Get Mystery Box with random crypto!

ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiobooks — ከስነ-ፅሁፍ ዓለም
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiobooks — ከስነ-ፅሁፍ ዓለም
የሰርጥ አድራሻ: @ethiobooks
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.79K
የሰርጥ መግለጫ

የስነ-ፅሁፍ ቻናላችንን
👉 https://t.me/Ethiobooks ተቀላቀሉ።
ለማንኛውም አስተያየት እና ማስታወቂያ
👉 @firaolbm
@tekletsadikK
እናመሰግናለን።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-22 12:00:22 አሚሽ - 2 የመጨረሻው!!
456 viewsተስፋዬ መብራቱ, 09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 11:00:17 አሚሽ - 1
514 viewsተስፋዬ መብራቱ, 08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 10:55:21
አ ሚ ሽ
━━━━
«በመኪና ሳይሆን በጋሪ፣
በኤሌክትሪክ ሳይሆን በፋኖስ»
@ethiobooks
524 viewsተስፋዬ መብራቱ, 07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 09:02:04 ‹‹የሰውነት ቀን››
══✦══
መላኩ አላምረው
'
የሰው ልጅ፦
በየነገዱና፣ በጎሣው ተቧድኖ፤
ሰው የመሆን ክብርን፣ በወል ስም ሸፍኖ።
በእንግድነት ምድሩ፣ ክፍፍል ይፈጥራል፤
በክፍፍሉ ልክ፣
ቀን እየሰየመ፣ በድግሥ ያከብራል።

አክባሪ እስካገኘ፣ ይከበር ግድየለም፤
ካለማክበር እንጂ፣
ከማክበር 'ሚመጣ፣ ብዙም ክፋት የለም።

ነገር ግን ...
የሴት ቀን ብቻውን፣ ከወንድ ተለይቶ፤
የብሔርነት ቀን፣ ልዩ ቦታ አግኝቶ።
ከበሽታዎችም፣ እየተመረጠ፤
የሚከበርበት፣ ቀን እየተሰጠ፤
በድምቀት ሲከበር፣ ሲደለቅ ከዋለ፤
‹‹ሰው የመሆን ቀንስ››፣ ቢታሰብ ምና'ለ?
═══════
ነፍጠኛ ስንኞች
፳፻፱ ዓ.ም.

https://t.me/Ethiobooks
963 viewsተስፋዬ መብራቱ, 06:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-19 10:00:16 በነቀፋ ውስጥ ያደጉ ሰዎች
━━━━✦━━━━

→ ገና በእግሩ መራመድ ሳይጀምር ጡጦውን ወርውሮ ከምንጣፉ ላይ ሲያፈስ በማየት የተናደደችው እናቱ ጣራው እስኪሰነጠቅ ድረስ በመጮኽ «አንተ ደንቆሮና ደደብ ልጅ፣ ያደረግኸውን ታያለህ?» ስትለው፣

→ በእግሩ መራመድ ሲጀምር ያሰናዳችውን ቤት ሲያተረማምስ «አንተ አጥፊ! ተንኮለኛ ልጅ» መባልን የለመደ፣

→ ትምህርት ቤት ሲጀምር አስተማሪው «እንደ አንተ ደደብ ልጅ አጋጥሞኝ አያውቅም፤ ለምን እንደ ወንድሞችህ ጥሩ ተማሪ አልሆንክም?» እየተባለ ያደገ፣

→ አባቱ «እኔ በአንተ ዕድሜ በነበርኩ ጊዜ ብዙ ነገር እሠራ ነበር፤ አንተ ግን ጨርሶ ዋጋ የለህም!» የተባለው፣

→ እናቱ «ምነው ሳትወለድ ማህፀኔ ውስጥ ውሃ ሆነህ በቀረህ፤ ወልደህ በልጆችህ አግኘው።» በማለት እየተረገመ ያደገ ልጅ ውጤቱ ምን ያህል መጥፎ ይሆን?

ሲነቀፍ ያደገ ልጅ በራሱ እምነት ያጣል። እናቱ፣ አባቱና እንዲሁም አስተማሪው ስለ እርሱ የሰጡት አስተያየት እውነት ነው ብሎ ከተቀበለ፤ «አዎን ደካማ ነኝ፣ ሌሎች እንዳሉት የማልረባ ነኝ።» ብሎ ካመነ፣ ሁልጊዜ «እሳሳት ይሆናል» የሚል ፍርሃት በውስጡ ስለሚኖር ምንም ነገር ለመሞከርና ተሯሩጦ ለመሥራት ፍላጎት አይኖረውም። ራሱን የሚጠላ በመሆኑ በቀላሉ የአእምሮ ጭንቀት ይይዘዋል።

በማወቅና ባለማወቅ ልጆቻችንን በነቀፌታ ለማሳደግ የምንሞክር ወላጆች፣ ከምናመጣው ጥቅም ይልቅ የምናደርሰው ጉዳት ይበልጥ ያመዝናል። «አትረባም» ተብሎ ያደገ ልጅ ያን ተቀብሎ በማመን፣ ወደፊት ምንም ዓይነት ሙከራ ላለማድረግ ይወስናል። ተስፋ ቢስነቱን ያምንበታል።

የአእምሮ ጭንቀት ትልቁ ምልክት ለማንኛውም ነገር ምንም ግድ የሌለው ሆኖ ሲታይ ነው። ልጅን ጤናማና አግባብ ባለው ግንባታ ውስጥ ማሳደግ፣ በሕይወቱ ዓላማ ያለው ሰው ማድረግ ነው። በነቀፋ ውስጥ የሚያድግ ልጅ ለአእምሮ ጭንቀት የተጋለጠ ይሆናል።
━━━━━━━━
የአእምሮ ጭንቀት
ከመለሰ ወጉ
ገፅ 55 - 56

https://t.me/Ethiobooks
1.2K viewsተስፋዬ መብራቱ, 07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-17 15:00:02 ➥ ትሩማን ካፖቴ ጋደም ካላለ ስለ ድርሰት ሥራው ማሰብም ሆነ መጻፍ የማይችል ሰው ነበር። በዚህ ተፈጥሯዊ ባህርዩ ራሱን "የግድሞሽ ጸሐፊ" በማለት ይጠራል።

➥ እንግሊዛዊው ሮበርት ሉዊስ ስቴቨንሰንና አሜሪካዊው ማርክ ትዌይንም ተጋድሞ መጻፍን እንደምቹ የመጻፊያ ሁኔታና ስፍራ ይመርጡታል።

➥ የመኝታ ልብሱን (ፒጃማውን) ለብሶ ድርሰቱን የሚጽፈው እንግሊዛዊው ቤንጃሚን ዲዝሬሊ ነው።

➥ የፈረንሳዩ ደራሲ የባልዛክ ልማድ አስቀድሞ ቡና መጠጣት ነው። ባልዛክ ባንድ ቀን ውስጥ እስከ 50 ሲኒ ቡና ፉት ይል ነበር። 'አጥብቀው የወደዱት ለሞት ያደርሳል' እንዲሉ በካፊን መመረዝ ሳቢያ ሕይወቱ እንዳለፈች ይነገራል።

➥ ታዋቂው ሃያሲና ባለቅኔ ዶክተር ሳሙኤል ጆንሰን ግን በአንድ ስፍራ ተቀምጦ 25 ብርጭቆ ሻይ እየጠጣ ሲጽፍ በሽታ የሚሉት አያውቀውም ነበር ይባላል።

➥ በተለየ አመሉ የሚታወቀው ጀርመናዊው ደራሲ ሲለር ነበር። ባለቅኔው ሲለር በድርሰት ሥራው ላይ ጥሩ የፍራፍሬ ሽታና መጠጥ አይለዩትም ነበር። ከሚጽፍበት ጠረጴዛ መሳቢያ ውስጥ ለመዓዛ (ለሽታ) የሚሆን ፍራፍሬ አስቀምጦ፣ አእምሮውን ለማነቃቃት ደግሞ ቡናና ሻምፓኝ ቀላቅሎ ይጠጣል።

➥ አሜሪካዊቷ ባለቅኔ አሚ ሉዌል ሲጋራ በብዛት በማጨስ በታሪክ የመጀመሪያዋ የሴት ገጣሚ ሳትሆን አትቀርም የሚል ግምት አለ። የዚህች ደራሲ የሚያስደንቅ ሕይወት ለሲጋራ ባላት ልዩ ፍቅር ላይ የሚጠቀስ ነው። አሚ ሉዌል ሲጋራን እንድታጣውና በየትኛውም ሁኔታ እንዲለያት አትሻም። በ1915 አንደኛው የዓለም ጦርነት እየተፋፋመ በነበረበት ወቅት እንኳ ኤሚ ሉዌል ገና ለገና እያደር የሲጋራ እጥረት እየተፈጠረና በኋላም ጨርሶ እየጠፋ ይሄዳል በሚል ስጋት፤ አዘውትራ የምታጨሰውን 10ሺህ የማኒላ ሲጋራ አስቀድማ ከገበያ በመግዛት እቤቷ አስቀምጣለች።
━━━━━━━━
ጣዝማ - አስደናቂው የደራሲያን ሕይወት
ንጉሤ አየለ እና ደጀኔ ጥላሁን
2007 ዓ.ም.

https://t.me/Ethiobooks
1.5K viewsተስፋዬ መብራቱ, 12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-17 11:01:13 አስደናቂ የማነቃቂያ ልማዶች
════•✦•════

በብዕር ሰዎች ዘንድ ከሚታዩ አስደናቂ ገፅታዎች አንዱ በጽሑፍ ሥራቸው ላይ ሳሉ የሚያዘወትሩት የአሠራር ባህርይና የሚከተሉት የግል ልማድ ነው። አንዳንድ ደራሲያን የድርሰት ሃሳብ እንዲመነጭላቸው የሚያመቻቹት ወይም የሚመርጡት የግል የመጻፊያ ሁኔታና ለአእምሯቸው ማነቃቂያ በሥራ ላይ የሚያዘወትሯቸው ነገሮች ከተለመዱት የሰው ልጅ አድራጎቶች ለየት ብለው ለማመን እስኪያስቸግር ድረስ ያስደንቃሉ።

➥ በኔት ከርፍ የተባለው ደራሲ ኪነ-ጥበባዊ የድርሰት ሃሳብ የሚመነጭለት ሽንት ቤት ሲቀመጥ ነው።

➥ ሄሚንግዌይ በአውሮፕላን አደጋ ጀርባው ከመጎዳቱ በፊት ድርሰቶቹን ይጽፍ የነበረው ወንበር ላይ ተቀምጦ ሳይሆን በሁለት እግሩ ቆሞ ነበር። የድርሰት ሥራውን ከመጀመሩ በፊት ግን እርሳሶቹን የሚቀርጸው ተቀምጦ ነው። ቁጭ ብሎ የቀረጻቸውን እርሳሶች ቆሞ ይጽፍባቸዋል። ከዚያም ቆሞ የጻፈውን ረቂቅ ቆሞ በታይፕ ይመታል።

➥ የዘመናዊ አጭር ልብ-ወለድ አባትና በተለይም የወንጀል ምርመራ አተራረክ (ዲቴክቲቭ ስቶሪ) መስራች የሆነው ደራሲና ባለቅኔ ኤድጋር አለን ፖ፤ ጽሑፉን ወረቀት ላይ ከማስፈሩ በፊት ዘወትር ድመቱን ከትከሻው ላይ ያስቀምጥ ነበር።

➥ ጆን ዊልሞት የተባለው ባለቅኔም የግጥም ድርሰቱን ሲጽፍ ዝንጀሮውን ከትከሻው ላይ የማስቀመጥ ልማድ የነበረው ሰው ነው።

➥ ቶማስ ዎልፍ የተባለው አሜሪካዊ የብዕር ሰው ደግሞ ጽሑፉን ከመጀመሩ አስቀድሞ ረዥም የእግር ጉዞ ያደርጋል። በእግሩ ረዥም መንገድ ሄዶ ከመጣ በኋላ ብዕሩን አንስቶ ጽሑፉን ይያያዘዋል። ምናልባትም በዚህ አመሉ ላቡ ጠብ ሲል ድርሰቱም ጠብ ይልለታል ማለት ነው።

➥ እንግሊዛዊው ሩድያርድ ኪፕሊንግ፤ በጋዜጠኝነቱ እንዲሁም በአጭርና ረዥም ልብ-ወለድ ደራሲነቱ የበረታ ብዕረኛ ነበር። ይሁንና ያለ ጥቁር ቀለም የፈጠራ ድርሰቱን መጎዳኘት አይሆንለትም ነበር። በዚህ የተነሳ ጥቁር ቀለም የኪፕሊንግ የፈጠራ አዚም ዕጣ ክፍል እንደሆነ ይነገርለታል።
➠ ➠ ➠
@ethiobooks
1.3K viewsተስፋዬ መብራቱ, 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-16 21:29:25 Watch "ስኬት ድራማ ክፍል አስር / SIKET EP 10 “አለቃዬ ስራዬ ነው? ወይንስ የቀጠረኝ ሰው?! ”" on YouTube


1.2K viewsBiruk Turameb, 18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-15 12:00:15 ኒል አርምስትሮንግ - 2 የመጨረሻው!
1.4K viewsተስፋዬ መብራቱ, 09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-15 11:00:12 ኒል አርምስትሮንግ - 1
1.3K viewsተስፋዬ መብራቱ, 08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ