Get Mystery Box with random crypto!

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ ማለዳ ጋዜጣ በሰራው ዘገባ ላይ በመጀመሪያ ዙር ባደረገው ማጣራት መረጃው | Ethiopia 24

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ ማለዳ ጋዜጣ በሰራው ዘገባ ላይ በመጀመሪያ ዙር ባደረገው ማጣራት መረጃው ሀሰት ሆኖ እንዳገኘው ገልጿል።

ጋዜጣው ባለፈው ቅዳሜ ያወጣው ዘገባን የማጣራት ሥራ የሚያከናውን ኮሚቴ በማዋቀር የማጣራት ሥራ መጀመሩን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ኮሚቴው ያገኘውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ የማጣራት ሥራውን ከ2014 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ተመራቂዎች መጀመሩን ገልጿል።

በዚህም ከዩኒቨርሲቲው SIMS የመረጃ ቋት ላይ
የሁሉንም የ2014 ዓ.ም ተመራቂዎች መረጃ በማውረድ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ካጸደቀው የተመራቂዎች ዝርዝር ቃለ-ጉባኤ ጋር የማነጻጸር ሥራ ሰርቷል፡፡

የጋዜጣው ም/ዋ/አዘጋጅ ሊዲያ ተስፋዬ መስከረም 18/2015 ዓ.ም ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፋሪስ ደሊል (ዶ/ር) በስልክ በሰጡት መረጃ ‹‹የ2014 ዓ.ም  በማኔጅመንት የትምህርት ክፍል የተመረቁትን አጣሩ›› ማለታቸው ተነስቷል።

ይሁን እንጂ በ2014 ዓ.ም በመደበኛው መርሃ ግብር በማኔጅመንት ፕሮግራም የተመረቁ ተመራቂዎች አለመኖራቸውን ኮሚቴው አረጋግጧል፡፡

አዲስ ማለዳ ያወጣው ዘገባ እውነት ስለመሆኑ ምንም ፍንጭ አልመገኘቱን ዩኒቨርሲቲው ጠቁሟል።

"በ2014 የትምህርት ዘመን የተመረቁ ተማሪዎችን በተመለከተ ኮሚቴው ባደረገው ማጣራት አንድም የተፋለሰ መረጃ አልተገኘም" ሲል ዩኒቨርሲቲው አረጋግጧል፡፡

የ2014 ተመራቂዎች መረጃ በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ www.wku.edu.et ላይ የሚገኝ መሆኑን የገለጸው ዩኒቨርሲቲው፤ ያለፉ ዓመታትን የማጣራት ሂደት የሚቀጥል መሆኑን ገልጿል፡፡

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

@ethiopia_24     @ethiopia_24