Get Mystery Box with random crypto!

ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሦሥት ቀናት ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው | ትምህርት ሚኒስተር

ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሦሥት ቀናት ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ መሆኑን ዩኒቨርሲቲዎች እያሳወቁ ነው።

ተማሪዎቹ በተዘጋጀላቸው ትራንስፖርት ወደየመጡበት እየተሸኙ መሆኑም ተመላክቷል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ በሚገኘው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና፤ በመጀመሪያው ዙር ከ586 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።

የመጀመሪያው ዙር ፈተና በመላ ሀገሪቱ በ130 የፈተና ማዕከላት ተሰጥቷል፡፡

@NEAEA_nea