Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት በዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ተቋማቱን ለቀው እን | Ethiopia 24

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት በዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ተቋማቱን ለቀው እንዲወጡ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

ይሁን እንጂ ጦርነትና የፀጥታ ችግር ካለባቸው የትግራይ፣ አማራ እና ኦሮሚያ አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች ወደ ቤተሰብ ለመሄድ እንደማይችሉ እና ውጪ ለመቆየት አቅም እንደሌላቸው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ገልጿል።

ፈተናው እስከሚጠናቀቅ ተማሪዎቹ የሚቀመጡበት ቦታ እንዲመቻችላቸው ህብረቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረቡን የህብረቱ ፕሬዝዳንት ሚካኤል ያቦነሽ ተናግረዋል።

ህብረቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ተማሪዎቹ ብሔራዊ አደጋና ስጋት ኮሚሽን ማዕከላት እንዲቆዩ ጥያቄ ቢያቀርቡም ኮሚሽኑ እንደማይችል ገልጿል።

በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲዎች የቴሌቪዥን ማሳያ ክፍሎችና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ተማሪዎቹ የሚቆዩበት መመሪያ እንዲሰጥ ህብረቱ ጠይቋል።

ተማሪዎቹ ለፈተና አሰጣጡ ስጋት እንዳይሆኑ ፈተናው በሚሰጥበት ወቅት ከማደሪያቸው እንዳይወጡና ምግብም ከተፈታኞቹ በኋላ እንዲመገቡ በማድረግ ችግር እንዳይፈጠር ህብረቱ እንደሚሰራ ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17/2015 ዓ.ም በሁሉም የዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምንም አይነት መደበኛ ተማሪ እንዳይገኝ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል። ( tikvah )

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24