Get Mystery Box with random crypto!

#1 ኢጎ ነው ጠላቴ። በአንድ ወቅት በሥዕል ችሎታው ወደር የሌለው የፈጠራ ሰው ይኖር ነበር።ከሥራ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

#1 ኢጎ ነው ጠላቴ።

በአንድ ወቅት በሥዕል ችሎታው ወደር የሌለው የፈጠራ ሰው ይኖር ነበር።ከሥራው ፍፁማዊነት የተነሣ ከድንጋይ የአንድ ሰው ምስል ከቀረፀ፣ ሰው ይሁን ድንጋይ መለየት በጣም ያስቸግራል። ሥራዎቹ ሕይወትን የተሞሉ ሕያውነትን የተላበሱ ስለነበሩ እውነት መስለው ይታያሉ።
ታዲያ አንድ መሰግል(ጠንቋይ) ጊዜ ሞቱ የቀረበ መሆኑን ይነግረዋል እንደ ማንኛውም ሰው ይህ የፈጠራ ሰውም ሞቱን ይፈራ ስለነበረ ከመጣበት ሞት ማምለጥ ፈለገ። አስቦበትና አብሰልስሎበት ሲያበቃ አንድ መፍትሄ አገኘ። የራሱን ምስል ከድንጋይ እየቀረፀ አስራ አንዱን ካዘጋጀ በኋላ የተቆረጠለት ዕለት መልዓከ ሞት በሩን አንኳክቶ ሲገባ፣ ትንፋሹን ውጦ ከድንጋይ አምሳያዎቹ መሃል ገብቶ ተመሳስሎ ቆመ። መልአከ ሞቱ ግራ ገባው፣ ዐይኑን ማመን ተሣነው። እንዲህ አይነት ነገር ገጥሞኝ አያውቅም! ፈጣሪ ሁለት ፍፁም ተመሳሳይ ሰዎችን ፈጥሮ አያውቅም። የሚፈጥረው እየለያየ ነው። ፈጣሪ እንደ ጠርሙስ መፈብረኪያ ማሽን አይደለም። የአንድን ፍጡር አምሳያ ደግሞ አይፈጥርም። ታዲያ ምን አዲስ ነገር መጣ? አስራ ሁለት ተመሳሳይ ሰዎች? እሺ ማንን ይውሰድ? ከአንድ በላይ ይዞ መሄድ አይችልም... መልአከ ሞት መውሰድ አቃተው። ግራ ተጋብቶ፣ተጨንቆ በስጋት ተውጦ ተመልሶ ሄደ። ፈጣሪ አምላክ ዘንድ ሲደርስም " ምንድነው ያደረግኸው? እኔ ማምጣት የምችለው አንድ ሰው ብቻ ነው፣ ሄጄ ያገኘሁት ግን አስራ ሁለት አንድ አይነት ነው። እንዴት ነው መምረጥ ያለብኝ? ሲል ይጠይቃል። ፈጣሪ አምላክም ሳቀና መልአከ ሞትን ከጠራው በኋላ፣ ከሃሳውያን መካከል እውነተኛውን የማግኛውን ቁልፍ ቀመር በጆሮ ሹክ አለው። ይህን የሚስጢር ቃል ከሰጠው በኋላም፣ "አሁን ብቻ ያ የፈጠራ ሰው ራሱን በመሠሎቹ ድንጋዮች መሀል በደበቀበት ቤት ውስጥ ትገባና ይህንን የነገርኩህን የሚስጢር ቃል መናገር ብቻ ነው።" ይለዋል።
መልአከ-ሞትም "እንዴት ነው የሚሰራው? " ሲል ይጠይቀዋል። ፈጣሪም፣ " ስለ እርሱ አትጨነቅ አንተ ብቻ ሂድና የነገርኩህን አድርግ።" ብሎ ያሰናብተዋል።
መልአከ-ሞትም የተነገረው ውጤት ይኖረዋል ብሎ ባያምንም የፈጣሪን ቃል አክብሮ ይሄዳል። የፈጠራ ሰውዬው መኖሪያ ቤት ከገባ በኋላ ዙሪያውን ተመልክቶ ሲያበቃ እንዲህ አለ፣" ጌታዬ ሁሉ ነገር እንከን የለሽ ነው ። ግን አንድ ቅር የሚያሰኝ ነገር አለ። ጥሩ ሰርተሃል ግን አንድ ስህተት አለው።" ይላል፣ በደፈናው ለአስራ ሁለቱም እየተናገረ።
ይህን ጊዜ አርቲስቱ መደበቁን ከነአካቴው ዘንግቶት።
" ስህተት፣ የታለ ስህተት፣ የቱ ጋ?" እያለ ዘሎ ወጣ።
መልአከ-ሞት ከት ብሎ ሳቀ! "ተይዘሃል ብቸኛው ስህተትህ ይሄው ነው። ራስህን መርሳት አትችልም። በል ና ተከተለኝ።" አለው እላችኋለሁ።
... እውነተኛ የሕይወት አርቲስት ፍፁም የተሰወረ እና ከእኔነት የወጣ ነው።
ኢጎ ካልተወገደ በቀር 'ከእኔ-በቀራችን' ማን ሊያድነን ይችላል???
@gasha_tube