Get Mystery Box with random crypto!

#ጀርባ ከቤትሽ ግድግዳ ከሳሎንሽ መሀል መስታወት ተሰቅሏል ፥ ስትስቂ ሳቅሽን፣ስታነቢ እንባሽን | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

#ጀርባ

ከቤትሽ ግድግዳ ከሳሎንሽ መሀል
መስታወት ተሰቅሏል ፥
ስትስቂ ሳቅሽን፣ስታነቢ እንባሽን
ገልብጦ ያሳይሻል ፥
እንዲህ ነው መስታወት የብርጭቆ ግብሩ ፥
ሲከፋሽ የከፋው ፣ስትሰክሪ ሰካራም
የዛሬ አንቺነትሽ ነፀብራቅ ማኖሩ ።

ስለዚህ የኔ ውድ .....!!
ከተሰባሪ እቃ ብርጭቆ ፊት ቆመሽ
<እኔ ማን ነኝ !?> እያልሽ እንዳት ጠይቂ..
መጀመሪያ ውዴ....
የዛሬ አንቺነትሽን ፣ ከነገው ምኞትሽ ፣
........ ከትላንት አስታርቂ ፤


በትዝታ ማዕበል የኋሊት ሂጂና
ከህይወት ፊት ቆመሽ ጀርባሽን እወቂ ።
........//......
ዳኙ

https://t.me/gasha_tube