Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopia 24

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopia_24 — Ethiopia 24 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopia_24 — Ethiopia 24
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopia_24
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.87K
የሰርጥ መግለጫ

2015/ 2023 አስተያየት መስጫ @Ethnewbot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-09-24 19:43:43
" የምንሄድበት የለም፤ መፍትሄ ይፈለግልን " - ተማሪዎች

የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መሰጠቱን ተከትሎ ፈተና የሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ማንኛውም ተማሪ እንዳይገኝ ተብሏል።

ይህ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኙ የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎችን ጭንቀት ውስጥ የከተተ ሲሆን ተማሪዎቹ መፍትሄ ይፈለግላቸው ዘንድ ጠይቀዋል።

አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባልና ቤተሰቦቹ በሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ፤ "ወደ መጡበት ቦታ መመለስ የማይችሉ ተማሪዎች ምን ሊደረጉ ነው ? ጦርነት ካለበት ቦታ የመጣን ተማሪዎች አለን ድምፃችን ተሰምቶ መፍትሄ ይፈለግልን፤ ወደ ቤታችን መሄድ አንችልም፤ መሄጃም የለንም" ብሏል።

ሌሎችም ተማሪዎች በተመሳሳይ መሄጃቸው እንደጨነቃቸው ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በአንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብቻ 50 የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች መኖራቸው ለማወቅ የቻለ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለእነዚህ መሄጃ ለጠፋቸው ተማሪዎች ምን አሰቧል በሚል ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር የቅርብ ሰው ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

እኚሁ ሰው ዩኒቨርሲቲው ለትምርህት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቦ ከግቢ ይውጡ እንደተባለና ምናልባት ከፈተና መለስ እንደሚመለሱ አስረድተዋል።

መሄጃ የሌላቸው ተማሪዎች እስከዛ የት እንዲያርፉ ታስቧል ለሚለው ጥያቄ፤ ከግቢ ወጥተው ወደየ መጡበት/ቤተሰብ ጋር ይሂዱ መባሉን ገልፀዋል። በዚህ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አቅጣጫ ቢያስቀምጡ ጥሩ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ት/ት ሚኒስቴር ሚሰጠን ምላሽ ካለ እናሳውቃለ። ( ቲክቫህ )

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

@ethiopia_24     @ethiopia_24
1.3K views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 19:29:39
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ለኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር የላከው ደብዳቤ

ጉጂ፣ምዕራብ ሸዋ፣ምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ ዞናች ላይ ከሚገኙ የተወሰኑ ወረዳዎች 56,169 ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ የሚችሉበት መንገድ እስኪሻሻል ድረስ ፈተናው በሌላ ዙር ይሰጥ ዘንድ ትምህርት ቢሮው በደብዳቤ ጠይቋል።


ደብዳቤው

የ2014 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲሰጥ በተወሰነው መሠረት ተማሪዎችን ድልድል ስናደርግ የመንገድ፣የትራንስፖርት እና የዩኒቨርሲቲዎች በመቀበል አቅም ችግር ምክንያት ካሉን አጠቃላይ #393,98 ተማሪዎች መካከል 56,69 ተማሪዎች ማለትም 14.26% ፈተና መወሰድ #ስለማይችሉ የመንገድ፣የትራንስፖርት እና የዩኒቨርሲቲዎች የመቀበል ሁኔታ እስኪሻሻል ድረስ ፈተና በሌላ ዙር እንዲሰጥልን እየጠየቅን አጠቃላይ መረጃ ሁለት ገጽ ከዚህ ደብዳቤ ጋር አያይዘን የላከን መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡   ( ATC )


ዝርዝር መረጃውን ከፎቶው ይመልከቱ

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
1.2K views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 19:21:27

አዲስ ማለዳ መስከረም 14/2015  ዓ.ም በቅጽ4 በቁጥር 203 እትሙ ላይ  ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲን አስመልክቶ ላወጣው ፅሁፍ የተሰጠ ምላሽ!

አዲስ ማለዳ በዛሬው ዕትሙ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲን አስመለክቶ ያወጣውን ዘገባ መነሻ በማድረግ የሚዲያውን ከፍተኛ የማኔጅመንት አካል የሆኑትን አቶ ሚካኤልን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል በስልክ አነጋግረው የጋዜጣውን አዘጋጅ አድራሻ የተቀበሉ ሲሆን ዋና አዘጋጁን አቶ ቢኒያም በተደጋጋሚ ለተደረገላቸው የስልክ ጥሪ ሙከራ ምላሽ ሊሰጡ ያልቻሉ ሲሆን በአንጻሩ በSMS  በላኩት የጽሁፍ መልዕክት “አሁን ማነጋገር ስለማልችል ስጨርስ እደውላለሁ“ የሚል ምላሽ ከመስጠት ውጭ እስካሁን ድረስ ተጨማሪ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

በሌላ በኩል የፅሁፉ አቅራቢ የሆነው አቶ ኢዮብ ትኩዬ ለመጀመሪያ የስልክ ጥሪ ምላሽ የሰጠ ሲሆን በምላሹም ግለሰቡ የዩኒቨርሲቲው ናቸው ያላቸው ሁለት የስልክ ቁጥሮች ላይ ለመደወል እንደሞከረ ቢገልጽም ቁጥሮቹን ለመናገር ፈቃደኛ አይደለም፡፡ለተጨማሪ ማብራሪ ድጋሚ ቢደወልለትም ስልክ ለማንሳትም ሆነ በSMS  ምላሽ አልሰጠም፡፡

በመሆነም ይህንን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲው የሚከተሉትን እርምጃዎች ወስዷል፡-

1ኛ. የዩኒቨርሲቲው ዋና ሬጅስትራርና የኮሌጅ ሬጅስትራር ቢሮዎች  ተገቢው የማጣራት ስራ እስኪሰራ ድረስ ሙሉ በሙሉ በሙሉ እንዲታሸጉና ተገቢው ጥብቅ የሆነ ጥበቃ እንዲደረግላቸው  ተደርጓል፡፡

2ኛ .የተማሪዎች የመረጃ ቋት የሆነው SIMS (Students’ Information Management System ) ተገቢው ማጣራት እስኪደረግ ድረስ እንዲዘጋ ተደርጓል፡፡

ስለሆነም ባልተረጋገጠ መረጃ ማህበረሰቡን ማደናገር እንዲሁም  ሚዛናዊ ያልሆነ መረጃ ካልታወቀ ምንጭ ይዞ ማቅረብ የተቋሙን ስምና ዝና ከማጉደፉም በተጨማሪ ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጀምሮ እስከ ሬጅስትራር ሀላፊ ድረስ መረጃውን ለማጣራት ምንም ዓይነት ጥረት ሳይደረግ የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የትውልድ ማፍሪያ የሆነውን አንድ ተቋም በዘፈቀደ ስም ማጥፋት ተገቢነት እንደሌለው ለመላው ህዝባችን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

ስለሆነም በቀጣይ በምናደርገው ዝርዝር የማጣራት ስራ የቀረበው መረጃ እውነት ሆኖ ካገኘነው በድርጊቱ ተዋናዮች ላይ ተገቢውን አስተዳደራዊና ህጋዊ ርምጃ የምንወስድ ሲሆን በአንጻሩ ግን የሀሰት ውንጀላ ሆኖ ካገኘነው  ዩኒቨርሲቲው አግባብነት ያለውን ህግ ተከትሎ ጉዳዩን ለህግ የሚያቀርብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ እስካሁን ባለው ሂደት ዩኒቨርሲቲው ለተመራቂ ተማሪዎች ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃ  (Temporary Degree) ብቻ እየሰጠ መሆኑን እና ኦሪጅናል ዲግሪ በተመለከተ ከብርሀንና ሰላም ማተሚያ ቤት ጋር  ውል ፈፅሞ በማሳተም ሂደት ላይ መሆኑን እየገለጽን የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ  ኦሪጂናል ዲግሪ ማስረጃ አለኝ  ብሎ የሚያቀርብ ግለሰብ ካለ የትምህርት ማስጃው ሕገወጥ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

     የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
1.2K views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 19:21:10
1.1K views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 16:48:15
#ወራቤ_ዩኒቨርሲቲ በተያዘው ወር መጨረሻ መሰጠት ለሚጀምረው #የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዝግጅቱን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ከ8 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

ተቋሙ የተመደቡለትን ተማሪዎች ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት መሀመድ አወል (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የመፈተኛ ክፍሎች፣ የተፈታኞች ማደሪያ ዝግጅት፣ የምግብ ግብዓት አቅርቦት ማሟላት እና ሌሎች ዝግጅቶች መደረጋቸውን ም/ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
1.8K views13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 14:03:01
#መደ_ወላቡ_ዩኒቨርሲቲ #የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስፈተን ቅድመ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ከ15 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

ፈተናውን ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የተቋሙ የአካዳሚክ ጉዳዮቸ ም/ፕሬዝዳንት በዛብህ ወንድሙ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ብሔራዊ ፈተናው በዩኒቨርሲቲው የሻሻመኔ፣ ሮቤ እና ጎባ ካምፓሶች የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

ተማሪዎቹን ተቀብሎ ለማስተናገድ የመፈተኛ ክፍሎች፣ የማደሪያና የመመገቢያ አገልግሎቶች ዝግጅት እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አህመድ ከሊል (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ ለፈተና ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲሄዱ በቆይታቸው የሚጠቀሙበትን ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ጨርቅ መያዝ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
2.2K views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 13:13:41
#ዲላ_ዩኒቨርሲቲ በወሩ መጨረሻ መሰጠት ለሚጀምረው #የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዝግጅቱን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን 19 ሺህ 639 ተማሪዎችን ተቀብሎ ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል።

በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት የሚመራ ዋና ግብረ ኃይል እና በም/ፕሬዝዳንቶች የሚመራ ንዑስ ግብረ ኃይል ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችሉ ሥራዎችን እያከናወኑ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ፍቃዱ ወ/ማርያም (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች አስፈላጊ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን ከመፈተኛ ክፍሎች ጋር በተገናኘ ያጋጠሙ የወንበር እጥረቶችን የማሟላት ሥራ ከሌሎች ተቋማት ጋር በመነጋገር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው 490 ፈታኞችን መልምሎ ዝርዝራቸውን ለትምህርት ሚኒስቴር መላኩን ጠቁመዋል።

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
2.2K viewsedited  10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 08:12:38
#Werabe_University ለማታ እና የሳምንት መጨረሻ የ1ኛ ዲግሪ ተማሪዎች በሙሉ፡

ምዝገባ በኦንላይን የሚፈጸም መሆኑን ስለማሳወቅ (Oline registration)
የማታና የሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር የ1ኛ ዲግሪ የ2011 ባች ተማሪዎች (#ለ5ኛ ዓመት 1ኛ ሰሚስቱር) የ2012 ባች ተማሪዎች (#ለ3ኛ ዓመት 2ኛ ሰሚስተር) የ2013 ባች ተማሪዎች(#ለ2ኛ ዓመት 2ኛ ሰሚስቴር) እንዲሁም የ2014 ባች ተማሪዎች (#ለ1ኛ ዓመት 2ኛ ሰሚስቴር) ምዝገባ የሚካሄደው መስከረም 19-20/2015 ዓ/ም መሆኑ ይታወቃል፡፡

ስለሆነም ምዝገባው የሚፈጸመው በኦንላይን (Online registration) መሆኑን አውቃቹ በዩኒቨርሲቲው ድህረ ገጽ WW.Wru.edu.et በመግባት Online registration የሚለውን በመጫንና ተገቢውን ቅድመ ተከተል በመከተል እንድትመዘገቡ ብሏል፡፡

ሙሉ መረጃው ከላይ ተያይዟል

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
600 views05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 18:03:57
#ብሔራዊ_ፈተና

ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ከ50 ኪሎ ሜትር በላይ ለሆኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የትራንስፖርት ወጪን ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች እንደሚሸፍኑ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በሁለት ዙር ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አገልግሎቱ ገልጿል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ለ #ኤፍ_ቢ_ሲ የሰጡት ቃል ፦

- ፈተና ማተምን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች ከወዲሁ ተጠናቀዋል።

- ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በ50 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ተፈታኝ ተማሪዎች ወጪን በራሳቸው ይሸፍናሉ፤ ከ50 ኪሎ ሜትር ርቀት #በላይ የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች ወጪያቸውን ይሸፍናሉ።

- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ የሚፈቀዱላቸው ፦

• መጽሐፍትን፣
• ሲያጠኗቸው የነበሩ ማስታወሻወች፣
• የንጽህና መጠበቂያዎች
• የሌሊት ልብስ ከተፈቀዱት ቁሳቁስ መካከል ናቸው።

ተማሪዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ የቀበሌ መታወቂያ፣ የመፈተኛ ካርድ ወይም አድሚሽን ካርድ መያዝ ይኖርባቸዋል።

- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ የሚከለከሏቸው ቁሳቁስ፦

• ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
• ከጋብቻ ቀለበት ውጪ የተለየ ፈርጥ ያላቸው ቀለበቶች፣
• ሀብሎች ፣
• የጸጉር ጌጦች
• ድምጽ የሚያወጡ ጃኬቶች መያዝ አይቻልም።

- የመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የመኝታና የምግብ አገልግሎት ያመቻቻሉ።

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
1.4K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 15:07:19
#ASTU

ትምህርት ሚኒስቴር በዩኒቨርስቲ ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ቅድመ ሁኔታዎችን እያጠናቀቀ መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሁሉም የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከ13/01/2015-18/ 01 /2015 ድረስ ከዩኒቨርሲቲው እንዲወጡ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ስለሆነም ሁሉም ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት  ንብረታቸውን ይዘው ዩኒቨርሲቲውን ለቀው እንዲወጡ እናሳስባለን።

የመመለሻ ቀን በመገናኛ ብዙኃን ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል፡፡ (አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ )

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
2.0K views12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ