Get Mystery Box with random crypto!

የሰርክ ፀሎት የማያረጅ ፣ የማይቀጭ ፣ ወረት አልባ ፍቅር ስጠኝ ፤ ማግኘቴ ውስጥ የምሰጠው | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

የሰርክ ፀሎት

የማያረጅ ፣ የማይቀጭ ፣ ወረት አልባ ፍቅር ስጠኝ ፤ ማግኘቴ ውስጥ የምሰጠው ፣ የማግዘው ፣ የሚደሰት ይኖረኝ ዘንድ ቸር ልብ ስጠኝ ፦

የምችለውን ችግር ስጠኝ ፣ መኖሬ በሰው ቸርነት ይቀጥል ዘንድ የምለምን አልሁን ፦

ሳጠፋ ይቅርታ የሚጠይቅ ልቦና ስበደል ይቅርታ አድራጊ ልብ ስጠኝ፦

ገመና የምሸሸግ ፣ ብልግናን የማላጎላ ፣ ዘመዴ የሆነውን የሰው ልጅ የምወድ እና የምረዳ አድርገኝ ፦

እንግዳ እንደሆንኩ ስኖር በዚች አለም ይገባኝ ዘንድ ልቦናዬን አብራልኝ !

ስለ
ሆነልኝ ፣ ስለምታረግልኝ ነገር እኔ ባሪያህ አመሰግንሃለሁ



አሜን

@gasha_tube