Get Mystery Box with random crypto!

#Update ዛሬ በተጠናቀቀው የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ12 ሺህ በላይ ተማ | ትምህርት ሚኒስተር

#Update

ዛሬ በተጠናቀቀው የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንዳልወሰዱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ለፈተናው ከተመዘገቡ 595 ሺህ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ውስጥ 586 ሺህ 541 ተፈታኞች ፈተናውን
እንደወሰዱ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር)
ተናግረዋል።

በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህር ዳር እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች "ከትምህርት ስርዓቱ ባፈነገጠ ሁኔታ አንፈተንም በማለት" 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጸዋል።

በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በደረሰ "ኃይል የተቀላቀለ ግርግር" የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ በፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት መድረሱንም አመልክተዋል።

ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ሚኒስቴሩ ምንም አይነት እድል እንደማይሰጥ አሳውቋል።

@NEAEA_nea