Get Mystery Box with random crypto!

የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም መጠናቀቁን ፖሊስ አስታወቀ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይና በተለ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም መጠናቀቁን ፖሊስ አስታወቀ

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይና በተለያዩ ቦታዎች የተከበረው የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም የሃይማኖት አባቶች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይና በተለያዩ ቦታዎች የተከበረው የደመራ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የፀጥታ አካሉ ዕቅድ በማውጣት በርካታ የሰው ኃይሉን በመከላከል ስራ ላይ ማሰማራቱን፤ ከበዓሉ አስተባባሪዎች ጋር በቅርበት በጋራ በመሰራቱ በአዲስ አበባ የተካሄደው የደመራ በዓል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ መከበሩን ፖሊስ ገልጿል፡፡
 
@gasha_tube