2023-04-05 10:22:14
የደለቡ ክፍያዎች
══ ✦ ══
በስነ-ፅሁፍ ሙያ ለተሰማሩ ደራሲያን ከተሰጡት ክፍያዎች በቃላት ደረጃ ብቻ 15 ሺህ ዶላር በማግኘት ከፍተኛውን ደረጃ የያዘ ደራሲ አለ። ይህም ደራሲ ከ1898 - 1961 የኖረው አሜሪካዊው ኧርነስት ሄሚንግዌይ ነው።
ሄሚንግዌይ "ዘ ሎንገስት ዴይ" በተሰኘው ፊልም ጽሑፍ (ስክሪፕት) ላይ ጆንስ እና ግሎሪያ ከባህር ዳርቻ ተቀምጠው ከሚነጋገሩት ምልልስ መሃል «
I can't eat that blood old box of tunny fish» የሚለውን ዓረፍተ ነገር ሁለቱን ቃላት አሻሽሎ፣ አራቱን ቃላት ደግሞ ለውጦ ወደ «
I can't stand this damned old tuna fish» በመቀየሩ፤ በአሻሻለውና በለወጠው በእያንዳንዱ ቃል 2 ሺህ 500 ዶላር፤ በጠቅላላው በስድስቱ ቃላት 15 ሺህ ዶላር ተከፍሎታል።
በዚህ ወደር የለሽ ክፍያው "ዘ ጊነስ ቡክ ኦፍ ወርልድ ሪከርድስ" ሄሚንግዌይን የቀደምትነት ደረጃ በመስጠት መዝግቦታል።
ከዚህ ሌላ "ስፖርትስ ኢሉስትሬትድ" ለተሰኘ መጽሔት በ2 ሺህ ቃላት ስለ ጎሽ ትግል ስፖርት በጻፈው መጣጥፍ፣ በእያንዳንዷ ቃል 15 ዶላር፣ በድምሩ 30 ሺህ ዶላር ተከፍሎታል።
ሄሚንግዌይ "የታላቅ ክፍያ አዚመኛ" የሚያሰኘው ሌላም የብዕር ውጤት የገጠመው ሰው ነው። ይኽውም "ዘ ስኖው ኦፍ ኪሊማንጃሮ" የተባለው የአጭር ልቦለድ ድርሰቱ፤ ከአጭር ልቦለዶች የሽያጭ ዋጋ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያውን አስደናቂና ከፍተኛ ክፍያ አስገኝቶለታል።
ሄሚንግዌይ በዚህ ድርሰቱ በ1936 ታትሞ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ በተሸጠውና በኋላም ድርሰቱ በፊልም ተሰርቶ የተሰጠውን ክፍያ ጨምሮ በጠቅላላው 250 ሺህ ወይም ሩብ ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ እጁ ገብቶለታል።
━━━━━━━━
ጣዝማ - አስደናቂው
የደራሲያን ሕይወት
ንጉሤ አየለ እና ደጀኔ ጥላሁን
https://t.me/Ethiobooks
281 viewsተስፋዬ መብራቱ, 07:22