Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስተር

የቴሌግራም ቻናል አርማ neaea_nea — ትምህርት ሚኒስተር
የቴሌግራም ቻናል አርማ neaea_nea — ትምህርት ሚኒስተር
የሰርጥ አድራሻ: @neaea_nea
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.71K
የሰርጥ መግለጫ

We are working to help all ethiopians

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-01-30 00:35:26 ምን ያህል ተማሪዎች በማጠናከሪያ ፕሮግራም ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ?

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 896,520 ተማሪዎች መካከል 29,909 ተማሪዎች ብቻ በቀጥታ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚገቡ የትምህርት ሚኒስቴር መግለጹ ይታወቃል።

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላስመዘገቡና የተሻለ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች መካከል 100 ሺህ የሚሆኑት ተማሪዎች በደከሙባቸው የትምህርት አይነቶች በልዩ ክትትል እንዲማሩ ከተደረገ በኋላ ድጋሜ እንዲፈተኑ በማድረግ ሁለተኛ ዙር ዕድል እንደሚሰጣቸው የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ይህም እንደ ዩኒቨርሲቲዎቹ የመቀበለ አቅምና የተማሪዎቹን ውጤት መሠረት አድርጎ በሚፈጸም የምልመላ መስፈርት የሚከናወን ነው።

ውጤት ያላመጡ ተማሪዎቹ በደከሙባቸው የትምህርት ዓይነቶች የማጠናከሪያ ድጋፍ ተደርጎላቸው በድጋሜ ፈተና እንዲወስዱ ተደርጎ የሚያልፉ ብቻ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ይደረጋል፡፡

በፈተናው ወቅት ለሴቶች እና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ለሚገኙ ተማሪዎች የመግቢያ ነጥብ ላይ እገዛ ይደረግላቸዋል ተብሏል፡፡ 

@NEAEA_nea
16.5K views21:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 20:31:53 #Update

በ2014 የትምህርት ዘመን 899 ሺህ 520 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናውን ወስደዋል።

ከነዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ ውጤት ያመጡት 29 ሺህ 909 ወይም 3 ነጥብ 3 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አሰራር ለመከተል ማቀዱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ከግማሽ በላይ ያመጡት 30 ሺህ ገደማዎቹ ተማሪዎች በሚቀጥለው ዓመት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብተው የአንደኛ ዓመት ተማሪ ይሆናሉ ብለዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም መሰረት በማድረግ የተሻለ ውጤት ያመጡት ተመርጠው ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ እንደሚደረግ አስረድተዋል።

ይሁንና እነዚህ ተማሪዎች በቀጥታ የዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንደማይሆኑ ጠቁመዋል። ተማሪዎቹ “የደከሙባቸው ትምህርቶችን” ለአንድ ዓመት በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተማሩ ከቆዩ በኋላ በዓመቱ መጨረሻ ፈተና ወስደው ካለፉ በዩኒቨርሲቲዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪ ሆነው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል። #EI

@NEAEA_nea
17.7K views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 16:24:39
መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል :- ትምህርት ሚኒስቴር

መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚገኙ  ተማሪዎች በአንድ ጊዜ እንደሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ገልጸዋል ።

መሪ ስራ አስፈጻሚው ኤባ ሚጀና ( ዶ/ር )  በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ አውደጥናት ላይ  እንደገለጹት  መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ  ወር ለሁሉም  ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች  በአንድ ጊዜ  ይሰጣል።

የመጀመሪያው ፈተና በሰኔ  ወር ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ  የመውጫ ፈተና  ከ6 ወራት  በኋላ  እንደሚሰጥም  ዶክተር ኤባ  አስረድተዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱም ሆኑ ተፈታኝ  ተማሪዎች ፈተናው በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉም አቶ ሰይድ አሳስበዋል።

በመውጫ ፈተና ብቃትና የፈተና ኮርሶች ልየታና የተገቢነት ማረጋገጥ ዙሪያ በተዘጋጀው አውደጥናት ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር
@NEAEA_NEA
32.8K views13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-18 21:19:58 የመውጫ ፈተና/Exit Exam

መንግስት በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ጠንካራ ትግበራ እና ርምጃዎችን ለመውሰድ ከያዛቸው የሪፎርም አጀንዳዎች መካከል የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ዋነኛው ነው።

በህግ እና በህክምና ሙያ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና እና የብቃት ማረጋገጫ ፍተሻ እንደ ልምድ በመውሰድ መንግስት በሌሎች የትምህርት መስኮችም የመውጫ ፈተና እንዲሰጥ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ትምህርት ሚኒስቴር የመንግስትን አቅጣጫ በመከተል በ2015 ዓ.ም በመንግስት እና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በየሙያውና ትምህርት ዘርፍ ተዘጋጅቶ ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ትግበራ ፖሊሲ እና ዝርዝር ማስፈፀሚያ መመሪያ በማዘጋጀት ወደ ሥራም ገብቷል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለመውጫ ፈተና ትግበራ የተዘጋጀውን የአፈፃፀም መመሪያ በማጸደቅም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አሰራጭቷል።

ለመሆኑ መመሪያው ምን ይላል?

➤ የመውጫ ፈተናው የመጀመሪያ ዲግሪ የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ይመለከታል።

➤ መመሪያው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ከሚከወኑ የማስፈፀሚያ ስልቶች አንዱ ነው።

➤ የመውጫ ፈተናውን ወስዶ 50 በመቶ ውጤት ማምጣት ያልቻለ ተማሪ መመረቅም ሆነ ከተማረበት ዩኒቨርሲቲ የዲግሪ ሰርተፊኬት ማግኘት አይችልም።

➤ በመውጫ ፈተና 50 በመቶ ማምጣት ያልቻለ ተጨማሪ ጊዜ ወስዶ በአግባቡ አጥንቶ ፈተናውን 50 በመቶ እና ከዛ በላይ አምጥቶ ማለፍ እንዲችል ለሁለት ተጨማሪ ጊዜ የመፈተን እድል ይሰጠዋል። ተፈታኙ እድሉን መጠቀም ያለበት የመጀመሪያውን ፈተና ከወሰደ በሦሥት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው።

➤ አንድ ተማሪ ለምርቃት ብቁ የሚሆነው የመውጫ ፈተናውን ካለፈ ብቻ ሲሆን ሦሥት ጊዜ ተፈትኖ የማለፊያ ነጥብ ያላገኘ ተፈታኝ ከብሔራዊ የብቃት ማዕቀፍ ተገቢው ማስረጃ ይሰጠዋል።

➤ የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና እንደየትምህርት ፕሮግራሙ ባህሪ በዓመት ሁለቴ እና ከዛም በላይ ሊሰጥ ይችላል።

➤ የመውጫ ፈተና የሙያ ማህበራት ተጠናክረው የሙያ ፍቃድ ፈተና መስጠት እስከሚጀምሩ በትምህርት ሚኒስቴር ወይም ውክልና በሚሰጠው ተቋም ይዘጋጃል።

➤ መውጫ ፈተና ላይ የሚካተቱ ኮርሶችን በተመለከተ በየትምህርት መስኩ በሚዘጋጁ የማስፈፀሚያ ዝርዝር መመሪያዎች ይለያል።

➭ የመውጫ ምዘና ጠቀሜታዎች፦

➤ ተመራቂ ተማሪ በቂ ዝግጅት እንዲያደርግና በራሱ እንዲተማመን ያስችላል።

➤ ተማሪ በዩኒቨርሲቲ ቆይታው ጠንክሮ እንዲሰራ፤ ብቁ ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲወጣ ያስችላል።

➤ ተቋማት ተማሪዎቻቸውን በጥሩ ውጤት ለማለፍና ያላቸውን ተፈላጊነት ለማስፋት በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲሰሩ ያደርጋል።

➤ መምህራን ተማሪዎቻቸውን ብቃት ተላብሰው እንዲመረቁ ለማስቻል በኃላፊነት ተከታታይ ምዘና በማካሄድ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ክፍተቶች እንዲሞሉ ያደርጋል።

➤ ቀጣሪ ድርጅቶች/ኢንዱስትሪው በተማሪው ብቃት ላይ አመኔታ እንዲኖረው ያደርጋል።

➤ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፥ የምሩቃንን ክህሎትና እውቀት ለመፈተሽ እና የሥራ ገበያንም ለማሳደግ ያግዛል።

➤  የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አቅምና ጥራትን ለማሻሻል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው።

➤ ተማሪዎች በሰለጠኑባቸውና በተማሩባቸው ሙያዎች ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ያስችላል።


@NEAEA_nea
32.2K views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 19:35:13
#Update

ዛሬ በተጠናቀቀው የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንዳልወሰዱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ለፈተናው ከተመዘገቡ 595 ሺህ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ውስጥ 586 ሺህ 541 ተፈታኞች ፈተናውን
እንደወሰዱ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር)
ተናግረዋል።

በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህር ዳር እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች "ከትምህርት ስርዓቱ ባፈነገጠ ሁኔታ አንፈተንም በማለት" 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጸዋል።

በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በደረሰ "ኃይል የተቀላቀለ ግርግር" የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ በፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት መድረሱንም አመልክተዋል።

ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ሚኒስቴሩ ምንም አይነት እድል እንደማይሰጥ አሳውቋል።

@NEAEA_nea
29.7K viewsedited  16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 19:35:13
ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሦሥት ቀናት ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ መሆኑን ዩኒቨርሲቲዎች እያሳወቁ ነው።

ተማሪዎቹ በተዘጋጀላቸው ትራንስፖርት ወደየመጡበት እየተሸኙ መሆኑም ተመላክቷል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ በሚገኘው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና፤ በመጀመሪያው ዙር ከ586 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።

የመጀመሪያው ዙር ፈተና በመላ ሀገሪቱ በ130 የፈተና ማዕከላት ተሰጥቷል፡፡

@NEAEA_nea
24.7K views16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 22:30:38
#DebreTaborUniversity

በዛሬው ጠዋት የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ወቅት በተፈጠረ ችግር የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ተስተጓጉሎ እንደነበረ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።

በተወሰኑ "ካልተኮራረጅን አንፈተንም፣ የፈተና አሰጣጥ ሥርዓቱን አናከብርም፤ አንፈተንም!" ባሉ "ሥነ-ምግባር በጎደላቸው ተማሪዎች" ምክንያት የፈተና አሰጣጡ ተስተጓጉሎ እንደነበር ተቋሙ አሰጋግጧል።

"ለመበጥበጥ የሞከሩ አካላትን" ዩኒቨርሲቲው ከደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር፣ ከደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደርና ከሌሎች አካላት ጋር ባደረገው ጥረት ግቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጉን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በተፈጠረው ችግር በተማሪዎች፣ በፈታኝ መምህራንና በፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት መድረሱን ዶይቼ ቬሌ አንድ የዓይን እማኝን ጠቅሶ ዘግቧል።

ፈተና መፈትን የማይፈልጉ ግቢውን እንዲለቅቁ መጠየቁን ተከትሎ ፈቃደኛ ተማሪዎች በሰላማዊ መንገድ እየተፈተኑ እንደሆነ፤ ፈቃደኛ ያልሆኑት ደግሞ ግቢውን ለቅቀው መውጣታቸውን እማኙ ተናግረዋል።

"ፈተናው በሌሎች የፈተና ጣቢያዎች ተሰርቋል፤ ስለዚህ አንፈተንም" ያሉ ተማሪዎች ጠዋት ላይ ግቢውን ለቀው መውጣቸውን አሁን ላይ ከስፍራው እየተሰሙ ያሉ መረጃዎች ያሳያሉ።

በተማሪዎች እና በፀጥታ አካላት መካከል በተከሰተ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉንም ሐኪሞችን በመጥቀስ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ህይወቱን ስላለፈው ተማሪ ያለው ነገር የለም።

የተማሪ ቤተሰቦች እንዲረጋጉ የጠየቀው ዩኒቨርሲቲው፤ በአሁኑ ሰዓት ተማሪዎች መልካም በሆነ የተረጋጋ መንፈስ እየተፈተኑ እንደሚገኙ ጠቁሟል።

"ኃላፊነት የጎደለው አሉባልታ በማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨት ላይ የሚገኙ አካላት ከድርጊታች እንዲታቀቡ" ተቋሙ አሳስቧል።

@NEAEA_nea
19.0K viewsedited  19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 22:30:38
#DebreMarkosUniversity

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል ብዙዎቹ በራሳቸው ፈቃድ ፈተናውን ጥለው መውጣታቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ይትባረክ አወቀ ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ እንደተናገሩት ከምሥራቅ ጎጃም አንዳንድ ወረዳዎች የመጡ ተማሪዎች "ለተፈታኝ ተማሪ የማይመጥን መፈክር በማሰማት በጠዋት የመፈተኛ ግቢያቸውን ጥለው ወጥተዋል።"

ተማሪዎቹ ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ የተለያዩ አካላት ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካም ብለዋል።

"ተማሪዎቹ ባልተጨበጠ ወሬና በመንደር ፖለቲካ ተጠልፈዋል" ያሉት አቶ ይትባረክ፤ ግቢውን ጥለው ከወጡት ተማሪዎች ውጪ ሌሎች ተረጋግተው እንደተፈተኑ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ እንደተደበደቡና እንደተዋከቡ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ እንደሆነም ገልጸዋል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ በበኩላቸው ተፈታኝ ተማሪዎች "ጥለው ወጡ" የተባለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ተናግረዋል።

ፈተናውን አቋርጠው የወጡት በዩኒቨርሲቲው ጤና ካምፓስ የሚፈተኑ እና "ፈተናው የከበዳቸዉ ጥቂት ተማሪዎች" የቲክቫህ ቤተሰቦይ ከተቋሙ ያደረሱን መረጃ ያሳያል።

ፈተና ጥለዉ ከወጡ ተማሪዎች መካከል አብዛኛዎቹ በ2013 ዓ.ም የጨረሱና ዳግም ፈተና የተፈቀደላቸው መሆናቸው ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ላይ ብጥብጥ እንዳለ ተማሪ እንደቆሰለ፣ እንደተደበደቡ ተደርጎ የሚሰራጨዉ መረጃ ሐሰት መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

@NEAEA_nea
14.7K viewsedited  19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 20:04:49
ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የመጀመሪያ ቀን ውሎ ተጠናቋል።

ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች በ130 ማዕከላት ብሔራዊ ፈተናውን እየወሰዱ ሲሆን በ128ቱ ማዕከላት በሰላም ተሰጥቷል፡፡

ፈተናው እየተሰጠባቸው ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል በሁለት የመፈተኛ ማዕከላት ችግር ማጋጠሙ ተገልጿል።

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ በምስራቅ ጎጃም እናርጅ እናውጋ ወረዳ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት "አንፈተንም" በማለት ለቀው መውጣቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ረፋዱን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

የተማሪዎቹ ምክንያት በአግባቡ ተጣርቶ የሚወሰደው እርምጃ ይገለጻል ብለዋል።

በሌላ በኩል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ የሚገኝ ድልድይ ተደርምሶ በተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል።

በአደጋው ጉዳት ያጋጠማቸው ተማሪዎች ህክምና የተደረገላቸው ሲሆን ተማሪዎቹ ካገገሙ በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ እንደሚደረግ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በድልድዩ መደርመስ አደጋ የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን የሲዳማ ክልል ሠላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ተናግረዋል።

በአደጋው 310 ተማሪዎች ቀላልና 110 ተማሪዎች ላይ መካከለኛና ከባድ ጉዳት ደርሷል። 20 ተማሪዎች የአጥንት ስብራት እንዳጋጠማቸው ኃላፊው አስረድተዋል።

ቢሮው ተማሪዎች ተረጋግተው ወደ ግቢው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ፈተናውን አስመልክቶ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን መመሪያ እንዲከታተሉ አሳስቧል።

@NEAEA_nea
13.6K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 15:20:16 የትምህርት ሚኒስቴር የብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ ፦

(ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ - የትምህርት ሚኒስትር)

- የፈተና ንክኪው በእጅጉ ተቀንሷል።

- ከዚህ በፊት በፈተና አሰጣጥ ወቅት የነበረውን " የኔ አካባቢ ሰው ፣ የኔ ዘመድ " የሚለውን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ማንኛውም የአንድ አካባቢ ተወላጅ እዛው አካባቢ ያሉ ተማሪዎችን አይፈትንም። ማንኛውም የአንድ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ እራሱ የሚያስተምርበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አይፈትንም።

- ተማሪዎች አንዴ ዩኒቨርሲቲ (ካምፓስ) ከገቡ በኃላ ከሌለው የውጪ ማህበረሰብ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አይኖራቸውም። ምንም ስልክ ወይም ሌላ የግንኙነት ነገር ይዘው አይገቡም።

- ተፈታኝ ተማሪዎች ለ4 ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ እናበላቸዋለን ፣ እናጠጣቸዋል፣  እንከባከባቸዋለን ነገር ግን በፍፁም ከሌላው ዓለም ጋር አይገናኙንም።

- ተማሪዎች ከሚነሱበት ቦታ የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው እንዳይሄዱ የክልል የፀጥታ ኃላፊዎች የፍተሻ ስራ ይሰራሉ፤ የክልል የፀጥታ አከላት ስራ ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲ በር ላይ እስኪደርሱ ብቻ ነው ከዛ በኃላ ያለውን የፍተሻ እና ጥበቃ ስራ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ይሆናሉ።

- ስልክ ይዞ አንድ ተማሪ ቢገኝ ስልክ ይቀማል ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ፈተናውን እንዳይወስድ ይደረጋል።

- ተማሪዎች በምንም ሁኔታ ፈተና ከሚወስዱበት ግቢያቸው ውጭ መውጣት አይችሉም፤ ከማንም ጋር መገናኘት አይችሉም።

- ከፍተኛ ዝግጅት እያደረግን ስለቆየን ችግር ይኖራል ብለን አናምንም።

- በእስር ላይ ላሉ፣ በውጭ ላሉ የኮሚኒቲ ት/ቤቶች ፣ በፀጥታ ምክንያት ፈተናውን ለመውሰድ ለማይችሉ ሌላ ሁለተኛ ፈተና ተዘጋጅቶላቸዋል። በአንድ ወር ውስጥ ይሰጣቸዋል።

የተፈጥሮ እና ሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች በተለያየ ጊዜ መፈተናቸውን ተከትሎ ተመሳሳይ የሆኑ ትምህርቶች እንዴት ይሰጣሉ ?

በትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ላይ እንደተገለፀው የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት እና ኩረጃን ለመከላከል በ2ቱ ዙር ተፈታኞች መካከል ምንም አይነት ግኝኑነት አይኖርም።

የመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች ፈተናቸውን ጨርሰው ከወጡ ከቀናት በኃላ ነው ሁለተኛው ዙር ተፈታኞች የሚፈተኑት።

ሁለቱም የሚወስዷቸው (የናቹራል እና ሶሻል) አንድ አይነት ትምህርቶች ላይ ጥንቃቄ ተደርጎ የተለያዩ ፈተናዎች ናቸው የተዘጋጁት።

ተማሪዎች ስልክ ይዘው ባለመሄዳቸው ከወላጆቻቸው ጋር እንዴት ይገናኛሉ ?

ትምህርት ሚኒስቴር ኩረጃን እና ስርቆት ለመከላከል ሲባል ተማሪዎች ወደ ሚፈተኑበት ተቋም ስልክ ይዘው መግባት እንደማይችሉ አሳውቋል።

ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ፈታኞችም የፈተና ክፍሎች አቅራቢያ እና ፈተናው የሚሰጥበት አካባቢ ስልክ ይዘው መገኘት አይችሉም።

በየዩኒቨርሲቲዎቹ አንድ አንድ ተወካይ የሚኖር ሲሆን በተወካዩ አማካኝነት ወላጆች ልጆቻቸውን ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ ይችላሉ።

የህትመት ዝግጅቱ ምን ይመስላል ? የፈተናው ኮዶች ስንት ናቸው ?

በአጠቃላይ የህትመት ዝግጅቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ጥንቃቄ የተደረገበት ሲሆን የፈተናው ኮዶች በፊት ከነበረው " 4 ኮድ " ወደ " 12 ኮድ " ከፍ ተደርጓል።

ለወላጆች የተላለፈ መልዕክት ፦

ወላጆች ተማሪዎች ይዘው መሄድ የሌለባቸው ፣ እና ስለሚጠበቅባቸው ግዴታቸው አስገንዝበው መላክ አለባቸው።

@NEAEA_nea
15.5K views12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ