Get Mystery Box with random crypto!

➥ ትሩማን ካፖቴ ጋደም ካላለ ስለ ድርሰት ሥራው ማሰብም ሆነ መጻፍ የማይችል ሰው ነበር። በዚህ ተ | ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

➥ ትሩማን ካፖቴ ጋደም ካላለ ስለ ድርሰት ሥራው ማሰብም ሆነ መጻፍ የማይችል ሰው ነበር። በዚህ ተፈጥሯዊ ባህርዩ ራሱን "የግድሞሽ ጸሐፊ" በማለት ይጠራል።

➥ እንግሊዛዊው ሮበርት ሉዊስ ስቴቨንሰንና አሜሪካዊው ማርክ ትዌይንም ተጋድሞ መጻፍን እንደምቹ የመጻፊያ ሁኔታና ስፍራ ይመርጡታል።

➥ የመኝታ ልብሱን (ፒጃማውን) ለብሶ ድርሰቱን የሚጽፈው እንግሊዛዊው ቤንጃሚን ዲዝሬሊ ነው።

➥ የፈረንሳዩ ደራሲ የባልዛክ ልማድ አስቀድሞ ቡና መጠጣት ነው። ባልዛክ ባንድ ቀን ውስጥ እስከ 50 ሲኒ ቡና ፉት ይል ነበር። 'አጥብቀው የወደዱት ለሞት ያደርሳል' እንዲሉ በካፊን መመረዝ ሳቢያ ሕይወቱ እንዳለፈች ይነገራል።

➥ ታዋቂው ሃያሲና ባለቅኔ ዶክተር ሳሙኤል ጆንሰን ግን በአንድ ስፍራ ተቀምጦ 25 ብርጭቆ ሻይ እየጠጣ ሲጽፍ በሽታ የሚሉት አያውቀውም ነበር ይባላል።

➥ በተለየ አመሉ የሚታወቀው ጀርመናዊው ደራሲ ሲለር ነበር። ባለቅኔው ሲለር በድርሰት ሥራው ላይ ጥሩ የፍራፍሬ ሽታና መጠጥ አይለዩትም ነበር። ከሚጽፍበት ጠረጴዛ መሳቢያ ውስጥ ለመዓዛ (ለሽታ) የሚሆን ፍራፍሬ አስቀምጦ፣ አእምሮውን ለማነቃቃት ደግሞ ቡናና ሻምፓኝ ቀላቅሎ ይጠጣል።

➥ አሜሪካዊቷ ባለቅኔ አሚ ሉዌል ሲጋራ በብዛት በማጨስ በታሪክ የመጀመሪያዋ የሴት ገጣሚ ሳትሆን አትቀርም የሚል ግምት አለ። የዚህች ደራሲ የሚያስደንቅ ሕይወት ለሲጋራ ባላት ልዩ ፍቅር ላይ የሚጠቀስ ነው። አሚ ሉዌል ሲጋራን እንድታጣውና በየትኛውም ሁኔታ እንዲለያት አትሻም። በ1915 አንደኛው የዓለም ጦርነት እየተፋፋመ በነበረበት ወቅት እንኳ ኤሚ ሉዌል ገና ለገና እያደር የሲጋራ እጥረት እየተፈጠረና በኋላም ጨርሶ እየጠፋ ይሄዳል በሚል ስጋት፤ አዘውትራ የምታጨሰውን 10ሺህ የማኒላ ሲጋራ አስቀድማ ከገበያ በመግዛት እቤቷ አስቀምጣለች።
━━━━━━━━
ጣዝማ - አስደናቂው የደራሲያን ሕይወት
ንጉሤ አየለ እና ደጀኔ ጥላሁን
2007 ዓ.ም.

https://t.me/Ethiobooks