Get Mystery Box with random crypto!

ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiobooks — ከስነ-ፅሁፍ ዓለም
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiobooks — ከስነ-ፅሁፍ ዓለም
የሰርጥ አድራሻ: @ethiobooks
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.79K
የሰርጥ መግለጫ

የስነ-ፅሁፍ ቻናላችንን
👉 https://t.me/Ethiobooks ተቀላቀሉ።
ለማንኛውም አስተያየት እና ማስታወቂያ
👉 @firaolbm
@tekletsadikK
እናመሰግናለን።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-05-06 11:00:05 ሰ ን  ዙ  -  1
1.3K viewsተስፋዬ መብራቱ, 08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 10:52:05
ሰ ን ዙ
━━━
«የ ጦ ር ነ ት ጠ ቢ ብ»
@ethiobooks
1.3K viewsተስፋዬ መብራቱ, 07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 10:51:55
1.2K viewsተስፋዬ መብራቱ, 07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 08:17:41 የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከሰቀሉ በኋላ ካደረጉት ታሪካዊ ዲስኩር፦
-------------------------------
"የሰማይ መላእክት፣ የምድር ሰራዊት ሊያስቡትና ሊያውቁት ይቻላቸው ባልነበረ፤ በዚህ በዛሬ ቀን ቸር እግዚአብሄር በመካከላችሁ ለመገኘት ስላበቃኝ በሰው አፍ የሚነገር ምስጋና የሚበቃ አይደለም። ከማናቸውም አስቀድሞ ለሁላችሁ ልነግራችሁና ልትረዱ የምፈልገው ይህ ቀን ላዲሲቱ ኢትዮጵያ ያዲስ ታሪክ ዘመን መክፈቻ መሆኑን ነው። በዚህም ባዲስ ዘመን ሁላችን መፈጸም ያለብን አዲስ ሥራ ይዠመራል።
. . . . .

የሀገሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ።

ዛሬ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ዘርግታ እልል እያለች ምስጋናዋን የምታቀርብበት፣ ደስታዋን የምትገልፅበት ቀን ነው።

የኢትዮጵያ ልጆች ከባድ የመከራ ቀንበርና ከዘለዓለም ባርነት ነፃ የወጡበት ቀንና እኛም አምስት ዓመት ሙሉ ተለይተነው ከነበረው ከምንወደውና ከምንናፍቀው ሕዝባችን ጋራ ለመቀላቀል የበቃንበት ቀን ስለሆነ ይህ ቀን የተከበረና የተቀደሰ፣ በያመቱም ታላቁ የኢትዮጵያ በዐል የሚውልበት ነው። በዚህም ቀን ለሚወዷት ላገራቸው ነፃነት፣ ለንጉሠ ነገሥታቸው ክብርና ለሰንደቅ ዓላማቸው ክብር ካባቶቻቸው የተላለፈውን ጥብቅ አደራ አናስወስድም በማለት መስዋእት ሆነው ደማቸውን ያፈሰሱትን ዐጥንታቸውን የከሰከሱትን ዠግኖቻችንን እናስታውሳለን። ለዚህም ለዠግኖች የኢትዮጵያ ታሪክ ምስክር ይሆናል።

ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ በዝርዝር ተነግረውና ተቆጥረው የማያልቁ ያገኘናቸው መከራና ስቃይ ትምህርት ሆነውን ሠራተኛነት፣ አንድነት፣ ኅብረትና ፍቅር በልባችሁ ተጽፈው ለምናስበው ለኢትዮጵያ ጉዳይ ረዳቶች ለመሆን ዋና ትምህርት የሚሰጣችሁ ነው።
ባዲሷ ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ወዲያ የማትነጣጠሉ፣ በሕግ ፊት ትክክልነትና ነፃነት ያላችሁ ሕዝቦች እንድትሆኑ እንፈልጋለን።
. . . . .

https://t.me/Ethiobooks
1.4K viewsተስፋዬ መብራቱ, 05:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 08:16:38
★ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም. ከታላቁ ቤተ መንግሥታቸው ገብተው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ሲሰቅሉ።
1.1K viewsተስፋዬ መብራቱ, 05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 10:00:08
እ ን ጀ ራ
 


እንጀራ በሰፌድ፣ አሞሌ በገመድ።


የእንጀራ ወጡ ረኃብ ነው።


እንጀራ ለራብ፣ ድንጋይ ለካብ።


የእንጀራ ቀንጣቢ፣ የድመት አላቢ።


እንጀራ ያለው ክቡድ፣ እንጀራ የሌለው ዕብድ።


እንጀራው ሳይኖር ከወጡ አስነኩልኝ።


የዳጉሳ እንጀራ በትኩሱ፣ የባእድ ፍቅር በአዲሱ።


እንጀራ የለም እንጂ በወተት አምገህ ትበላ ነበር።


እንጀራን ምን ይጨርሰዋል? መጉረስ።


የሽሮ ፉከራ፣ እስኪቀርብ እንጀራ።


እንጀራ ለባዕድ፣ መከራ ለዘመድ።


እንጀራ ይጋግሯል እማድቤት፣ መላ ያማክሯል ለሴት።


የእንጀራ አብራጃውን፣ የወጥ ለብታውን።


እንጀራ በማየት አይጠገብም።


እንጀራ ያለ ወጥ፣ ቤት ያለ ሴት፣ ከብት ያለበረት።


ለእንጀራ ሽሮ፣ ለጭፈራ ከበሮ።


የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል።

       
ነገር በምሳሌ
@ethiobooks
1.4K viewsተስፋዬ መብራቱ, 07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 10:00:07 እንጀራ እንደ - - -


"- - - ምን?" እንዳትሉኝ፤ እንጀራ - ማለቴ የሻገተ እንጀራ የበሽታ ምንጭ ሊሆን እንደሚችል እናንተም ትገምቱ ይሆናል። ሁላችንም እንጀራ በሊታዎች ነን ካልን በተለያየ ጊዜ የሻገተ እንጀራ የመጠቀም ዕድላችን በማወቅም ባለማወቅም ያጋጥማል። ያው እንደምትውቁት በአብዛኛው የሻገተ እንጀራ ሻገተ ተብሎ አይጣልም። ወይ በፀሐይ፣ ወይ በሙቀት ደርቆ የድርቆሽ ፍርፍር ሆኖ ይቀርባል።

አንዳንዶቻችን ቤት ደሞ "ለልጅ ምንም አይለው" ተብሎ ይሰጠናል። አሊያም "የእንጀራ ጡር አለው" ተብሎ ወይ ለኔ ብጤ አሊያም ለቤት እንስሳት በመኖነት ይቀርባል። ችግሩ ያለው እዚህ ላይ ነው። የሻገተ እንጀራ የሚያስወግድ አንጀት ስለሌለን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እንጠቃለን።

ሻጋታ የፈንገስ ዓይነት ነው። ፈንገሱም በውስጡ 'Aflatoxin' የሚባል አደገኛ መርዛማነት ያለው ንጥረ ነገር ይዟል። ይህ 'አፍላቶክሲን' የሚያስከትለው ጉዳት እንደ ግለሰቡ እድሜ፣ ፆታ፣ የመርዙ መጠን፣ የተጠቃበት ጊዜ (Duration)፣ የግለሰቡ የጤና ደረጃ፣ የሚኖርበት አካባቢ ሊለያይ ቢችልም ጎጂነቱ ግን ምንም የማያወላውል ነው።

ባጠቃላይ በዚህ ከሻጋታ የሚገኘው መርዝ ሰዎችን በሁለት መንገድ ይጎዳል።
አንደኛው፦ ከፍተኛ መጠን ያለውን መርዝ በአጭር ጊዜ ውስጥ የወሰድን ከሆነ ለጉበት በሽታ፣ ለካንሰር፣ ለአእምሮ ዘገምተኝነት፣ ለሆድ ህመም፣ ለሳንባ እና ለአጠቃላይ የሰውነት እብጠት እንዲሁም ለሞት ሊዳርግ ይችላል።
ሁለተኛው፦ ደግሞ አነስተኛ መጠን ያለውን መርዝ ለረዥም ጊዜ መውሰድ ሲሆን ይህም በተለይ ከእንጀራ ጋር በተያያዘ፣ በኛ ማኅበረሰብ ውስጥ ሊከሰት የሚችለው ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የአካላዊ እድገት ዘገምተኛነትና የጉበት ካንሰር ሊያስከትል እንደሚችል በሰፊው ይታመናል። ምናልባት የኛ ሀገር ልጆች ኮሳሳ መሆንና የጉበት ካንሰር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ መምጣት፣ ከዚህ ጋር የተያያዘ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት አለኝ።

በዚህ በኩል ጥናቶች ቢሠሩ እውነቱ ፍንትው ብሎ ሊወጣ እንደሚችል እያመንኩ፤ እንጀራን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም የሻገቱ የምግብ ዓይነቶችን በሰውም ሆነ በእንስሳት መኖነት መጠቀም ጠንቁ ብዙ መሆኑን ተገንዝበን፤ በተለይ ሕፃናትን ከነዚህ ዓይነት ምግቦች መከላከል ችላ የማይባል ጉዳይ እንዲሆን አሰምርበታለሁ!!
>>>
ገፅ 75 - 76
━━━━━━━━━
ጤና፣ ነገር እና ጉዳይ
ዶክተር ብርሃኔ ረዳኢ

https://t.me/Ethiobooks
1.5K viewsተስፋዬ መብራቱ, 07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 23:51:47 አንቺ ልትነግሽበት! ስኬት ክፍል አንድ ቅምሻ - Siket EP 01
https://youtube.com/shorts/8bKSMuQRl1c?feature=share
122 viewsBiruk Turameb, 20:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 09:06:33 ይ በ ለ ኝ
═✦═
ይስማዕከ ወርቁ
'
የኔ ገብስ ዛላ
"ማማ" ሳልሰራልሽ
"ወንጭፌ" ሳይሰላ
"ወፍሽን" "እር" - - - ሳልል
"ማሳዬን" ሳላጥረው
ኑሮዬን ሳሰላ
ሳያሽሽ "መዳፌ"
ታንቀህ ክረም ሲለኝ
ምርቅሽን ሳልከላ
እፍ ሳልል ቅሜሽ
ይኸው እስከዛሬ
ከትናጋዬ ነሽ።
═══════


ተላለፉ ሲለን
══✦══
ከመረዋው ውግረት
ከቃጭሉ ዋይታ
እኩል ብንሰማም
በአንድ ደወል ድምፅ
ግለ-ሕሊናችን
አንድ ላይ ቢደቃም
ተላለፉ ሲለን
ፊትና ኋላ እንጂ
እኩል አንነቃም።
═══════
የወንድ ምጥ

https://t.me/Ethiobooks
658 viewsተስፋዬ መብራቱ, 06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 10:00:16

❝መጽሐፍን ከማቃጠል የባሰ በርካታ ወንጀሎች አሉ። ከነዚህ መሃል መጽሐፍትን አለማንበብ ትልቁ ወንጀል ነው።❞
ጆሴፍ ብሮድስኪ


❝የትምህርት ሁሉ ዓላማና ግብ ስብዕናን ማዳበር ነው።❞
ፍራንሲስ ፓርከር


❝ማንበብ ያለብህ ለመቃረን ወይም ስህተት ለመፈለግ ሳይሆን፣ ለማመዛዘን እና ለማወቅ ይሁን።❞
ፕሮ. ዚግመንት ባውማን


❝ምናባችንን ከተኛበት የሚቀሠቅስልን ሞተር መጽሐፍ ማንበብ ነው።❞
አለን ቤኔት


❝ትምህርት ከሚለግሳቸው ምግባራት ሁሉ የሚልቀው፣ መከናወን ያለበትን ተግባር ተወደደም ተጠላም በተመደበለት ጊዜ ውስጥ ማከናወን መቻል ነው።❞
ቶማስ ሃክስሊ


❝የዕውቀት ብልጭታ ያሞቀናል፣ በጎ ሲቃ ነውና።❞
ኦ ቪ ድ


ጥቅሶች
@ethiobooks
479 viewsተስፋዬ መብራቱ, 07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ