Get Mystery Box with random crypto!

ይሄ ጫማ እኔ ነኝ ══✦══ አሌክስ አብርሃም ' ከላይ ከባድ ሸክም ግዙፍ የሰው ኪሎ ከ | ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

ይሄ ጫማ እኔ ነኝ
══✦══
አሌክስ አብርሃም
'
ከላይ ከባድ ሸክም ግዙፍ የሰው ኪሎ
ከታች ደግሞ መሬት ያውም መሬት ግሎ
በሁለቱ መሀል ይህ ጫማ ተጣብቆ
ያረጀ ዕለት ነው የሚጣለው ወልቆ
.
እናም
.
ይሄ
ይህ ጫማ እኔ ነኝ
የሰዎችን ሀሳብ በግድ የተጫንኩኝ
ከሕይወት እግር ላይ እስክጣል ወልቄ
ከባለ ጊዜ'ና ህሊናዬ መሀል ያለሁ ተጣብቄ።
═══════

https://t.me/Ethiobooks