Get Mystery Box with random crypto!

#DebreTaborUniversity በዛሬው ጠዋት የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ወቅት በተፈጠረ ችግ | ትምህርት ሚኒስተር

#DebreTaborUniversity

በዛሬው ጠዋት የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ወቅት በተፈጠረ ችግር የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ተስተጓጉሎ እንደነበረ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።

በተወሰኑ "ካልተኮራረጅን አንፈተንም፣ የፈተና አሰጣጥ ሥርዓቱን አናከብርም፤ አንፈተንም!" ባሉ "ሥነ-ምግባር በጎደላቸው ተማሪዎች" ምክንያት የፈተና አሰጣጡ ተስተጓጉሎ እንደነበር ተቋሙ አሰጋግጧል።

"ለመበጥበጥ የሞከሩ አካላትን" ዩኒቨርሲቲው ከደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር፣ ከደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደርና ከሌሎች አካላት ጋር ባደረገው ጥረት ግቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጉን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በተፈጠረው ችግር በተማሪዎች፣ በፈታኝ መምህራንና በፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት መድረሱን ዶይቼ ቬሌ አንድ የዓይን እማኝን ጠቅሶ ዘግቧል።

ፈተና መፈትን የማይፈልጉ ግቢውን እንዲለቅቁ መጠየቁን ተከትሎ ፈቃደኛ ተማሪዎች በሰላማዊ መንገድ እየተፈተኑ እንደሆነ፤ ፈቃደኛ ያልሆኑት ደግሞ ግቢውን ለቅቀው መውጣታቸውን እማኙ ተናግረዋል።

"ፈተናው በሌሎች የፈተና ጣቢያዎች ተሰርቋል፤ ስለዚህ አንፈተንም" ያሉ ተማሪዎች ጠዋት ላይ ግቢውን ለቀው መውጣቸውን አሁን ላይ ከስፍራው እየተሰሙ ያሉ መረጃዎች ያሳያሉ።

በተማሪዎች እና በፀጥታ አካላት መካከል በተከሰተ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉንም ሐኪሞችን በመጥቀስ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ህይወቱን ስላለፈው ተማሪ ያለው ነገር የለም።

የተማሪ ቤተሰቦች እንዲረጋጉ የጠየቀው ዩኒቨርሲቲው፤ በአሁኑ ሰዓት ተማሪዎች መልካም በሆነ የተረጋጋ መንፈስ እየተፈተኑ እንደሚገኙ ጠቁሟል።

"ኃላፊነት የጎደለው አሉባልታ በማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨት ላይ የሚገኙ አካላት ከድርጊታች እንዲታቀቡ" ተቋሙ አሳስቧል።

@NEAEA_nea