Get Mystery Box with random crypto!

#DebreMarkosUniversity በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ከ | ትምህርት ሚኒስተር

#DebreMarkosUniversity

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል ብዙዎቹ በራሳቸው ፈቃድ ፈተናውን ጥለው መውጣታቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ይትባረክ አወቀ ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ እንደተናገሩት ከምሥራቅ ጎጃም አንዳንድ ወረዳዎች የመጡ ተማሪዎች "ለተፈታኝ ተማሪ የማይመጥን መፈክር በማሰማት በጠዋት የመፈተኛ ግቢያቸውን ጥለው ወጥተዋል።"

ተማሪዎቹ ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ የተለያዩ አካላት ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካም ብለዋል።

"ተማሪዎቹ ባልተጨበጠ ወሬና በመንደር ፖለቲካ ተጠልፈዋል" ያሉት አቶ ይትባረክ፤ ግቢውን ጥለው ከወጡት ተማሪዎች ውጪ ሌሎች ተረጋግተው እንደተፈተኑ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ እንደተደበደቡና እንደተዋከቡ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ እንደሆነም ገልጸዋል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ በበኩላቸው ተፈታኝ ተማሪዎች "ጥለው ወጡ" የተባለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ተናግረዋል።

ፈተናውን አቋርጠው የወጡት በዩኒቨርሲቲው ጤና ካምፓስ የሚፈተኑ እና "ፈተናው የከበዳቸዉ ጥቂት ተማሪዎች" የቲክቫህ ቤተሰቦይ ከተቋሙ ያደረሱን መረጃ ያሳያል።

ፈተና ጥለዉ ከወጡ ተማሪዎች መካከል አብዛኛዎቹ በ2013 ዓ.ም የጨረሱና ዳግም ፈተና የተፈቀደላቸው መሆናቸው ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ላይ ብጥብጥ እንዳለ ተማሪ እንደቆሰለ፣ እንደተደበደቡ ተደርጎ የሚሰራጨዉ መረጃ ሐሰት መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

@NEAEA_nea