2023-04-03 10:01:58
(የዐባይ ውኃ ብልሃርዚያ ያስይዛል!?) «እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2018 ዓ.ም. ሽራይን አብደል ዋሂድ የተባለች የግብፅ ታዋቂና ተወዳጅ ዘፋኝ በተባበሩት ዐረብ ኢሚሬትስ ውስጥ ታላቅ ኮንሰርት ተዘጋጅቶላት ታዋቂ የሆነውንና ስለ ዐባይ ወንዝ ግርማና ፍቅር የሚያወሳውን ዘፈኗን ለአድናቂዎቿ ታቀነቅናለች። የዘፈኑ መጠሪያ "
Haven't You Ever Drunk from the Nile?" የሚል ሲሆን፤ የዘፈኑ ይዘት ከሞላ ጎደል "ከዐባይ ውኃ የጠጣ ሰው የትም ቢሆን ተመልሶ መምጣቱ አይቀርም" የሚል ነው።
ዘፈኑን በስሜት ዘፍና ስትጨርስ አድናቂዎቿ እንድትደግምላቸው በጩኸትና ፉጨት ይጠይቃሉ። ጥያቄውን ተቀብላ ደግማ ዘፈነች። አሁንም ስትጨርስ እንደገና እንድትዘፍን ለሦስተኛ ጊዜ ተጠየቀች። በዚህ ጊዜ ከመደጋገም ይልቅ ወደ ሌሎች ዘፈኖቿ መሄድ ስለፈለገች ጉዳዩን በቀልድ መልክ ለታዳሚዎቿ፦ "ወዳጆቼ! የዐባይን ውኃ ደጋግሞ መጠጣት ብልሃርዚያ ያስይዛል፤ ስለዚህ ይቅርባችሁ። ይልቅ ሌላ የምንጭ ውኃ ጠጡ።" አለች።
ይህንን እንደተናገረች ከኢሚሬትስ እስከ ግብፅ ካይሮ፣ ከተራ ሙዚቃ አድናቂ እስከ ሀገሪቱ ፖለቲከኞች ጆሮ ወሬው በብርሃን ፍጥነት ተዳረሰ።
ሽራይን ታላቁን ወንዝ ዐባይን በመድፈሯና ክብሩን ዝቅ በማድረጓ ተከሰሰች። ኮንሰርቷ እንዲቋረጥ ተደረገ። የግብፅ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የእስር ብይን አስተላለፈባት። አየህ የዐባይን ክብር በግብፅ!» ...
«እኛ ሀገር የራሳችንን ድክመት ወደ ወንዙ አስተላልፈን፦ 'ዐባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል!' በማለት እንሳለቃለን። እውነታው ግን ለዐባይ ማደሪያ ያልሰጠነው እኛ ነን። እናም የችጋር ግንድ ይዘን የምንዞር እኛ እንጂ እርሱማ አስዋን ላይ ማደሪያ ከተበጀለት ቆየ እኮ!» ...
«እናም ስለ ውኃ ባለን ደካማ የሥነ-ልቡና ውቅር ምክንያት ኢትዮጵያ ሀገራችን የዚህ ተአምራዊ ፍጥረት መፍለቂያና ማከማቻ ብትሆንም፤ አሁንም ድረስ ውኃ ታቅፈን በድርቅ እንሰቃያለን፣ ኃይል ቀብረን በጨለማ እንኖራለን።» ...
«ልብ በል! ... ከኢትዮጵያ ወደ ሌላ የሚፈስ እንጂ ከሌላ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣ ወንዝ አንድም የለም። ኢትዮጵያ ወንዞቿ ከተቀደሰው ማህፀኗ ፈልቀው ከእርሷ ወጥተው የሚሄዱ እንጂ ከሌላ ቦታ መንጭተው የሚመጡ አይደሉም። የኢትዮጵያ ወንዞች ደግሞ አፈርና ማዕድን የታደሉ የእናት ጡት ማለት ናቸው። የኢትዮጵያ ወንዞችና ጅረቶች ከአካል ከገላዋ የሚመነጩ፣ ከውስጥ ከሕዋሷ የሚቀዱ፤ ለእኛ እንዲሆኑን፣ እንዲያሳድጉን፣ እንዲያጎለምሱን ከፈጣሪ የተሰጡን ስጦታዎች ነበሩ።» ...
>>>
━━━━━━━━
ሚተራሊዮን
ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
ጥር 2014 ዓ.ም.
187 - 189
https://t.me/Ethiobooks
698 viewsተስፋዬ መብራቱ, edited 07:01