Get Mystery Box with random crypto!

#ተአምረኛው_አእምሮህ ተአምረኛው አእምሮህ በሕይወትህ ተአምራትን ለማድረግ በተጠንቀቅ ላይ ነው | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

#ተአምረኛው_አእምሮህ



ተአምረኛው አእምሮህ በሕይወትህ ተአምራትን ለማድረግ በተጠንቀቅ ላይ ነው፡፡  የሚጠብቀው ያንተን ትእዛዝ ብቻ ነው!  ይህ መጽሐፍ እንዴት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ አእምሮህን እንደምታዝዘው የሚያስተምር መጽሐፍ ነው፡፡

ሃኪሞች ለታካሚዎቻቸው የሚሰጡት የውሸት መድኃኒት #ፕላሲቦ ይባላል፡፡ ሰዎች ከካንሰር ተፈውሰዋል፤ ከሞት ወደ ሕይወት መጥተዋል፤ አንዳንዶች ምንም ማድረግ የማይችለውንና የውሸት የሆነውን መድኃኒት እውነተኛና ገዳይ ነው ብለው ራሳቸውን ለማጥፊያት ተጠቅመውበት ሞተዋል!!!

#የዳኑትም_የሞቱትም_ስላመኑ_እንጂ መድኃኒቱ የውሸት ነው፤ የውሸት!!!

አሁን ነው የአእምሮህን ተአምረኛነት የምትማረው፡፡

#ከሞት_ሕይወትን_ብትፈልግ -
ተአምሩ አእምሮህ ዘንድ ይገኛል፤

#ከውድቀት_ስኬትን_ብትመርጥ - ተአምረኛው አእምሮህ ይችላል፤

#ከአርባ_ቀን_እድልህ_ይልቅ በረከትን ብትሻ - አእምሮህ ተአምር ይሰራል፤

#ከድህነት_ሁለንተናዊ_ሀብትን_ብትፈልግ - ተአምረኛው አእምሮህ ዋስትናህ ነው፡፡

ይህ የሚሆነው ግን የፕላሲቦ ኢፌክት ሲገባህ፣ የአእምሮ ኒውሮኖች አሰራርን ስታውቅ፣ ጂኖችህ፣ ሴሎችህ፣ ሰውነትህ ከተአምረኛው አእምሮህ ጋር ያላቸውን ሚስጥር ስትረዳ ብቻ ነው፡፡

ተአምርን ከውጪ የሚጠብቁ ሰዎች ተአምረኛ አእምሮ እንዳላቸው የማያውቁ ናቸው፡፡ ይህ መጽሐፍ የአእምሯቸውን ተአምረኛነት በሳይንሳዊ መንገድ በማወቅ ትክክለኛ ለውጥ ለሚፈልጉ ሁሉ ተጻፈ!!

#ተአምረኛው_አእምሮህ መጽሐፍ
@gasha_tube