Get Mystery Box with random crypto!

ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gasha_tube — ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gasha_tube — ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ
የሰርጥ አድራሻ: @gasha_tube
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.79K
የሰርጥ መግለጫ

News & Entertainment Channel
⭕️በቅርቡ በethio sat የቴሌቪዥን ስርጭታችንን ልንጀምር ዝግጁነታችንን ጨርሰናል⭐️
#በዚ_ቻናል_ያዘጋጀንላቹ_ፕሮግራሞች ።
➠ ዜናዎች ➠ መዝናኛዎች
➠ አስገራሚ ታሪኮች ➠ ስለ ጤናዎ አዳዲስ መረጃዎች
➠ የቢዝነስ አሳቦች ➠ አነቃቂ ምክሮች
➠የቴክኖሎጂ ዜናዎች
➠ ኢትዮጵያዊ የሆኑ እሴቶች በየቀኑ ለእናንተ
እናቀርባለን

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-10-19 20:56:04
1.4K views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 20:21:19 መቶ በመቶ እርግጠኛ!

አንድ እጅግ በጣም የተራበ ተኩላ አንድን ከጓደኞቿና ከእረኛዋ የተለየች በግ ከሩቅ ተመለከተ፡፡ መልካም ራት እንዳገኘ ቢያስብም ከሩቁ አይታው የመደንበር ምልክት ስላሳየች ቢሮጥ ሊደርስባት እንደማይችል ስላሰበ እያግባባ ርቀቱን ለማሳጠርና በቀላሉ ለመያዝ በሚመቸውና ማምለጥ በማትችልበት ክልል ውስጥ ለመቅረብ አሰበ፡፡

ትንሽ እርምጃ ጠጋ አለና ድምጹን ከፍ አድርጎ፣ “የዛሬ ሁለት አመት በጣም ተዳፍረሽኝ ነበር” አላት፡፡ በጊቱ ለማምለጥ ሲቃጣት “የዛሬ ሁለት ዓመት” በማለት ስለዋሸ አበሳጭቷት፣ “ምንድን ነው የምታወራው፣ የዛሬ ሁለት አመት እኮ እኔ አልተወለድኩም ነበር” አለችው፡፡

ተኩላው እንደገና ትንሽ እርምጃዎችን ከጨመረ በኋላ፣ “ባለፈው አመት የመጫወቻ ሜዳየን ሳር በልተሽ የጨረስሽው አንቺ መሆኑን ሰምቻለሁ” አላት”፡፡ በጊቱ ጊዜ ሳታባክን ማምለጥ እንዳለባት ቢገባትም አሁንም ለዚህ ቅድ ውሸቱ ተገቢውን ምላሽ መስጠት እንዳለባት ስላሰበች፣ “የዛሬ አመት ሳር የሚባል ነገር አልቀመስኩም፣ እሺ!!!” አለችው፡፡

ተኩላው ዓላማው የተሳካለት መሆኑ ስለገባው፣ አሁንም ትንሽ ጠጋ ብሎ፣ “ከስድስት ወር በፊት እኛ ተኩላዎች ብቻ ከምንጠጣበት ምንጭ ተደብቀሽ ስትጠጪ ቆሻሻሽን አራግፈሽ አደፍርሰሽብናል” አላት፡፡ በጊቱም፣ “አሁንስ አበዛው፣ አንድ ጊዜ ጠጋ ብዬ በጩኸት ልክ ልኩን እነግረውና እሮጣለሁ” ብላ በማሰብና የተወሰኑ እርምጃዎችን ጠጋ በማለት፣ “አሁንስ አበዛኸው! የዛሬ ስድስት ወር ገና የእናቴን ጡት በመጥባት ላይ ስለነበርኩ ውኃ መጠጣት አልጀመርኩም” ብላ ጮኸች፡፡ በዚህ ጊዜ በጊቱ ማምለጥ የማትችልበት ቅርበት ውስጥ ራሷን ስላቀረበች ተኩላው ያቀደውን እቅድ ፈጸመ፡፡

አብዛኛው የሕይወት ክስተቶች በመደራደር፣ በመከራረከርና እስከመጨረሻው ሃሳብን በመለዋወጥ ሊያዙ የሚገባቸው የመሆኑ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አንዳንድ ጊዜ ግን ጊዜ ሳናባክን ካልተለየን ራሳችንን ለወጥመድ አሳልፈን የምንሰጠጥባቸው ሁታዎች እንዳሉ ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡

•  መቶ በመቶ ማድረግ እንዳለብህና ጊዜውም ትክክለኛ እንደሆነ ያመንክበት ነገር ካለ አታዘግየው፡፡

•  መቶ በመቶ መወሰን እንዳለብህና ጊዜውም ትክክለኛ እንደሆነ ያመንክበት ነገር ካለ አንድ ቀን አታሳድረው፡፡

•  መቶ በመቶ መለየት የሚገባህ ሰው ወይም ሁኔታ እንዳለ ካመንክና ጊዜውም ትክክልኛ እንደሆነ ካመንክ አንድ ቀን አታሳድረው፡፡

•  መቶ በመቶ እንደማያዛልቅህ እርግጠኛ በሆንክበት ስፍራና ሁኔታ ውስጥ ምን ታደርጋለህ?

•  እንደማያስቀጥልህና እንደማያዛልቅህ በሚገባ እርግጠኛ ከሆንክበት ሰው ጋር ለምን ትደራደራለህ?

መወሰን፣ መውጣት፣ ማቆም ፣ መለየት . . . እንደሚገባህ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆነህ በመደራደር ያከረምከው ጉዳይ፣ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ሳታስበው መውጣት የማትችልበትን ሁኔታ ፈጥሮ እንደሚቆይህ አትዘንጋ፡፡

Dr-Eyob-Mamo
@gasha_tube
2.2K views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 20:20:56
1.7K views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 18:57:02 ሐብታም የመሆን ጥበብ Rich Dad Poor Dad
72 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 18:56:46
#ሐብታም_የመሆን_ጥበብ
#


ዝናው በአለም የናኘው ሪች ዳድ፣ ፑር ዳድ (Rich Dad, Poor Dad) መጽሐፍ ሐብታም የመሆን ጥበብ በሚል ተተርጉሞ ለሁለተኛ ጊዜ ታትሞ በገበያ ላይ ውሏል፡፡

ከ35 ሚሊዮን ኮፒ በላይ የተሸጠ፣ ከ52 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች የተተረጎመ፣ ለ20 ዓመታት የምንጊዜም ምርጥ ግላዊ የፋይናስ መጽሐፍ ለመሆን የበቃ፣ የሮበርት ኪዮሳኪ ድንቅ መጽሐፍ!!

ደሀው አባትና ሀብታሙ አባት ስለገንዘብ የሚሰጡት አስገራሚ ትምህርት በማራኪ ሁኔታ የቀረበበት፣ ሚሊዮኖች ስለገንዘብ ያላቸውን አስተሳሰብ የቀየረ መጽሐፍ!

ዩኤስ ኤ ቱደይ #ሰዎች_እንዴት_ሚሊየነር_እንደሚሆኑ ያስተምራል ሲል…

ዎል ስትሪት ጆርናል ደግሞ #ሐብታም_ለመሆን_የሚፈልጉ_ሁሉ_ሊያነቡት_የሚገባ ምርጥ መጽሐፍ ሲል ነው ያንቆለጳጰሰው!
@gasha_tube
76 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 15:50:20
ዘመናዊ የልብስ ቁም ሳጥን ባለ 3
0928025669
ቀለል ያለ ከቦታ ወደ ቦታ ለማንቀሳቀስ የማያስቸግር
ተሰካኪ ብረቶች የሆኑ
ቁመት 175 ሳ.ሜ
የጎን ስፋት 130 ሳ.ሜ
ወደ ዉሰጥ 45 ሳ.ሜ
ልብሱ ሸራ ሲሆን
በሩ በዚፕ ይዘጋል
ፍሬሙ የብረት ቱቦዎች ናቸዉ
መገጣጠሚያው ካርቦኔትድ የሆነ ጠንካራ ፕላስቲክ ነው
መደርደሪያው የሸራ መደርደሪያ ነዉ
ዋጋ 3800 ብር
0928025669
Additionally #Free #delivery
በነፃ እቤቶ ድረስ እናደርሳለን
ለክፍለ ሀገር ደንበኞች EMS / DHL እናደርሳለን
255 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 22:09:21 ዛሬ የምነግራቹ ያገለገለ ስልክ ከ ሰው ላይ ስትገዙ ማድረግ ያለባችሁን ጥንቃቄ እና ማረጋገጥ ያለባችሁን ነገሮች ናቸው....

ከስር የዘረዘርኳቸው ነገሮች በ እናንተ ፍላጎት ልትተዋቸውም ትችላላቹ

➜ በመጀመሪያ ከስልኩ Screen ጀምሩ ና የፊት screen ኑ አለመሰበሩን ጉዳት አለመድረሱን አጣሩ

➜ በመቀጠል የፊት ካሜራው ላይ ጉዳት አለመድረሱን አጣሩ / ጥራቱን ሳይሆን ከተሰበረ ምናምን

➜ አሁን ወደ ጎን ሂዱና የጎን volume እና power buttons መታዘዝ አለመታዘዛቸውን አረጋግጡ

➜በመቀጠል ወደ ኀላ ዙሩና ከኀላ ያሉትን እንደፊቱ አጣሩ

➜ቀጣይ ስልኩ የ sim card በትክክል መቀበሉን, Sd card, Earphone እና በተጨማሪም USB የሚቀበል መሆኑን አጣሩ/ ይሄ ሊቀርም ይችላል ግን ቢሰራ በጣም ጥሩ ነው በቀላሉ በ Connector usb flash በስልካቹ መጠቀም ትችላላቹ። ስልኩን የ ኀላ ክዳን የሚከፈት ከሆነም የ ባትሪ power ስንት እንደሆነ ማየት ትችላላቹ።የማይከፈት ከሆነ ወይም ካልተፃፈ ቡሀላ መፍትሄውን ነግራቹአለው።

➜ ቀጣም ወደ ውስጥ እንግባ የ lock screen check አድርጉ ወደ ውስጥ ገብታችሁም Call, sms,WiFi አጣሩ
➜ አሁን የስልኩን camera, ቅድም ያስገባቹትን sd card ማንበቡን አረጋግጡ

➜ አሁን ከዚህ ቡሀላ ያለውን ሙሉ ነገር ለማጣራት አንድ አኘ ብቻ ስልኩ ላይ መጫን ይበቃል።Device info ይባላል በጣም ገራሚ አኘ ነው ከሌሎች አፓች በተለየ መልኩ ሁሉንም የስልኩን መረጃ ማረጋገጥ ያስችላችኀል።ቅድም ያልኳችሁንም Battery States በዚህ አኘ ማየት ትችላላቹ።

➜ ምናልባት ሰውየው አኘ በ xender ስትላላኩ እንዳይደብረው በቀላሉ አፑን መጀመሪያ memory card ላይ copy አርጋቹ አስቀምጡ በመቀጠልም Memory check ለማረግ ስታስገቡ install አርጋቹ ማየት ነው።አፑ ሁሉንም ነገር ያሳያል

አሁን አንድ የማቀር ነገር አለ የምትገዙት ስልክ Original ወይስ copy መሆኑን ማረጋገጥ።ይሄም በፍላጎታችሁ ላይ ይወሰናል

መጀመሪያ ስልኩ ላይ *#06# አስገቡ እና የ ስልኩን  imei no አግኙ/ያዙ

http://www.imei.info ወደ ዚህ Website ሂዱ እና የ ስልኩን Imei no አስገቡ

ከዛ search አርጎ ያመጣው የዛን ስል information ከሆነ original ነው ማለት ለው የ ሌላ ስልክ info ካመጣ ደሞ FAKE



@gasha_tube
529 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 22:26:37
ማህበራዊ ገፆችን በመጠቀም በትንሽ ወጪ ብዙ ደንበኞች ጋር ይድረሱ፣ምርቶትን ያስተዋዉቁ፣ሽያጮን ይጨምሩ።

𝗥𝗲𝗮𝗰𝗵 𝗺𝗼𝗿𝗲 𝗰𝘂𝘀𝘁𝗼𝗺𝗲𝗿𝘀 𝗮𝘁 𝗮 𝗹𝗼𝘄 𝗯𝘂𝗱𝗴𝗲𝘁 𝘂𝘀𝗶𝗻𝗴 𝘀𝗼𝗰𝗶𝗮𝗹 𝗺𝗲𝗱𝗶𝗮.


ለድርጅትዎ፣ ለቢዝነስዎ፣ ለቻናልዎ እንዲሁም ለማንኛውም አይነት ምርት እና አገልግሎት አድቨርታይዚንግ ወይንም የማስተዋወቅ ስራ እንሰራለን።

ምርት ወይም አገልግሎትዎ ከብዙሀን ዘንድ እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ቻናልዎ እንዲያድግ ከፈለጉ፣ በብዙሀን ዘንድ በማንኛዉም ነገር እውቅና ከፈለጉ ትክክለኛዉ አማራጭዎ እኛ ነን።


የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

𝗙𝗮𝗰𝗲𝗯𝗼𝗼𝗸 𝗯𝗼𝗼𝘀𝘁
𝗧𝗲𝗹𝗲𝗴𝗿𝗮𝗺 𝗮𝗱𝘃𝗲𝗿𝘁𝗶𝘀𝗶𝗻𝗴

𝑩𝒓𝒂𝒏𝒅𝒆𝒅 𝒔𝒕𝒓𝒂𝒕𝒆𝒈𝒚
𝑫𝒊𝒈𝒊𝒕𝒂𝒍 𝑴𝒂𝒓𝒌𝒆𝒕𝒊𝒏𝒈 𝑺𝒕𝒓𝒂𝒕𝒆𝒈𝒚
𝒔𝒐𝒄𝒊𝒂𝒍 𝒎𝒆𝒅𝒊𝒂 𝒎𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕

𝗪𝗲𝗯𝘀𝗶𝘁𝗲 𝗗𝗲𝘀𝗶𝗴𝗻
𝗚𝗿𝗮𝗽𝗵𝗶𝗰 𝗗𝗲𝘀𝗶𝗴𝗻
𝗟𝗼𝗴𝗼 𝗗𝗲𝘀𝗶𝗴𝗻
𝗧𝗲𝗹𝗲𝗴𝗿𝗮𝗺 𝗕𝗼𝘁 𝗱𝗲𝘃𝗲𝗹𝗼𝗽𝗺𝗲𝗻𝘁
𝗽𝗼𝘀𝘁𝗲𝗿


𝘍𝘖𝘓𝘓𝘖𝘞 𝑼𝑺 𝑶𝑵 𝑺𝑶𝑪𝑰𝑨𝑳 𝑴𝑬𝑫𝑰𝑨 -----
𝗧𝗲𝗹𝗲𝗴𝗿𝗮𝗺 Channel:https://t.me/Sina_market_channel
𝗙𝗮𝗰𝗲𝗯𝗼𝗼𝗸: https://www.facebook.com/Snia.Market.Facebook
𝗜𝗻𝘀𝘁𝗮𝗴𝗿𝗮𝗺: https://www.instagram.com/Sina_Market_ethiopia

ያናግሩን

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
          𝐂𝐀𝐋𝐋 𝐓𝐄𝐗𝐓     
     𝗣𝗵𝗼𝗻𝗲 ☞ 0928025669
𝗧𝗲𝗹𝗲𝗴𝗿𝗮𝗺 ☞@SinaMarket_Manager
75 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 14:38:55 ተአምረኛው - አእምሮህ @ Enmare Book pdf


ርእስ ፦ ተአምረኛው - አእምሮህ
ምርጥ የ ሳይኮሎጂ መፅሐፍ


ተአምረኛው አእምሮህ በሕይወትህ ተአምራትን ለማድረግ በተጠንቀቅ ላይ
ነው፡፡ | የሚጠብቀው ያንተን ትእዛዝ ብቻ ነው!

ይህ መጽሐፍ እንዴት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ አእምሮህን እንደምታዝዘው የሚያስተምር መጽሐፍ ነው፡፡
527 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 20:51:05
#ተአምረኛው_አእምሮህ



ተአምረኛው አእምሮህ በሕይወትህ ተአምራትን ለማድረግ በተጠንቀቅ ላይ ነው፡፡  የሚጠብቀው ያንተን ትእዛዝ ብቻ ነው!  ይህ መጽሐፍ እንዴት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ አእምሮህን እንደምታዝዘው የሚያስተምር መጽሐፍ ነው፡፡

ሃኪሞች ለታካሚዎቻቸው የሚሰጡት የውሸት መድኃኒት #ፕላሲቦ ይባላል፡፡ ሰዎች ከካንሰር ተፈውሰዋል፤ ከሞት ወደ ሕይወት መጥተዋል፤ አንዳንዶች ምንም ማድረግ የማይችለውንና የውሸት የሆነውን መድኃኒት እውነተኛና ገዳይ ነው ብለው ራሳቸውን ለማጥፊያት ተጠቅመውበት ሞተዋል!!!

#የዳኑትም_የሞቱትም_ስላመኑ_እንጂ መድኃኒቱ የውሸት ነው፤ የውሸት!!!

አሁን ነው የአእምሮህን ተአምረኛነት የምትማረው፡፡

#ከሞት_ሕይወትን_ብትፈልግ -
ተአምሩ አእምሮህ ዘንድ ይገኛል፤

#ከውድቀት_ስኬትን_ብትመርጥ - ተአምረኛው አእምሮህ ይችላል፤

#ከአርባ_ቀን_እድልህ_ይልቅ በረከትን ብትሻ - አእምሮህ ተአምር ይሰራል፤

#ከድህነት_ሁለንተናዊ_ሀብትን_ብትፈልግ - ተአምረኛው አእምሮህ ዋስትናህ ነው፡፡

ይህ የሚሆነው ግን የፕላሲቦ ኢፌክት ሲገባህ፣ የአእምሮ ኒውሮኖች አሰራርን ስታውቅ፣ ጂኖችህ፣ ሴሎችህ፣ ሰውነትህ ከተአምረኛው አእምሮህ ጋር ያላቸውን ሚስጥር ስትረዳ ብቻ ነው፡፡

ተአምርን ከውጪ የሚጠብቁ ሰዎች ተአምረኛ አእምሮ እንዳላቸው የማያውቁ ናቸው፡፡ ይህ መጽሐፍ የአእምሯቸውን ተአምረኛነት በሳይንሳዊ መንገድ በማወቅ ትክክለኛ ለውጥ ለሚፈልጉ ሁሉ ተጻፈ!!

#ተአምረኛው_አእምሮህ መጽሐፍ
@gasha_tube
800 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ