2023-06-05 10:00:02
ካፒቴን ጆን ብላንቻርድ
═══ ✦ ═══
ግሩም ተበጀ
'
ካፒቴን ጆን ብላንቻርድ ከተቀመጠበት አግዳሚ ወንበር ተነስቶ ዩኒፎርሙን እያስተካከለ ከፊት ለፊቱ ከታላቁ የኒውዮርክ ማዕከላዊ የባቡር ጣቢያ እየተገማሸረ የሚወጣውን የሰው ጎርፍ ይመለከት ጀመር፡፡ አዎን ዛሬ በታላቁ የባቡር ጣቢያ ታላቅ ቀጠሮ ይዟል። በልቡ ውስጥ ታላቅ ቦታ ለያዘች ግን ፈጽሞ ፊቷን አይቷት የማያውቀውን፣ ጽጌረዳ አበባ ይዛ የምትጠብቀውን ልጅ እየጠበቀ ነው።
በልጅቷ ላይ ስሜት ያደረበት ከዛሬ 13 ወራት በፊት ፍሎሪዳ ካለ ቤተ-መጻሕፍት የመጽሐፍ መደርደሪያ ላይ እንደዋዛ አንድ መጽሐፍ አንስቶ ገጾቹን ካገላበጠ በኋላ ነው። ቀልቡን የሳበው በመጽሀፉ ውስጥ የተጻፈው ቁምነገር አልነበረም። ይልቅስ በመጽሐፉ ገጾች ጥግጋት በልስልስ የእጅ ጽሑፍ በእርሳስ የሰፈሩት ማስታወሻዎች አንድ ረቂቅና አማላይ ነፍስን አመላከቱት። "ማን ይሆን እነዚህን ማስታወሻዎች ያሰፈረው?" ሲል ተደመመ።
ከመጽሐፉ የፊት ገጾች መሃል የመጽሐፉ የቀድሞ ባለቤት ስም ሰፍሯል - ሚስ ሆሊስ ሜይነል። ከብዙ ጥረት በኋላ አድራሻዋን ለማግኘት ቻለ። የምትኖረው ኒውዮርክ ውስጥ ነው። ደብዳቤ ጽፎ ተዋወቃት። እናም እንዲጻጻፉ የብዕር ጓደኛው እንድትሆን ጠየቃት። ብዙም ሳይቆይ ግን...የሁለተኛው ዓለም ጦርነት በመቀስቀሱ አሜሪካንን ጥሎ ወደ ባህር ማዶ አቀና፡፡ ከዚያ በኋላ ለቀጠሉት ለአንድ ዓመት ከአንድ ወር ጊዜያት በርካታ ደብዳቤዎች ተጻጻፉ፣ ይበልጥም ነፍስ ለነፍስ ለመተዋወቅ በቁ።
የተጻጻፏቸው እያንዳንዱ ደብዳቤዎችም በለም ልብ ላይ እንደሚያርፉ የፍቅር ዘሮች ነበሩ። ፍቅር አቆጠቆጠ። መውደድ ወፊቱ ክንፏን ዘረጋች። ካፒቴን ብላንቻርድ ፎቶዋን እንድትልክለት ጠየቃት። እሷ ግን አይሆንም አለች። "የኔ ገጽታ በግንኙነታችን ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ አለ?" ስትል ጠየቀች። "ከሌለ ፎቶዬ ምን ያደርግልሃል?"
ጦርነቱ ተጠናቅቆ ካፒቴን ብላንቻርድ ከአውሮፓ የሚመለስበት ጊዜ ሲደርስ፣ በኒውዮርክ ማዕከላዊ የባቡር ጣቢያ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ለመገናኘት ተቀጣጠሩ። "በቀጠሯችን ሰዓት በቀላሉ እንድትለየኝ በኮቴ ላይ ቀይ ጽጌረዳ አደርጋለሁ።" ብላ ጽፋለታለች። እናም... እነሆ... ካፒቴን ብላንቻርድ ዩኒፎርሙን
እያስተካከለ... በልቡ ውስጥ እንጂ በመልክ የማያውቃትን ባለ ቀይ ጽጌረዳዋን ጉብል ይጠባበቅ ጀመር። ከዚህ በኋላ ያለውን ገጠመኙን ራሱ ካፒቴን ብላንቻርድ እንዲህ ሲል ይተርክልናል፦
«አንዲት ቆንጅዬ ልጅ ወደኔ አቅጣጫ ስትመጣ አየሁ። ሸንቃጣ ነች። ከጠራ ሰማያዊ አይኖቿ ጋ ወርቃማ ጸጉሯ ትከሻዋ ላይ እንደ አንዳች እየተነሰነሰ ወደኔ ስትመጣ ራሷ ጸደይን ትመስላለች። ያለማመንታት በደመነፍስ ወደ ልጅቷ አቅጣጫ መጓዜን ቀጠልኩ።» ...
➠ ➠ ➠
@ethiobooks
1.1K viewsተስፋዬ መብራቱ, 07:00