Get Mystery Box with random crypto!

#Update በ2014 የትምህርት ዘመን 899 ሺህ 520 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናው | ትምህርት ሚኒስተር

#Update

በ2014 የትምህርት ዘመን 899 ሺህ 520 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናውን ወስደዋል።

ከነዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ ውጤት ያመጡት 29 ሺህ 909 ወይም 3 ነጥብ 3 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አሰራር ለመከተል ማቀዱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ከግማሽ በላይ ያመጡት 30 ሺህ ገደማዎቹ ተማሪዎች በሚቀጥለው ዓመት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብተው የአንደኛ ዓመት ተማሪ ይሆናሉ ብለዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም መሰረት በማድረግ የተሻለ ውጤት ያመጡት ተመርጠው ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ እንደሚደረግ አስረድተዋል።

ይሁንና እነዚህ ተማሪዎች በቀጥታ የዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንደማይሆኑ ጠቁመዋል። ተማሪዎቹ “የደከሙባቸው ትምህርቶችን” ለአንድ ዓመት በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተማሩ ከቆዩ በኋላ በዓመቱ መጨረሻ ፈተና ወስደው ካለፉ በዩኒቨርሲቲዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪ ሆነው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል። #EI

@NEAEA_nea