Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopia 24

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopia_24 — Ethiopia 24 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopia_24 — Ethiopia 24
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopia_24
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.87K
የሰርጥ መግለጫ

2015/ 2023 አስተያየት መስጫ @Ethnewbot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-10-04 09:41:08
ስልክ ይዞ የተገኘ ተማሪ ስልኩ አይቀማም በቀጥታ ከፈተናው ይወገዳል ፤ ፈተና አይፈተንም ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

- ሶሻል እና ናቹራል ላይ ላሉ ተመሳሳይ የትምህርት ዓይነቶች የተለያዩ ፈተናዎች ተዘጋጅተዋል

- ተማሪዎች ከግቢ በምንም ዓይነት ምክንያት መውጣት አይችሉም

- በስህተት እንኳን ስልክ ይዞ የተገኘ ተማሪ ከፈተናው ይወገዳል ፤ ከግቢውም እንዲርቅ ይደረጋል

- ተማሪዎቹ አንዴ ካምፓስ ውስጥ ከገቡ በኋላ ከሌላው ዓለም ጋር ግኑኝነት አይኖራቸውም

- ግቢ ከገቡ በኋላ ፈተናው ቢወጣ እንኳን ተማሪዎች ሊጠቀሙ የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል

- ተፈታኞች በግቢ ቆይታቸው እናበላቸዋለን፣እናጠጣቸዋለን፣እንከባከባቸዋለን፣... ከሌላው ዓለም ግን ግንኙነት የላቸውም

- የአንድ አካባቢ ተወላጅ አካባቢው ላይ ያሉ ተማሪዎችን አይፈትንም

- ማንኛውም የአንድ ዩንቨርሲቲ አስተማሪ የሚያስተምርበት ዩንቨርሲቲ ውስጥ አይፈትንም

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
2.1K views06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 09:37:11
#ደባርቅ_ዩኒቨርሲቲ
ከላይ በተዘረዘሩ የትምህርት መስኮች ለመምህርነት የወጣ የቅጥር ማስታወቂያ

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
1.9K views06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 13:57:39
#ትምህርት_ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ፦ በተለያዩ አካባቢዎች #ከሰላም እና #ፀጥታ ጋር ተያይዞ #መፈተን_የማይችሉ እና ከሀገር የወጡ የኮሚኒቲ ተማሪዎች በአጠቃላይ 56,000 ተማሪዎች ሲሆኑ በቀጣይ #ሁለተኛ ዙር ፈተና ይዘጋጅላቸዋል ።

- አሁን ለፈተና ለማይቀመጡ 56 ሺህ ተማሪዎች በአንድ ወር ውስጥ ለፈተናው እንዲቀመጡ ይደረጋል።

- ከመስከረም 30 ጀምሮ የሚሰጠው ብሄራዊ ፈተና ዝግጅት እና ህትመት በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።

- ተማሪዎችን ወደ ተመደቡባቸው አካባቢዎች የሚያደርሷቸው የክልል የፀጥታ አካላት ሲሆኑ በዩኒቨርሲቲዎች የጥበቃና ፍተሻ ስራን የሚሰሩት #የፌዴራል_ፖሊስ አባላት ናቸው። (ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ - የትምህርት ሚኒስትር , WMCC/ኢብኮ)

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
488 viewsedited  10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 13:37:56
#የ12ኛ_ክፍል_ብሔራዊ_ፈተና

የተፈታኝ ተማሪዎች ግዴታዎች

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
639 views10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 17:39:29 በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የኦንላይን ትምህርት ሊሰጥ ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የኦንላይን ትምህርት ለመስጠት የዕውቅና ፍቃድ ጥያቄን ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶች ማድረጉ ተገለጸ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመነጋገር ኢ-ለርኒንግን ለማስፋፋት ፕሮጀክት ቀርጾ የ22 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማግኘቱንና በአሜሪካው አሪዞና ዩኒቨርሲቲ አማካይነት መርሃ ግብሩን ዕውን ለማድረግ ሥራዎች መጀመራቸው ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በርቀት የትምህርት መደብ የተወሰኑ ትምህርቶችን ቢሰጡም በመደበኛነት የኦንላይን ትምህርት ለመስጠት የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ፈቃድ የሰጠው የትምህርት ተቋም የለም።

ትምህርት ሚኒስቴር በተያዘው ዓመት አምስት ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ትምህርት ለመስጠት ፈቃድ እንዲያገኙ ለማድረግ ማቀዱን የገለጸ ሲሆን ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ በደረጃ የኦንላይን ትምህርት እንዲሰጡ መታቀዱ ተገልጿል፡፡

የኦንላይን/E-Learning ትምህርቱ ዋነኛ ትኩረቶች፦

• ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች የሚጠቀሙበት የትምህርት አማራጭ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ማቅረብ።

• ሁሉም መምህራን በኦንላይን የመማር ማስተማር የትምህርት ዘዴ ተጨማሪ ስልጠና ይወስዳሉ።

• የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኦንላይን ለመማር የሚችሉበት ሰልጠና ይሰጣቸዋል፡፡

የኦንላይን ትምህርትን ለማስፋፋት የትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን ከዚህ ቀደም ባወጣው መመርያ ፈቃድ የወሰዱ ውስን የግል ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡

የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋት ዩኒቨርሲቲዎች ቴክኖሎጂን ተጠቅመው የኦንላይንን ትምህርትን ለማጠናከር የመሠረተ ልማቶችንና ፋሲሊቲዎችን የማሟላት ሥራዎች መጀመራቸው ተገልጿል። ( ሪፖርተር )

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
377 views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 17:26:13 በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለምትወስዱ ተማሪዎች ከዚቀደም የወጡ እንግሊዝኛ ጥያቄዎች

English EUEE QUESTIONS

VOCABULARY


518 views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 06:40:45
ትምህርት ሚኒስቴር #በደብረ_ማርቆስ_ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ፣ ጤና ሳይንስ ግቢና ቡሬ ግቢ / ካምፓስ #የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንዲወስዱ የተመደቡ ወረዳዎችና ትምህርት ቤቶች ዝርዝር ከላይ ይመልከቱ፡፡

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
2.2K views03:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 14:53:56
#የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና #የጊዜ_ሰሌዳ እንደሚከተለው ቀርቧል።

➤ የመጀመሪያ ዙር (የሶሻል ሳይንስ) ፦

ከመስከረም 26 - 28 (ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ)

መስከረም 29 (ኦረንቴሽን ይሰጣል)

ከመስከረም 30 - ጥቅምት 2 (ፈተና ይሰጣል)

ከጥቅምት 3 - ጥቅምት 4 (ተፈታኞች ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ)

➤ ሁለተኛ ዙር (የተፈጥሮ ሳይንስ) ፦

ከጥቅምት 5 - ጥቅምት 6 (ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ)

ጥቅምት 7 (ኦረንቴሽን ይሰጣል)

ከጥቅምት 8 - ጥቅምት 11 (ፈተና ይሰጣል)

ከጥቅምት 12 - ጥቅምት 13 (ተፈታኞች ወደየአከባቢያቸው ይመለሳሉ)

(ትምህርት ሚኒስቴር / የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት)

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
3.7K views11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 11:33:44
#ማስታወቂያ

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተመድባችሁ ለምትፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ

2014/15 የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ ማሟላት ያለባችሁ ነገሮች በትምርት ሚኒስቴር

*መያዝ የተፈቀዱ**

# አንሶላ፣ትራስ ጨርቅ፣
#የማታ ልብስ፣
#ደረቅ ምግብ፣
#ልብስ፣ቦርሳ፣
#የመፈተኛ ካርድ፣
#እርሳስ፣ላጲስ፣የማስታወሻ ደብተር፣
#ባዶ ወረቀት እና መጽሐፍ መያዝ ትችላላችሁ።

*መያዝ  የተከለከሉ**

#ማንኛውም ድምፅ እና ቪዲዮ የሚቀዳ/ፎቶግራፍ የሚያነሳ መሳሪያ፤ካሜራ

#ማንኛውም ከቴሌ መስመርም ይሁን ከቴሌ ውጭ መልዕክት በድጂታል ቴክኖሎጂ መቀበያ ወይም ማስተላለፊያ ውጤቶች(ታብሌት፣ኮሚፕዩተር፣ላብቶፕ፣ ስልክ፣አይፓድ፥ሃርድ ዲስክ፣ፍላሽ እና ሌሎችንም) ባለመያዝ

ዝግጅቱን አጠናቆ ወደሚጠብወቃችሁ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከመስከረም 26/1/2015 ጀምሮ ወደ ዩኒቨርስቲው በሰላም እንድትመጡ ያሳስባል፡፡

በመሆኑም  ከመስከረም 26/1/2015 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 11 /2/2015 ድረስ የሚሰጠውን የ2014/15 የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የሰላም አምባሳደር በሆነው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ  በመረጋጋት እና በትኩረት በመስራት ጥሩ ውጤት እንድታመጡ ዩኒቨርሲቲው ይመኛል፡፡ (ሠመራ ዩኒቨርሲቲ)

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
4.8K views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 08:39:39
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት በዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ተቋማቱን ለቀው እንዲወጡ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

ይሁን እንጂ ጦርነትና የፀጥታ ችግር ካለባቸው የትግራይ፣ አማራ እና ኦሮሚያ አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች ወደ ቤተሰብ ለመሄድ እንደማይችሉ እና ውጪ ለመቆየት አቅም እንደሌላቸው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ገልጿል።

ፈተናው እስከሚጠናቀቅ ተማሪዎቹ የሚቀመጡበት ቦታ እንዲመቻችላቸው ህብረቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረቡን የህብረቱ ፕሬዝዳንት ሚካኤል ያቦነሽ ተናግረዋል።

ህብረቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ተማሪዎቹ ብሔራዊ አደጋና ስጋት ኮሚሽን ማዕከላት እንዲቆዩ ጥያቄ ቢያቀርቡም ኮሚሽኑ እንደማይችል ገልጿል።

በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲዎች የቴሌቪዥን ማሳያ ክፍሎችና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ተማሪዎቹ የሚቆዩበት መመሪያ እንዲሰጥ ህብረቱ ጠይቋል።

ተማሪዎቹ ለፈተና አሰጣጡ ስጋት እንዳይሆኑ ፈተናው በሚሰጥበት ወቅት ከማደሪያቸው እንዳይወጡና ምግብም ከተፈታኞቹ በኋላ እንዲመገቡ በማድረግ ችግር እንዳይፈጠር ህብረቱ እንደሚሰራ ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17/2015 ዓ.ም በሁሉም የዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምንም አይነት መደበኛ ተማሪ እንዳይገኝ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል። ( tikvah )

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
4.4K views05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ