Get Mystery Box with random crypto!

ፒተር ቤሊሽ Game of thrones ውስጥ ያለ ብልህና ተንኮለኛ ገፀባህርይ ነው። ነገር ግን ፊል | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

ፒተር ቤሊሽ Game of thrones ውስጥ ያለ ብልህና ተንኮለኛ ገፀባህርይ ነው። ነገር ግን ፊልሙ ላይ አንዳንድ ቦታ የሚናገራቸው ነገሮች ይገርሙኛል። ፒተር ከአንድ ሌላ ገፀባህርይ ጋር ካወራ ( በተለይ ከቫሪስ) የሆነ አንድ የሚያስደንቃችሁን ንግግር ይናገራል። አንድ ቦታ ላይ ለሳንሳ ይመስለኛል እንዲህ ይላታል። "It doesn't matter what we want, once we get it, then we want something else."

የሰው ልጅ ያልተገደበ ፍላጎቱ ውስጥ ይዋልላል። ዛሬ ቀዩን መኪና ግዛ ነገ ሌላ ያምርሃል። ዛሬ ቤት ግዛ ነገ ሌላ ያምርሃል። ዛሬ አንዱን አግኝ ነገ ሌላ ነገር ፍለጋ ላይ ነህ። ባለህ ነገር አትረካም።

እድሜ ልካችንን አንዱን ስናገኝ ሌላ ስንፈልግ እየዳከርን እንኖራለን። ፍላጎታችን ሸክም ሆኖብናል። ከፍላጎታችንን ጋር እንቅበዘበዛለን። ፒተር እውነቱን ነው።

ምኞ
ትና ፍላጎትህ ላይ መሰልጠን ካልቻልክ የፍላጎትህ ባሪያ ነው የምትሆነው!!
@gasha_tube