Get Mystery Box with random crypto!

'ዝምታ ጸጥ ማለት ብቻ አይደለም፡፡'     'ትልቁ ፍልሚያ ከራስ ጋር ነው፡፡' ዝምታ ምንድነው | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

"ዝምታ ጸጥ ማለት ብቻ አይደለም፡፡"

    "ትልቁ ፍልሚያ ከራስ ጋር ነው፡፡"

ዝምታ ምንድነው? ሰው ለምን ዝምታን ይፈልጋል?
ሁላችንም ዝም ስንል በዝምታችን ውስጥ የቀበርናቸው ምክንያቶች የለም ወይ?
እርግጥ የዝምታ አንዱ መሠረት ጸጥታ ነው፡፡ጸጥ ማለት ደግሞ ከባድ ክህሎትን ያሻል፡፡  ጸጥታ ታላቅነት ነው ታላቅ ኃይላት ጸጥ ያሉ ናቸው፡፡
ተፈጥሮ ነገሮችን በጸጥታ ማከናወኑን ተክናበታለች፡አትክልቱ ፍራፍሬው ሰብል ጥራጥሬው እየጮኸ የሚያድግ ቢሆን ገበሬ ሰላም ባጣ መናፈሻችን ውስጥ ያሉት አበቦች ቢከራከሩ እንኳንስ ሊያዝናኑን ከሩቅ በሸሸናቸው ነበር፡፡የዝናብ ድምጽ እንቅልፍ የሚያመጣ ልዝብ ለዛ ባይኖረው እንደ አይሮፕላኖቻችን የሚያስገመግም ቢሆን ክረምታችን ምን ሊመስል ይችል ነበር? ወጀብና መብረቅን የሚያውቅ ሁሉ መልሱን ይረዳዋል፡፡

ግን እኛ የሰው ልጆችስ? እኛማ ጸጥታን የምንፈራ ፍጡሮች ነን!ምርቶቻችን በሙሉ ድምጽ እንዲያሰሙ ታስበው የሚፈበረኩ ይመስላሉ፡፡መኪናዎቻችን ያጓራሉ፣ ባቡሮቻችን ያሸከትፋሉ፣ ጥሩንባቸውን ያንቧርቃሉ ደውሎቻችን ያቃጭላሉ፣ ማሽኖቻችን ያፋጫሉ በእጃችን ውጤቶች ባልተናነሰ እኛም ድምጾችን እንፈጥራለን፡፡ ገና ወደዚህች ምድር ስንመጣ "እሪ..."ብለን ፍጥረትን እንበጠብጣለን ስናድግም ብዙ እናወራለን፣ በየገበያው በየአደባባዩ፣በየሚዲያው በየፓርላማው እንጨቃጨቃለን አንደማመጥም እናፏጫለን፣ እንጮሀለን፣እናለቅሳለን እናሽካካለን በእጆቻችን እናጨበጭባለን፣በኮቴዎቻችን እንረግጣለን፡፡(የሰው ልጆችን በሙሉ ከገጿ ላይ ቢነሱላት ምድር ጸጥ ያለች ወይዘሮ ትመስል ነበር፡፡ ንጽህናና ሰላሟን ያገኘች ባለ ክብ ፊት ወይዘሮ ለምለም-
ዐ : ለም፡፡)

በደንብ ወደውስጣችን እንድንመለከት ራስን ለማግኘት  የጥሞና ግዜ የሚያስገነዝብ ድንቅ መፅሀፍ እድታነቡት እጋብዛለው

ምንጭ ፦ አርምሞ መፅሀፍ