Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስቴር የብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ ፦ (ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ - የትምህርት ሚኒስት | ትምህርት ሚኒስተር

የትምህርት ሚኒስቴር የብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ ፦

(ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ - የትምህርት ሚኒስትር)

- የፈተና ንክኪው በእጅጉ ተቀንሷል።

- ከዚህ በፊት በፈተና አሰጣጥ ወቅት የነበረውን " የኔ አካባቢ ሰው ፣ የኔ ዘመድ " የሚለውን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ማንኛውም የአንድ አካባቢ ተወላጅ እዛው አካባቢ ያሉ ተማሪዎችን አይፈትንም። ማንኛውም የአንድ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ እራሱ የሚያስተምርበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አይፈትንም።

- ተማሪዎች አንዴ ዩኒቨርሲቲ (ካምፓስ) ከገቡ በኃላ ከሌለው የውጪ ማህበረሰብ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አይኖራቸውም። ምንም ስልክ ወይም ሌላ የግንኙነት ነገር ይዘው አይገቡም።

- ተፈታኝ ተማሪዎች ለ4 ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ እናበላቸዋለን ፣ እናጠጣቸዋል፣  እንከባከባቸዋለን ነገር ግን በፍፁም ከሌላው ዓለም ጋር አይገናኙንም።

- ተማሪዎች ከሚነሱበት ቦታ የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው እንዳይሄዱ የክልል የፀጥታ ኃላፊዎች የፍተሻ ስራ ይሰራሉ፤ የክልል የፀጥታ አከላት ስራ ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲ በር ላይ እስኪደርሱ ብቻ ነው ከዛ በኃላ ያለውን የፍተሻ እና ጥበቃ ስራ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ይሆናሉ።

- ስልክ ይዞ አንድ ተማሪ ቢገኝ ስልክ ይቀማል ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ፈተናውን እንዳይወስድ ይደረጋል።

- ተማሪዎች በምንም ሁኔታ ፈተና ከሚወስዱበት ግቢያቸው ውጭ መውጣት አይችሉም፤ ከማንም ጋር መገናኘት አይችሉም።

- ከፍተኛ ዝግጅት እያደረግን ስለቆየን ችግር ይኖራል ብለን አናምንም።

- በእስር ላይ ላሉ፣ በውጭ ላሉ የኮሚኒቲ ት/ቤቶች ፣ በፀጥታ ምክንያት ፈተናውን ለመውሰድ ለማይችሉ ሌላ ሁለተኛ ፈተና ተዘጋጅቶላቸዋል። በአንድ ወር ውስጥ ይሰጣቸዋል።

የተፈጥሮ እና ሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች በተለያየ ጊዜ መፈተናቸውን ተከትሎ ተመሳሳይ የሆኑ ትምህርቶች እንዴት ይሰጣሉ ?

በትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ላይ እንደተገለፀው የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት እና ኩረጃን ለመከላከል በ2ቱ ዙር ተፈታኞች መካከል ምንም አይነት ግኝኑነት አይኖርም።

የመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች ፈተናቸውን ጨርሰው ከወጡ ከቀናት በኃላ ነው ሁለተኛው ዙር ተፈታኞች የሚፈተኑት።

ሁለቱም የሚወስዷቸው (የናቹራል እና ሶሻል) አንድ አይነት ትምህርቶች ላይ ጥንቃቄ ተደርጎ የተለያዩ ፈተናዎች ናቸው የተዘጋጁት።

ተማሪዎች ስልክ ይዘው ባለመሄዳቸው ከወላጆቻቸው ጋር እንዴት ይገናኛሉ ?

ትምህርት ሚኒስቴር ኩረጃን እና ስርቆት ለመከላከል ሲባል ተማሪዎች ወደ ሚፈተኑበት ተቋም ስልክ ይዘው መግባት እንደማይችሉ አሳውቋል።

ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ፈታኞችም የፈተና ክፍሎች አቅራቢያ እና ፈተናው የሚሰጥበት አካባቢ ስልክ ይዘው መገኘት አይችሉም።

በየዩኒቨርሲቲዎቹ አንድ አንድ ተወካይ የሚኖር ሲሆን በተወካዩ አማካኝነት ወላጆች ልጆቻቸውን ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ ይችላሉ።

የህትመት ዝግጅቱ ምን ይመስላል ? የፈተናው ኮዶች ስንት ናቸው ?

በአጠቃላይ የህትመት ዝግጅቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ጥንቃቄ የተደረገበት ሲሆን የፈተናው ኮዶች በፊት ከነበረው " 4 ኮድ " ወደ " 12 ኮድ " ከፍ ተደርጓል።

ለወላጆች የተላለፈ መልዕክት ፦

ወላጆች ተማሪዎች ይዘው መሄድ የሌለባቸው ፣ እና ስለሚጠበቅባቸው ግዴታቸው አስገንዝበው መላክ አለባቸው።

@NEAEA_nea