Get Mystery Box with random crypto!

ምን ያህል ተማሪዎች በማጠናከሪያ ፕሮግራም ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ? በ2014 የትምህርት ዘመን የ | ትምህርት ሚኒስተር

ምን ያህል ተማሪዎች በማጠናከሪያ ፕሮግራም ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ?

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 896,520 ተማሪዎች መካከል 29,909 ተማሪዎች ብቻ በቀጥታ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚገቡ የትምህርት ሚኒስቴር መግለጹ ይታወቃል።

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላስመዘገቡና የተሻለ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች መካከል 100 ሺህ የሚሆኑት ተማሪዎች በደከሙባቸው የትምህርት አይነቶች በልዩ ክትትል እንዲማሩ ከተደረገ በኋላ ድጋሜ እንዲፈተኑ በማድረግ ሁለተኛ ዙር ዕድል እንደሚሰጣቸው የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ይህም እንደ ዩኒቨርሲቲዎቹ የመቀበለ አቅምና የተማሪዎቹን ውጤት መሠረት አድርጎ በሚፈጸም የምልመላ መስፈርት የሚከናወን ነው።

ውጤት ያላመጡ ተማሪዎቹ በደከሙባቸው የትምህርት ዓይነቶች የማጠናከሪያ ድጋፍ ተደርጎላቸው በድጋሜ ፈተና እንዲወስዱ ተደርጎ የሚያልፉ ብቻ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ይደረጋል፡፡

በፈተናው ወቅት ለሴቶች እና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ለሚገኙ ተማሪዎች የመግቢያ ነጥብ ላይ እገዛ ይደረግላቸዋል ተብሏል፡፡ 

@NEAEA_nea