Get Mystery Box with random crypto!

ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gasha_tube — ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gasha_tube — ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ
የሰርጥ አድራሻ: @gasha_tube
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.79K
የሰርጥ መግለጫ

News & Entertainment Channel
⭕️በቅርቡ በethio sat የቴሌቪዥን ስርጭታችንን ልንጀምር ዝግጁነታችንን ጨርሰናል⭐️
#በዚ_ቻናል_ያዘጋጀንላቹ_ፕሮግራሞች ።
➠ ዜናዎች ➠ መዝናኛዎች
➠ አስገራሚ ታሪኮች ➠ ስለ ጤናዎ አዳዲስ መረጃዎች
➠ የቢዝነስ አሳቦች ➠ አነቃቂ ምክሮች
➠የቴክኖሎጂ ዜናዎች
➠ ኢትዮጵያዊ የሆኑ እሴቶች በየቀኑ ለእናንተ
እናቀርባለን

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-09-29 16:13:53
𝗛𝗜𝗚𝗛 𝗤𝗨𝗔𝗟𝗜𝗧𝗬 𝗗𝗢𝗢𝗥𝗦 & 𝗙𝗜𝗩𝗘 𝗦𝗧𝗔𝗥𝗘 𝗘𝗹𝗲𝘃𝗮𝘁𝗼𝗿

* 0973329393
*0967292864
ፎቶ ላይ የምትመለከቱት በር
በውጪ ተመርተው በሃገራችን ኢትዮጵያ ዱከም 𝗘𝗔𝗦𝗧𝗘𝗥𝗡 𝗜𝗡𝗗𝗨𝗦𝗧𝗥𝗬 PARK የሚገጣጠሙ 100% ከብረት የተሰሩ ነገር ግን 100% የእንጨት ባህሪ ያላቸው ውበትን ከእንጨት ፣ ጥንካሬን ከብረት ያጣመሩ  security doors እነሆ...
ለመኖሪያ ቤቶች
ለሆቴሎች እና አፓርትመንት
ለሆስፒታሎች እና ለእምነት ተቋማት
ለቢሮ እና ለኮንዶሚንየም
ለዋና መግቢያ እንዲሁም ለውስጥ ለውስጥ ክፍሎች ምቹ ተደርገው የተሰሩ ዘመን አመጣሽ ውብ እና ጠንካራ በሮች

የማይዝግ 𝗚𝗮𝗹𝘃𝗮𝗻𝗶𝘇𝗲𝗱 የሚታጠቡ
በፀሃይ ብርሃን ብዛት fade የማያረጉ
በ 3 ቱም አቅጣጫ ከ 6 እስከ 10 ተወርዋሪ  ዘመናዊ እና ውብ የብረት በሮች ሲሆኑ ባህሪያቸው (Character) ግን የእንጨት ነው ማለትም በእጅ ሲነካ ወይም ሲመታ የሚያሰማው ድምፅም ሆነ አጠቃላይ ገፅታቸው የእንጨት ባህሪ የሆኑ ናቸው

ድምፅ የማያሳልፋ (𝗦𝗼𝘂𝗻𝗱-proof) እንዲሁም የትኛውም አይነት እርጥበት የማያበላሻቸው(𝗪𝗮𝘁𝗲𝗿-proof) ናቸው።

ከስድስት እስከ አስር ድረስ የሚደርስ የቁልፍ ተወርዋሪ ያለው 𝗦𝗲𝗰𝘂𝗿𝗲𝗱 ማስተር key ያለው  ነው

ከዉስጥ ወደ ውጪ የሚያሳይ ሌንስ  እና መጥሪያ ደውል የተገጠመላቸው ናቸው።

ውበታቸውን የሚያጎላ ራሱን የቻለ ሞስትራ (𝗙𝗿𝗮𝗺𝗲) አሏቸው።

በመረጡት "ዲዛይን" እና "ከለር

የምናስመጣቸውን 𝗯𝘂𝗶𝗹𝗱𝗶𝗻𝗴 𝗰𝗼𝗻𝘀𝘁𝗿𝘂𝗰𝘁𝗶𝗼𝗻 𝗺𝗮𝘁𝗲𝗿𝗶𝗮𝗹𝘀

ለበለጠ መረጃ 
  ስፈልጉ 0973329393
ይደውሉ።
288 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 14:03:05
የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ የአስክሬን ሽኝት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ የአስክሬን ሽኝት መርሐ ግብር ከመኖሪያ ቤቱ ጀምሮ እየተካሄደ ነው፡፡

ከአርቲስቱ መኖሪያ ቤት ጀምሮ እየተካሄደ ያለው የአስክሬን ሽኝት መርሐ ግብር÷ በመቀጠልም በወዳጅነት ፓርክ በመንግሥት ባለስልጣናት፣ በሙያ አጋሮቹ፣ በአድናቂዎቹ እና ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት የአስክሬን ስንብት ይካሄዳል።

የተወዳጁ አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ስርአት በመንበረ ጸባኦት ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።

ተወዳጁ የጥበብ ሰው ማዲንጎ አፈወርቅ ስለ ፍቅር፣ ትዝታ፣ ባህል፣ ሀገር፣ ታሪክና ሌሎች ጉዳዮችን የሚዳስሱ መልዕክቶችን በተስረቅራቂ ድምጹ በማዜም በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ስራ ላይ የራሱን አሻራ አሳርፏል።

ማዲንጎ አፈወርቅ ኢትዮጵያ በተፈተነችበት ወቅት እያመመው ግንባር ድረስ በመሄድና ማሰልጠኛም ምልምሎችን በማነቃቃት የራሱ የሆነ ታሪክ የሰራ አርቲስት መሆኑም ይታወቃል።

በቀድሞው የጎንደር ክፍለ ሀገር አዘዞ ተወልዶ በደብረታቦር ያደገው አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ መስከረም 17 ቀን 2015 ዓ.ም ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

@gasha_tube
578 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 09:08:47
የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም መጠናቀቁን ፖሊስ አስታወቀ

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይና በተለያዩ ቦታዎች የተከበረው የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም የሃይማኖት አባቶች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይና በተለያዩ ቦታዎች የተከበረው የደመራ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የፀጥታ አካሉ ዕቅድ በማውጣት በርካታ የሰው ኃይሉን በመከላከል ስራ ላይ ማሰማራቱን፤ ከበዓሉ አስተባባሪዎች ጋር በቅርበት በጋራ በመሰራቱ በአዲስ አበባ የተካሄደው የደመራ በዓል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ መከበሩን ፖሊስ ገልጿል፡፡
 
@gasha_tube
421 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 21:17:00 + ዘኬዎስ አጭር ባይሆን +

ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶስን ለማየት ተቸገረ:: ሕዝቡ ብዙ ነውና የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት:: የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው::

እሱ ዛፍ ላይ ጌታን ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም:: ጌታ ሊታዩ ከሚሞክሩ ይልቅ ሊያዩት የሚሹትን ይወዳልና ዘኬዎስን ጠራው::

ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጥጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኬዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ላይ እያየ ና ልማርህ አለው:: "ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል" አለው:: ጌታ ወደ ቤቱ ገባ:: ለዘኬዎስ ቤት መዳን ሆነለት::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋር እየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚያበቃ ትጋት አያሳይም ነበር:: ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሲጣላ ሊቆይ ይችል ነበር::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ከዛፍ ላይ አይወጣም ነበር:: 
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን የሠራዊት አምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር:: በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉሥ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው:: የዘኬዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር:: እግዚአብሔር የመዳኑን ቀን የቆረጠለት ቁመቱን ሲያሳንሰው ነበር:: በምድር በመጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኬዎስ አጭር በመሆኑ ነው::

ስለ ቁመት የማወራ እንዳይመስልህ:: እግዚአብሔር ለነፍሳችን መዳን የሚያሳጥርብን ብዙ ነገር አለ::
እንደ ዘኬዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥርህ ነገር ግን አይጠፋም::

ይሄ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም? እሱን ማለቴ ነው::
ይሄ ይጎድለኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር::
እጥረትህ መክበሪያህ ነው:: ጉድለትህም መዳኛህ ነው::

እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያትህ ይሁን:: በጉድለትህ እንደ ዘኬዎስ ከፍ በልበት:: ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም::
ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ::  በቤትህ መዳን ይሆንልሃል:: ከዚያም ስላጠረህ ስለጎደለህ ነገር ፈጣሪህን ስታመሰግነው ትኖራለህ::

እመነኝ አንዳንድ ጉድለቶች እድሎች ናቸው::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ይቀር ነበር::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
@gasha_tube
320 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 21:16:28
267 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 18:21:09
"ዝምታ ጸጥ ማለት ብቻ አይደለም፡፡"

    "ትልቁ ፍልሚያ ከራስ ጋር ነው፡፡"

ዝምታ ምንድነው? ሰው ለምን ዝምታን ይፈልጋል?
ሁላችንም ዝም ስንል በዝምታችን ውስጥ የቀበርናቸው ምክንያቶች የለም ወይ?
እርግጥ የዝምታ አንዱ መሠረት ጸጥታ ነው፡፡ጸጥ ማለት ደግሞ ከባድ ክህሎትን ያሻል፡፡  ጸጥታ ታላቅነት ነው ታላቅ ኃይላት ጸጥ ያሉ ናቸው፡፡
ተፈጥሮ ነገሮችን በጸጥታ ማከናወኑን ተክናበታለች፡አትክልቱ ፍራፍሬው ሰብል ጥራጥሬው እየጮኸ የሚያድግ ቢሆን ገበሬ ሰላም ባጣ መናፈሻችን ውስጥ ያሉት አበቦች ቢከራከሩ እንኳንስ ሊያዝናኑን ከሩቅ በሸሸናቸው ነበር፡፡የዝናብ ድምጽ እንቅልፍ የሚያመጣ ልዝብ ለዛ ባይኖረው እንደ አይሮፕላኖቻችን የሚያስገመግም ቢሆን ክረምታችን ምን ሊመስል ይችል ነበር? ወጀብና መብረቅን የሚያውቅ ሁሉ መልሱን ይረዳዋል፡፡

ግን እኛ የሰው ልጆችስ? እኛማ ጸጥታን የምንፈራ ፍጡሮች ነን!ምርቶቻችን በሙሉ ድምጽ እንዲያሰሙ ታስበው የሚፈበረኩ ይመስላሉ፡፡መኪናዎቻችን ያጓራሉ፣ ባቡሮቻችን ያሸከትፋሉ፣ ጥሩንባቸውን ያንቧርቃሉ ደውሎቻችን ያቃጭላሉ፣ ማሽኖቻችን ያፋጫሉ በእጃችን ውጤቶች ባልተናነሰ እኛም ድምጾችን እንፈጥራለን፡፡ ገና ወደዚህች ምድር ስንመጣ "እሪ..."ብለን ፍጥረትን እንበጠብጣለን ስናድግም ብዙ እናወራለን፣ በየገበያው በየአደባባዩ፣በየሚዲያው በየፓርላማው እንጨቃጨቃለን አንደማመጥም እናፏጫለን፣ እንጮሀለን፣እናለቅሳለን እናሽካካለን በእጆቻችን እናጨበጭባለን፣በኮቴዎቻችን እንረግጣለን፡፡(የሰው ልጆችን በሙሉ ከገጿ ላይ ቢነሱላት ምድር ጸጥ ያለች ወይዘሮ ትመስል ነበር፡፡ ንጽህናና ሰላሟን ያገኘች ባለ ክብ ፊት ወይዘሮ ለምለም-
ዐ : ለም፡፡)

በደንብ ወደውስጣችን እንድንመለከት ራስን ለማግኘት  የጥሞና ግዜ የሚያስገነዝብ ድንቅ መፅሀፍ እድታነቡት እጋብዛለው

ምንጭ ፦ አርምሞ መፅሀፍ
200 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 21:01:02
አዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች

ሰኞ መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የሚካሄደውን የደመራ የመለኮስ ስነ-ስርአት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፦

•  ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም  ከኤድናሞል በአትላሳ ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ  ኡራኤል አደባባይ

• ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ

• ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ  ለገሃር  ለሚመጡ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛ ላይ

• ከቡልጋሪያ በሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር የሚሄዱ ጠማማ ፎቅ አካባቢ

•  ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ እንዲሁም ከጦር ኃይሎች በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ለገሃር  የሚወስደው ሚክሲኮ አደባባይ

• ከተከለ ሃይማኖት በጎማ ቁጠባ  ወደ ለገሃር ሰንጋተራ 40/60 ኮንደሚኒዬም አካባቢ

• ከጌጃ ሰፈር ፣ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎማ ቁጠባ

• ከመርካቶ በተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሜትሮሎጂ በር ላይ

• ከራስ ቴአትር በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ

• ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ ሼል

• ከፒያሳ በቸርችር ጎዳና ለገሃር ቴዎድሮስ አደባባይ

• በአሮጌው ቄራ ፍል ውሃ ንግድ ማተሚያ ቤት

• ከካዛቺስ ወደ ሂልተን ካዛንቺስ ቶታል

• ከአዋሬ በካዛንቺስ ወደ ፍል ውሃ የሚወስደው መንገድ የቀድሞ 6ኛ ፖሊስ መታጠፊያ ላይ ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

ህብረተሰቡ ይህን አውቆ አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም መልዕክት አስተላልፏል።

በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም ክልክል ነው ተብሏል።

@gasha_tube
311 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 17:15:29
ሰው ፊቱን ባጠቆረብህ ቁጥር የምትበረግግ እና አድናቆት በቸረህ ቁጥር የምትፈነጥዝ አትሁን ። ካለዚያ የሰው ተለዋዋጭ ስሜት ባርያ ትሆናለህ።

አንተነትህ በሰው አስተያየት ላይ የተንጠለጠለ አይሁን ። ሰላም ስትለው ችላ ካለ ደግመህም በሌላ ቀነ ሰላም ስትለው ከተቆነነ ዝጋው! ፡፡
ሳቅ ለመፍጠር ብለህ እራስህን እያቃለልክ የባጥ የቆጡን እየቀባጠርክ ስብእና ላይ አትንደባለል ።
@gasha_tube
@gasha_tube

አትንጀውጀው ሰዎች በተሳሳተ መንገድ ተረዱኝ ብለህ አዛው በዛው ለማረም አትባክን ።

በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ ከተመሳሳይ ሰዎች ጋር በተለያየ ጊዜ እየተሟገትክ ጉንጭህን አታልፋ ።
ችርስ !
792 views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 11:42:58 #1 ኢጎ ነው ጠላቴ።

በአንድ ወቅት በሥዕል ችሎታው ወደር የሌለው የፈጠራ ሰው ይኖር ነበር።ከሥራው ፍፁማዊነት የተነሣ ከድንጋይ የአንድ ሰው ምስል ከቀረፀ፣ ሰው ይሁን ድንጋይ መለየት በጣም ያስቸግራል። ሥራዎቹ ሕይወትን የተሞሉ ሕያውነትን የተላበሱ ስለነበሩ እውነት መስለው ይታያሉ።
ታዲያ አንድ መሰግል(ጠንቋይ) ጊዜ ሞቱ የቀረበ መሆኑን ይነግረዋል እንደ ማንኛውም ሰው ይህ የፈጠራ ሰውም ሞቱን ይፈራ ስለነበረ ከመጣበት ሞት ማምለጥ ፈለገ። አስቦበትና አብሰልስሎበት ሲያበቃ አንድ መፍትሄ አገኘ። የራሱን ምስል ከድንጋይ እየቀረፀ አስራ አንዱን ካዘጋጀ በኋላ የተቆረጠለት ዕለት መልዓከ ሞት በሩን አንኳክቶ ሲገባ፣ ትንፋሹን ውጦ ከድንጋይ አምሳያዎቹ መሃል ገብቶ ተመሳስሎ ቆመ። መልአከ ሞቱ ግራ ገባው፣ ዐይኑን ማመን ተሣነው። እንዲህ አይነት ነገር ገጥሞኝ አያውቅም! ፈጣሪ ሁለት ፍፁም ተመሳሳይ ሰዎችን ፈጥሮ አያውቅም። የሚፈጥረው እየለያየ ነው። ፈጣሪ እንደ ጠርሙስ መፈብረኪያ ማሽን አይደለም። የአንድን ፍጡር አምሳያ ደግሞ አይፈጥርም። ታዲያ ምን አዲስ ነገር መጣ? አስራ ሁለት ተመሳሳይ ሰዎች? እሺ ማንን ይውሰድ? ከአንድ በላይ ይዞ መሄድ አይችልም... መልአከ ሞት መውሰድ አቃተው። ግራ ተጋብቶ፣ተጨንቆ በስጋት ተውጦ ተመልሶ ሄደ። ፈጣሪ አምላክ ዘንድ ሲደርስም " ምንድነው ያደረግኸው? እኔ ማምጣት የምችለው አንድ ሰው ብቻ ነው፣ ሄጄ ያገኘሁት ግን አስራ ሁለት አንድ አይነት ነው። እንዴት ነው መምረጥ ያለብኝ? ሲል ይጠይቃል። ፈጣሪ አምላክም ሳቀና መልአከ ሞትን ከጠራው በኋላ፣ ከሃሳውያን መካከል እውነተኛውን የማግኛውን ቁልፍ ቀመር በጆሮ ሹክ አለው። ይህን የሚስጢር ቃል ከሰጠው በኋላም፣ "አሁን ብቻ ያ የፈጠራ ሰው ራሱን በመሠሎቹ ድንጋዮች መሀል በደበቀበት ቤት ውስጥ ትገባና ይህንን የነገርኩህን የሚስጢር ቃል መናገር ብቻ ነው።" ይለዋል።
መልአከ-ሞትም "እንዴት ነው የሚሰራው? " ሲል ይጠይቀዋል። ፈጣሪም፣ " ስለ እርሱ አትጨነቅ አንተ ብቻ ሂድና የነገርኩህን አድርግ።" ብሎ ያሰናብተዋል።
መልአከ-ሞትም የተነገረው ውጤት ይኖረዋል ብሎ ባያምንም የፈጣሪን ቃል አክብሮ ይሄዳል። የፈጠራ ሰውዬው መኖሪያ ቤት ከገባ በኋላ ዙሪያውን ተመልክቶ ሲያበቃ እንዲህ አለ፣" ጌታዬ ሁሉ ነገር እንከን የለሽ ነው ። ግን አንድ ቅር የሚያሰኝ ነገር አለ። ጥሩ ሰርተሃል ግን አንድ ስህተት አለው።" ይላል፣ በደፈናው ለአስራ ሁለቱም እየተናገረ።
ይህን ጊዜ አርቲስቱ መደበቁን ከነአካቴው ዘንግቶት።
" ስህተት፣ የታለ ስህተት፣ የቱ ጋ?" እያለ ዘሎ ወጣ።
መልአከ-ሞት ከት ብሎ ሳቀ! "ተይዘሃል ብቸኛው ስህተትህ ይሄው ነው። ራስህን መርሳት አትችልም። በል ና ተከተለኝ።" አለው እላችኋለሁ።
... እውነተኛ የሕይወት አርቲስት ፍፁም የተሰወረ እና ከእኔነት የወጣ ነው።
ኢጎ ካልተወገደ በቀር 'ከእኔ-በቀራችን' ማን ሊያድነን ይችላል???
@gasha_tube
1.3K views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 11:42:40
1.0K views𝖊𝖙𝖍𝖎𝖔 𝖆𝖑𝖎𝖇𝖆𝖇𝖆 Тєαм, 08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ