Get Mystery Box with random crypto!

አስደናቂ የማነቃቂያ ልማዶች ════•✦•════ በብዕር ሰዎች ዘንድ ከሚታዩ አስደናቂ ገፅታዎች | ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

አስደናቂ የማነቃቂያ ልማዶች
════•✦•════

በብዕር ሰዎች ዘንድ ከሚታዩ አስደናቂ ገፅታዎች አንዱ በጽሑፍ ሥራቸው ላይ ሳሉ የሚያዘወትሩት የአሠራር ባህርይና የሚከተሉት የግል ልማድ ነው። አንዳንድ ደራሲያን የድርሰት ሃሳብ እንዲመነጭላቸው የሚያመቻቹት ወይም የሚመርጡት የግል የመጻፊያ ሁኔታና ለአእምሯቸው ማነቃቂያ በሥራ ላይ የሚያዘወትሯቸው ነገሮች ከተለመዱት የሰው ልጅ አድራጎቶች ለየት ብለው ለማመን እስኪያስቸግር ድረስ ያስደንቃሉ።

➥ በኔት ከርፍ የተባለው ደራሲ ኪነ-ጥበባዊ የድርሰት ሃሳብ የሚመነጭለት ሽንት ቤት ሲቀመጥ ነው።

➥ ሄሚንግዌይ በአውሮፕላን አደጋ ጀርባው ከመጎዳቱ በፊት ድርሰቶቹን ይጽፍ የነበረው ወንበር ላይ ተቀምጦ ሳይሆን በሁለት እግሩ ቆሞ ነበር። የድርሰት ሥራውን ከመጀመሩ በፊት ግን እርሳሶቹን የሚቀርጸው ተቀምጦ ነው። ቁጭ ብሎ የቀረጻቸውን እርሳሶች ቆሞ ይጽፍባቸዋል። ከዚያም ቆሞ የጻፈውን ረቂቅ ቆሞ በታይፕ ይመታል።

➥ የዘመናዊ አጭር ልብ-ወለድ አባትና በተለይም የወንጀል ምርመራ አተራረክ (ዲቴክቲቭ ስቶሪ) መስራች የሆነው ደራሲና ባለቅኔ ኤድጋር አለን ፖ፤ ጽሑፉን ወረቀት ላይ ከማስፈሩ በፊት ዘወትር ድመቱን ከትከሻው ላይ ያስቀምጥ ነበር።

➥ ጆን ዊልሞት የተባለው ባለቅኔም የግጥም ድርሰቱን ሲጽፍ ዝንጀሮውን ከትከሻው ላይ የማስቀመጥ ልማድ የነበረው ሰው ነው።

➥ ቶማስ ዎልፍ የተባለው አሜሪካዊ የብዕር ሰው ደግሞ ጽሑፉን ከመጀመሩ አስቀድሞ ረዥም የእግር ጉዞ ያደርጋል። በእግሩ ረዥም መንገድ ሄዶ ከመጣ በኋላ ብዕሩን አንስቶ ጽሑፉን ይያያዘዋል። ምናልባትም በዚህ አመሉ ላቡ ጠብ ሲል ድርሰቱም ጠብ ይልለታል ማለት ነው።

➥ እንግሊዛዊው ሩድያርድ ኪፕሊንግ፤ በጋዜጠኝነቱ እንዲሁም በአጭርና ረዥም ልብ-ወለድ ደራሲነቱ የበረታ ብዕረኛ ነበር። ይሁንና ያለ ጥቁር ቀለም የፈጠራ ድርሰቱን መጎዳኘት አይሆንለትም ነበር። በዚህ የተነሳ ጥቁር ቀለም የኪፕሊንግ የፈጠራ አዚም ዕጣ ክፍል እንደሆነ ይነገርለታል።
➠ ➠ ➠
@ethiobooks