Get Mystery Box with random crypto!

በነቀፋ ውስጥ ያደጉ ሰዎች ━━━━✦━━━━ → ገና በእግሩ መራመድ ሳይጀምር ጡጦውን ወርውሮ ከም | ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

በነቀፋ ውስጥ ያደጉ ሰዎች
━━━━✦━━━━

→ ገና በእግሩ መራመድ ሳይጀምር ጡጦውን ወርውሮ ከምንጣፉ ላይ ሲያፈስ በማየት የተናደደችው እናቱ ጣራው እስኪሰነጠቅ ድረስ በመጮኽ «አንተ ደንቆሮና ደደብ ልጅ፣ ያደረግኸውን ታያለህ?» ስትለው፣

→ በእግሩ መራመድ ሲጀምር ያሰናዳችውን ቤት ሲያተረማምስ «አንተ አጥፊ! ተንኮለኛ ልጅ» መባልን የለመደ፣

→ ትምህርት ቤት ሲጀምር አስተማሪው «እንደ አንተ ደደብ ልጅ አጋጥሞኝ አያውቅም፤ ለምን እንደ ወንድሞችህ ጥሩ ተማሪ አልሆንክም?» እየተባለ ያደገ፣

→ አባቱ «እኔ በአንተ ዕድሜ በነበርኩ ጊዜ ብዙ ነገር እሠራ ነበር፤ አንተ ግን ጨርሶ ዋጋ የለህም!» የተባለው፣

→ እናቱ «ምነው ሳትወለድ ማህፀኔ ውስጥ ውሃ ሆነህ በቀረህ፤ ወልደህ በልጆችህ አግኘው።» በማለት እየተረገመ ያደገ ልጅ ውጤቱ ምን ያህል መጥፎ ይሆን?

ሲነቀፍ ያደገ ልጅ በራሱ እምነት ያጣል። እናቱ፣ አባቱና እንዲሁም አስተማሪው ስለ እርሱ የሰጡት አስተያየት እውነት ነው ብሎ ከተቀበለ፤ «አዎን ደካማ ነኝ፣ ሌሎች እንዳሉት የማልረባ ነኝ።» ብሎ ካመነ፣ ሁልጊዜ «እሳሳት ይሆናል» የሚል ፍርሃት በውስጡ ስለሚኖር ምንም ነገር ለመሞከርና ተሯሩጦ ለመሥራት ፍላጎት አይኖረውም። ራሱን የሚጠላ በመሆኑ በቀላሉ የአእምሮ ጭንቀት ይይዘዋል።

በማወቅና ባለማወቅ ልጆቻችንን በነቀፌታ ለማሳደግ የምንሞክር ወላጆች፣ ከምናመጣው ጥቅም ይልቅ የምናደርሰው ጉዳት ይበልጥ ያመዝናል። «አትረባም» ተብሎ ያደገ ልጅ ያን ተቀብሎ በማመን፣ ወደፊት ምንም ዓይነት ሙከራ ላለማድረግ ይወስናል። ተስፋ ቢስነቱን ያምንበታል።

የአእምሮ ጭንቀት ትልቁ ምልክት ለማንኛውም ነገር ምንም ግድ የሌለው ሆኖ ሲታይ ነው። ልጅን ጤናማና አግባብ ባለው ግንባታ ውስጥ ማሳደግ፣ በሕይወቱ ዓላማ ያለው ሰው ማድረግ ነው። በነቀፋ ውስጥ የሚያድግ ልጅ ለአእምሮ ጭንቀት የተጋለጠ ይሆናል።
━━━━━━━━
የአእምሮ ጭንቀት
ከመለሰ ወጉ
ገፅ 55 - 56

https://t.me/Ethiobooks