Get Mystery Box with random crypto!

ሜዲቴሽን ወይንም በጥልቅ ማሰላሰል ወይም ተመስጦ ሰፊ ፍልስፍና ነው። ዝምብሎ እግርን አጣምሮ፣ አይ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

ሜዲቴሽን ወይንም በጥልቅ ማሰላሰል ወይም ተመስጦ ሰፊ ፍልስፍና ነው። ዝምብሎ እግርን አጣምሮ፣ አይንን ከድኖ፣ ትንፋሽን መቆጣጠር አይደለም። ሜዲቴሽን ከሃሳብ እስር፣ ከጭንቅላት አለም ወጥቶ ህልውናን እንዳለ ማስተዋል ነው። ሜዲቴሽን ከሃሳብ ግርግር ማረፍ ነው። ሜዲቴሽን ከእንቅልፍ ወደ ንቃት አለም መሸጋገሪያ ነው። ከማሰብ ወደ መሆን ከፍ ማያ ነው።

ሜዲቴሽንን በቀላሉ የምታስረዳ አንድ ምሳሌ አለች። የኩሬ ውሃ ጭቃ ሞልቶት ቢደፈርስ እየነካካን አናጠራውም። በነካካነው ቁጥር ይበልጥ እየደፈረሰ ነው የሚመጣው። መፍትሔው ኩሬውን አለመንካት ነው፤ መፍትሔው ኩሬው ዳር ተቀምጦ የተፈጥሮን ትንግርት ማስተዋል ነው። ኩሬው ለራሱ ሲተው እየጠራ፣ እየጠራ ይመጣና ኩልል ያለ ንፁህ፣ የተጣራ ውሃ ይሆናል።

አእምሯችን እንደ ተንጣለለው ኩሬ በሃሳብ ጭቃ ደፍርሷል። ኩሬውን እየነካካን እንደማናጠራው ሁሉ አእምሮንም በሃሳብ ጉልበት መግራት አይቻልም። ኩሬው ራሱ በራሱ እንዲጠራ እንደምንተወው ሁሉ፣ አእምሮም ንቃት ላይ እንዲደርስ፣ ከሃሳብ ግርግር አሳርፎ ለራሱ ምትሃታዊ አርምሞ መተው አለበት። በጥልቅ አሰላሳዩም ተፈጥሮ በአእምሮ ላይ የራሱን ተአምር ሲሰራ በዝምታ ተውጦ ያስተውላል። በጥልቅ ማሰላሰል ሌላ ምንም ውስብስብ ነገር የለውም። በአጭሩ ከሃሳብ ነፃ ሆኖ ወደ መሆን ማእቀፍ መሸጋገር ነው። Meditation is a state of thoughtlessness. It's a state of being. It's a state of consciousness.
@gasha_tube
@gasha_tube