Get Mystery Box with random crypto!

‹‹የሰውነት ቀን›› ══✦══ መላኩ አላምረው ' የሰው ልጅ፦ በየነገዱና፣ በጎሣው ተቧድ | ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

‹‹የሰውነት ቀን››
══✦══
መላኩ አላምረው
'
የሰው ልጅ፦
በየነገዱና፣ በጎሣው ተቧድኖ፤
ሰው የመሆን ክብርን፣ በወል ስም ሸፍኖ።
በእንግድነት ምድሩ፣ ክፍፍል ይፈጥራል፤
በክፍፍሉ ልክ፣
ቀን እየሰየመ፣ በድግሥ ያከብራል።

አክባሪ እስካገኘ፣ ይከበር ግድየለም፤
ካለማክበር እንጂ፣
ከማክበር 'ሚመጣ፣ ብዙም ክፋት የለም።

ነገር ግን ...
የሴት ቀን ብቻውን፣ ከወንድ ተለይቶ፤
የብሔርነት ቀን፣ ልዩ ቦታ አግኝቶ።
ከበሽታዎችም፣ እየተመረጠ፤
የሚከበርበት፣ ቀን እየተሰጠ፤
በድምቀት ሲከበር፣ ሲደለቅ ከዋለ፤
‹‹ሰው የመሆን ቀንስ››፣ ቢታሰብ ምና'ለ?
═══════
ነፍጠኛ ስንኞች
፳፻፱ ዓ.ም.

https://t.me/Ethiobooks