Get Mystery Box with random crypto!

ለመታረቅ የመጀመሪያ ሁን ብዙዎቻችን በአንድ ወቅት በተፈጠሩ አለመግባባቶች ወይም በደረሰብን በደል | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

ለመታረቅ የመጀመሪያ ሁን

ብዙዎቻችን በአንድ ወቅት በተፈጠሩ አለመግባባቶች ወይም በደረሰብን በደል ምክንያት ለረጅም ጊዜ እናቄማለን። የምታረቀው ያስቀየመን ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል እራሱ መጥቶ ይቅርታ ከጠየቀን ብቻ ነው ብለን ድርቅ እንላለን።

አንዴ ጤንነቷ ጥሩ ያልሆነ የማውቃት ሴት ከወንድ ልጇ ጋር ለሰባት አመታት እንደማይነጋገሩ ነገረችኝ። " ለምን ?" ብዬ ጠየኳት። ከልጇ ጋር በሚስቱ ምክንያት አለመግባባት እንደነበረና እሱ ካልደወለ ላለመደወል እንደወሰነች ነገረችኝ። አንቺ የመጀመሪያው ብትሆኚስ ?" ብዬ ጠቆም ሳደርጋት " አይሆንም " እሱ ነው ይቅርታ መጠየቅ ያለበት !" አለችኝ። እሷ ከምትደውል ሣታገኘው ብትሞትም ምንም እንደማይመስላት ነገረችኝ። ከተወሰነ የማበረታቻ ንግግር በኋላ ሀሣቧን ለውጣ እሷ የመጀመሪያዋ ለመሆን ተስማማች። ስትደውልለት ልጁ በመደወሏ በጣም እንደተደሰተ ነገረችኝ። ቀጥሎም ለጥፋቱ ይቅርታ ጠየቃት። ይቅርታውን ስላልጠበቀች እጅግ ተገረመች።

በአብዛኛው አንዱ ደፍሮ የመጀመሪያውን እርምጃ ሲራመድ ሌለኛውም የበለጠ ይቀርብና ሁሉም አሸናፊ ይሆናል። ቂም ይዘን ስንቆይ በአእምሯችን ውስጥ ቀላሉን ነገር ወደ ከባድ እና ውስብስብ እንለውጠዋለን። አቋማችን ከደስታችን በላይ አስፈላጊ ይመስለናል። አይደለም !

ሰላማዊ ሰው መሆን የምትፈልግ ከሆነ ትክክል መሆን ደስተኛ ከመሆን እንደማይበልጥ እየተረዳህ ትመጣለህ። ደስተኛ ለመሆን ያለፈውን መርሣትና ለመታረቅ የመጀመሪያ መሆን ትልቅ ሚና አለው። አንተ የመጀመሪያው መሆንህ ስህተት መሆንህን አያሳይም። ነገር ግን ሁኔታዎችን ወደ መልካም ይለውጣል።

ያለፈውን ስትተው ሰላምህ ፣ ለመታረቅ የመጀመሪያው ስትሆን ደግሞ ሰዎችም ለስለስ ብለው ይቀርቡሃል። እንዲያውም የበለጠ ሊቀርቡህና ስትፈልጋቸው የበለጠ ሊደርሱልህ ይችላሉ። ግን በሆነ ምክንያት እንደዚያ ባያደርጉም ችግር የለውም። ቢያንስ ቢያንስ የድርሻህን ስለተወጣህ ውስጣዊ እርካታ ይሰማሃል። በእርግጠኝነት ደግሞ ራስህን ሰላማዊ ሁነህ ታገኘዋለህ።
____
ምንጭ
፦ ቀላሉን ነገር አታካብድ መጽሐፍ
ጸሐፊ ፦ ዶክተር ሪቻርድ ካርሰን
ተርጓሚ ፦ ዶክተር ዮናስ ላቀው
@gasha_tube
@gasha_tube