ፈረሱ ለግሞ ከቤቱ ያመልጣል።

ጎረቤቶቹም እቤቱ መጥተው “ፈረስህ መጥፋቱንና ማዘንህን ሰማን። ልናፅናናህ መጥተን ነው።” አሉት።

ገበሬውም “ አላዘንኩም! ለበጎ ነው” አላቸው።

ከጥቂት ቀናት በኋላ ፈረሱ ከጠፋበት ቦታ ብዙ ወርቅና ማዕድናት፥ አስለምዶ ከጫነው ሰው አምልጦ ገበሬው ጋ ይመለሳል።

ጎረቤቶቹ ወደ ቤቱ መጥተው "እንኳን ደስ አለህ። ፈረስህ ብዙ ወርቅና ብር ይዛልህ በመምጣቱ እንደተደሰትክ ሰምተን መጣን። " አሉት።

እሱም "ብዙም አልተደሰትኩም። ለበጎ ነው!" አላቸው።

ከጥቂት ጊዜም በኋላም ፈረሱ የብቸኛ ወጣት ልጁ እግር በርግጫው ይሰብረዋል።

ጎረቤቶቹም አሁንም መጥተው " የልጅህ እግር መሰበር አይተህ እንዳዘንክ ሰምተን ልናፅናናህ መጣን። " አሉት።

እሱም በመቀጠል እንዲህ አላቸው "ብዙም አላዘንኩም። ለበጎ ነው!"

ከጥቂት ቀናት በኋላ በሀገሪቱ ከፍተኛ ጦርነት ተከፍቶ፤ ሁሉም ጤነኛ ወጣት በግዴታ እንዲዘምት አዋጅ ተላለፈ። የጎረቤቶቹም ልጆች ሲዘምቱ፤ የእርሱ ልጅ እግሩ ስለተሰበረ ከዘመቻው ይቀራል።

ከጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነቱ አለቀ። ከጦርነቱ የተረፈ አንድም ወጣት አልነበረም። ጎረቤቶቹም ልጆቻቸው መሞታቸው ተነገራቸው።

ገበሬውም ወደ ሰማይ አንጋጦ "የልጄ እግር መሠበር ለበጎ ሆነለት። ተመስገን!" አለ።

ወዳጄ፦ በነገር ሁሉ 'ሁሉም ለበጎ ነው!' በል።

መልካም ሁሉ ተመኘዉላቹ

@gasha_tube
174 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-13 21:13:15
ፒተር ቤሊሽ Game of thrones ውስጥ ያለ ብልህና ተንኮለኛ ገፀባህርይ ነው። ነገር ግን ፊልሙ ላይ አንዳንድ ቦታ የሚናገራቸው ነገሮች ይገርሙኛል። ፒተር ከአንድ ሌላ ገፀባህርይ ጋር ካወራ ( በተለይ ከቫሪስ) የሆነ አንድ የሚያስደንቃችሁን ንግግር ይናገራል። አንድ ቦታ ላይ ለሳንሳ ይመስለኛል እንዲህ ይላታል። "It doesn't matter what we want, once we get it, then we want something else."

የሰው ልጅ ያልተገደበ ፍላጎቱ ውስጥ ይዋልላል። ዛሬ ቀዩን መኪና ግዛ ነገ ሌላ ያምርሃል። ዛሬ ቤት ግዛ ነገ ሌላ ያምርሃል። ዛሬ አንዱን አግኝ ነገ ሌላ ነገር ፍለጋ ላይ ነህ። ባለህ ነገር አትረካም።

እድሜ ልካችንን አንዱን ስናገኝ ሌላ ስንፈልግ እየዳከርን እንኖራለን። ፍላጎታችን ሸክም ሆኖብናል። ከፍላጎታችንን ጋር እንቅበዘበዛለን። ፒተር እውነቱን ነው።

ምኞ
ትና ፍላጎትህ ላይ መሰልጠን ካልቻልክ የፍላጎትህ ባሪያ ነው የምትሆነው!!
@gasha_tube
200 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, edited  18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 21:00:10
አትቁም_ወደ_ነገ_ሂድ…

"… እንደኔ ግን መሄድ ከመቆም ይሻላል። ... መቆም ቢያንስ ለጠላቶችህ የታወቀ አድራሻ ይሰጣል። መሄድ ግን ቢያገኙህ እንኳን ለፍተው እንዲያገኙህ ያደርጋል።

መቆም በቆምክበት ቦታ ብቻ ያለውን እድል እንድትጠቀም ያደርግሃል ፤ መሄድ ግን የማታውቀውንም ዕድል እንድትሞክር ይረዳሃል። ስትቆም መጀመሪያ ታረጃለህ ፣ ቆይቶም ትበሰብሳለህ። ስትሄድ ግን መጀመሪያ ትደክማለህ ፣ ቀጥሎ ግን ትጠነክራለህ።

ባለቀ ትናንት አትታሰር ፣ በተበላ ዛሬ አትወሰን ፤ ይልቅ ወደ ማይታወቀው ነገ ሂድ። ነገ ወዳ አንተ ሳይመጣብህ አንተ ወደ ነገ ሂድ።

አንድ ቦታ ላይ የግድ እንድንቆም!ቢፈለግ ኖሮ እግር ሳይሆን እንደ ዛፍ ሥር ይሰጠን ነበር። የመሄዳችን ዋናው ምክንያቱ የምንቆይበት ምክንያት አለመኖሩ ነው።"

በዳንኤል ክብረት


@gasha_tube
180 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 20:31:26
….. እኔ ጥበብን እሻለሁ፤ ልቤ ዕውቀትን ተቃትታለች፤ በጥበብ ፍቅር ተነድፍያለሁ፤ በጥበብ ገመዶችም ታስርያለሁ፡፡ ጥበብ ከብዙ ወርቅና ብር ይልቅ ተልቃለችና፡፡ ጥበብ በምድር ከተፈጠሩት ሁሉ ትበልጣለች፡፡ ጥበብ ለልብ አስደሳች፣ለዓይኖች መብራት፣ ለእግር ቅልጥፍና፣ ለደረት ጥሩር፣ ለራስ አክሊል፣ ለአንገት የወርቅ ማርዳ፣ ለወገብ መታጠቂያ ለጆሮ ማዳመጫ ለልብ ብልሃት ነች፡፡…..

….. ጸሎት ማድረግ የምችል አይመስለኝም ፡፡ ሁልጊዜ ለጸሎት ስቆምም ሆነ ስንበረከክ የምለው ይጠፋኛል፡፡ምሰጋና ሳበዛ የጎደለኝ ትዝ ይለኛል፡፡ ጥያቄ ሳበዛ የተደረገልኝ በዐይነ ሕሊናዬ ይመጣና ውለታ ቢስ የሆንኹ ይመስለኛል፡፡…..
… እኛ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈጸም ወይም ችግር ለመፍታት ሰንነሳ እግዚአብሔር የእኛን ጉዳይ ሊፈጽም፣የእኛን ችግር ሊፈታ ይነሳል፡፡


….. በጎነት ወይም ደግነት ሌሎችን የማነቀሳቀስ ሀይል አለው፡፡ ደግነት ከአንዱ ወደ አንዱ የሚቀጣጠል ችቦ ነው፡፡ አዋቂዎች እንደሚሉት ደግነት ጥሩነት አይደለም ከዚያም በላይ ነው፡፡ ጥሩነት የደግነት አነስተኛ ደረጃው ነው ፡፡ ደገነት በውስጡ ባልንጀርነትን፣ ለጋስነትን፣ፍቅርንና ትህትናን የያዘ ነው፡፡…

…. ሀገር ቀዝቃዛ ሊሆ
ን ይችላል ግን አይበርድም፤ሀገር በረሃ ሊሆን ይችላል ግን አያቃጥልም፤ሀገር ሸንተረር ሊሆን ይችላል ግን አያታክትህም፡፡ በተለይ እኛ ኢትዮጵያዊያን ሀገራችን ምንም ትባል ምንም ለእኛ ምቹ ናት እንወዳታለን ፡፡…..

*ሚተራሊዮን*
ዶ/ር ዓለማየሁ
ዋሴ**
@gasha_tube
222 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ