2022-09-17 13:53:56
አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ይዟቸው የመጡ አዳዲስ ነገሮች ምን ምን ናቸው ?
አምስት ዓመታትን በፈጀውና ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ስርዓተ ትምህርት ክለሳ የያዛቸው አዳዲስ ነገሮች ፦
ስርዓተ ትምህርቱ በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ባሉ የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚተገበር ቢሆንም፤ ኢንተርናሽናልና የማህበረሰብ አቀፍ ትምህርትቤቶችን አያካትትም፤
በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ግብረ ገብ፣ አገር በቀል ዕውቀት፣ ሙያና የቀለም ትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ ምርትና ተግባር፣ ጥናትና ምርምር ትኩረት ተደርጎባቸው እንዲሰጡ ይሆናሉ፤
ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ላሉ የክፍል ደረጃዎች ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋ ይሰጣል፤
ከሰባተኛ ክፍል እስከ12ኛ ክፍል ያሉት ደግሞ ሁሉም ተማሪ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ይማራል፤
ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እስከ12ኛ ክፍል ድረስ ያሉት ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ይወስዳሉ፤
ሦስተኛ ክፍል ላይ ተጨማሪ ቋንቋዎችን መስጠት ይጀመራል፤ በክልሎቹ ውስጥ በስፋት የሚነገረውን ተጨማሪ ቋንቋ በመምረጥ ተማሪዎቹ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲወስዱት ይደረጋል፤
በቀድመው የትምህርት ሥርዓት 10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረው አገራዊ የመልቀቂያ ፈተና ይቀርና በምትኩ አጠቃላይ ፈተናው በክልል ደረጃ ስድስተኛ ክፍል እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ ስምንተኛ እና 12ኛ ክፍል ላይ ይሰጣል፤
ከዚህ ቀደም ሦስት ዓመት የነበረው የተማሪዎች የዩኒሸርስቲ ቆይታ ደግሞ ዝቅተኛዉ አራት ዓመት ይደረጋል፤
ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች በመጀመሪያ ዓመት ከሚሠጡ ትምህርቶች ውስጥ እንደ ጂኦግራፊ፣ አንትሮፖሎጂ፣ ሶሺዮሎጂና ሥነ-ምግባር የመሳሰሉት ይካተታሉ፤
ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል የግብረገብ ትምህርት ይሰጣል፤ በተጨማሪም የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ውህድ የሆነ ትምህርት ይሰጣል፤
ሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል በተናጠል ይሰጡ የነበሩት ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪና ባይሎጂ አጠቃላይ ትምህርት ወይም ጀነራል ሳይንስ ተብለው እንዲሁም ጆግራፊና ሂስትሪም ተቀናጅተው የሚሰጡ ይሆናል፤
የሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች የእርሻ ትምህርት፣ አካውንቲንግ፣ ቢዝነስና ጀነራል የሆነውን የሥራና ክህሎት ትምህርት በሙያ ትምህርት ተካቶላቸው የሚሰጣቸው ይሆናል፤
11ኛ እና 12ኛ ክፍሎች ላይ ደግሞ ጤና ፣ ግብርና፣ የእርሻ ትምህርት፣ ማኒፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን፣ ቢዝነስ፣ አካውንቲንግ የመሳሰሉት የሙያ ትምህርትነቶችን እንዲማሩ ይደረጋል፤
የዘጠነኛና የአስረኛ ክፍልን እንዲሁም ከአንድ እስከስምንተኛ ክፍል ያሉ የተመረጡ አምስት የትምህርት አይነቶችን መጸሐፍት ዝግጅት ትምህርት ሚኒስቴር ያከናውነዋል፤
ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ያለውን የትምህርት መፀሐፍት ክልሎች በራሳቸው ባህልና አካባቢያዊ ሁኔታ ቃኝተው ያዘጋጁታል፤ ( የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት )
SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot
➹share &Join Us
@ethiopia_24 @ethiopia_24
@ethiopia_24 @ethiopia_24
8.3K views10:53