Get Mystery Box with random crypto!

አትቁም_ወደ_ነገ_ሂድ… '… እንደኔ ግን መሄድ ከመቆም ይሻላል። ... መቆም ቢያንስ ለጠላቶችህ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

አትቁም_ወደ_ነገ_ሂድ…

"… እንደኔ ግን መሄድ ከመቆም ይሻላል። ... መቆም ቢያንስ ለጠላቶችህ የታወቀ አድራሻ ይሰጣል። መሄድ ግን ቢያገኙህ እንኳን ለፍተው እንዲያገኙህ ያደርጋል።

መቆም በቆምክበት ቦታ ብቻ ያለውን እድል እንድትጠቀም ያደርግሃል ፤ መሄድ ግን የማታውቀውንም ዕድል እንድትሞክር ይረዳሃል። ስትቆም መጀመሪያ ታረጃለህ ፣ ቆይቶም ትበሰብሳለህ። ስትሄድ ግን መጀመሪያ ትደክማለህ ፣ ቀጥሎ ግን ትጠነክራለህ።

ባለቀ ትናንት አትታሰር ፣ በተበላ ዛሬ አትወሰን ፤ ይልቅ ወደ ማይታወቀው ነገ ሂድ። ነገ ወዳ አንተ ሳይመጣብህ አንተ ወደ ነገ ሂድ።

አንድ ቦታ ላይ የግድ እንድንቆም!ቢፈለግ ኖሮ እግር ሳይሆን እንደ ዛፍ ሥር ይሰጠን ነበር። የመሄዳችን ዋናው ምክንያቱ የምንቆይበት ምክንያት አለመኖሩ ነው።"

በዳንኤል ክብረት


@gasha_tube