Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 132.13K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2024-04-16 04:37:21 ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን የተሰጠ መግለጫ
***
ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ የማይማረው ህወሐት ለአራተኛ ዙር በህዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል። የፌዴራልና የአማራ ክልል ክልሉ መንግስታትም በህዝብ ላይ የተቃጣውን የጥፋት ወረራ በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ አበክረን እንጠይቃለን!

የኢትዮጵያ ህዝብ ዘላለማዊ ጠላት የሆነው ወያኔ ህወሐት በህዝብ ትግል ተገፍትሮ ወደ ትግራይ ከተሰበሰበ በኋላ በተደጋጋሚ ወረራ በመፈፀም በህዝባችን ላይ ለጆሮ የሚከብድ ዘግናኝ ግፍ ፈፅሟል። ምንም እንኳን ህወሐት በተደጋጋሚ ጊዜ በቆሰቆሰው ጦርነት የአማራ እና የአፋር ህዝብ በቀጥታ የገፈቱ ቀማሽ ይሁኑ እንጅ ዋና ዓላማው ኢትዮጵያ ሐገራችንን መበታተን እና የፈራረሰች ሐገር መፍጠር መሆኑን በአፈ ቀላጤው በኩል በተደጋጋሚ ተናግሯል።

ይህ የእናት ጡት ነካሽ ቡድን የሐገራችን ደጀን የሆነውን የሰሜን እዝ የመከለከያ ሰራዊት በማጥቃቱ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያጋጠመውን ቁጣ መቋቋም ተስኖት ለሶስተኛ ጊዜ እየተመላለሰ ያደረገው የሐገር ማፍረስ ሙከራ ባይሳካለትም እንኳን አድፍጦ ለጦርነት ከመዘጋጀት ግን ቦዝኖ አያውቅም።

ህወሐት ከጦርነት ውጭ መኖር የማይችል፣ በጦርነት አድጎ በጦርነት ያረጀ ቡድን በመሆኑ በመላው የኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ አማፂያንን ከማስታጠቅ አልፎ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በመወገን ሐገራችንን የጦር ቀጠና ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ነበር የከረመው። በቀጥታ ከሚደግፋቸው የጥፋት ኃይሎች በተጨማሪ የራሱን ኃይል በማደራጀት የሰርጎ ገብ ኃይል እየላከ ህዝባችንን ሲረብሽ መክረሙ ሳያንሰው በአሁኑ ሰዓት በራያ በኩል ቀጥተኛ የሆነ ጥቃት በህዝባችን ላይ ለአራተኛ ጊዜ ወረራ ከፍቶ ይገኛል።

ኋላ ቀርነት እና ግትርናት ዋና መገለጫው የሆነው የጥፋት ቡድን የሚሊዮኖችን ህይዎት በቀጠፈውና ከተደጋጋሚ ስህተቱ ባለመማር ዛሬም ለሌላ ዙር እልቂት ተዘጋጅቶ በህዝባችን ላይ ጦርነት ከፍቷል።

በህዝቦች እኩልነት እና በብሔረሰቦች መብት ፈፅሞ የማያምነው ህወሐት እኔ የማልገዛት ኢትዮጵያ ተረጋግታ መኖር የለባትም የሚል ያልተገራ ክፉ አመሉን በተደጋጋሚ አሳይቷል። በዚህም እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን እኩልነትን ፈፅሞ እንደማይሻ አረጋግጧል።

ለህዝባችን የሚከተሉትን መልዕክቶች እናስተላልፋለን

1. ምንም እንኳን አሸባሪው እና ተስፋፊው ወያኔ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጠላት ቢሆንም ፣ በተለይ የአማራ ህዝብ የቡድኑ ወረራ ቀጥተኛ ሰለባ እና ገፈት ቀማሽ በመሆኑ ጦርነቱን የመመከት ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በሁሉም አካባቢዎች የሚገኘው ሕዝባችን ካለፈው የጥፋት ግዜ በመማር ከታሪካዊ ጠላቱ የሚሰነዘርበትን ወረራ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት እንዲመክት፣

2. ህዝባችን ከወያኔ ትጥቅ አስፈች ፕሮፖጋንዳ ራሱን እንዲጠብቅ እና ከዚህ ታሪካዊ ጠላት የሚመጣን ማንኛውንም ውዥንብር ጆሮ እንዳይሰጥ፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የወገን ኃይሎች ለወያኔ የሚያሳዩትን የተለሳለሰ የባንዳነት መንገድ ህዝባችን ፈፅሞ እንዳያዳምጥ እና እንዲህ ያሉትን ቡድኖች አጥብቆ እንዲታገል፣

3. የአማራ እና የአፋር ህዝብ የጦርነቱ ዋና ገፈት ቀማሽ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኃይሎች የሚፈልጉትን ሁሉ በማቅረብ ከሐገሩ ጎን እንዲቆም

4. ህዝባችን ይህን ታሪካዊ ጠላት በመቅጣት የተለመደ ጀግንነቱን እንዲወጣ ስንል ጥሪ እያቀረብን፤ በተለይ መንግስት በህዝባችን ላይ ለአራተኛ ጊዜ እየተፈጸመ የሚገኘውን ወረራ በዝምታ የሚመለከት ከሆነ፤ ህዝባችን ስርአትን አምኖ ችግሮች ሁሉ በህግ አግባብ ይፈታሉ የሚል ቀናኢነቱ ማታለያ ሆኖ ከዋለ፤ ይህ በራያ ብቻ የማይቆም ይልቁንም የሁሉ ነገር መፍረሻና ማፍረሻ እንዲሆን መንግስት የፈቀደ መሆኑን ታሪክ የሚመዘግበው ሀቅ ይሆናል።

5. በህወሐት ችግር የአማራና የትግራይ ህዝቦች እንዲሁም መላ ሀገሪቱና ቀጠናው ችግር ውስጥ እየወደቀ በመሆኑ ይህ በአስቸኳይ እንዲቆም እያሳሰብን በተለይ የፌዴራሉ መንግስትና የአማራ ክልል መንግስት በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ የሚገኘውን ወረራ በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ አበክረን እንጠይቃለን!

ሚያዝያ 07/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ

   - ETHIO-MEREJA -
   T.me/ethio_mereja
19.6K viewsedited  01:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 16:32:18
ኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸዉ እንደ አልኮል መጠጦች ፣ ሲጋራና የታሸገ ዉሃ ላይ ላይ ቴምብር እንዲለጠፍ የሚያስገድደዉ መመሪያ ወጣ

የገንዘብ ሚኒስትር የኤክሳይዝ ቴምብር አስተዳዳር ስርዓትን ለመወሰን የሚያስችለውን መመሪያ ከሰሞኑ አዉጥቷል።

በዚህ መመሪያዉ የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸዉ እቃዎች ማለትም የአልኮል መጠጦች፤ አልኮልና እና አልኮል አልባ ቢራ፤ ሲጋራ፤ ሲጋሪልስ፤ ትምባሆ ፣ የታሸገ ውሃና ሌሎች ኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸዉ ዕቃዎች ላይ ተግበራዊ ይደርጋል ።

የኤክሳይዝ ቴምብር በወረቀት፤ በዲጂታል ወይም ሚኒስቴሩ በሚወስነው መልክ የተዘጋጀና የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው
እቃዎች ላይ የሚታተም ወይም የሚለጠፍ ቴምብር ማለት እንደሆነ በዝርዝር ያስቀምጣል።የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣዉ በዚህ መመሪያ የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው እቃዎች አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ተሳታፊ የሆነ ማናቸውም ላኪ በእጁ የሚገኙትን የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው እና የኤክሳይዝ ቴምብር ያልተለጠፈባቸው ወይም ምልክት ያልተደረገባቸዉን ዕቃዎችን ለገበያ ማዋል አይችልም።(ካፒታል)

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja
15.1K viewsedited  13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 15:56:11
የጃፓን መንግስት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን 12 ተሽከርካሪዎችን ድጋፍ አደረገ

በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ የተሽከርካሪ ድጋፉን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ አስረክበዋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፤ ከጃፓን መንግስት በድጋፍ የተገኙ ተሽከርካሪዎች፤ ኮሚሽኑ በተለያዩ ክልሎች የሚያከናውናቸውን የመስክ ስራዎች ለማቀላጠፍ ያግዛሉ ብለዋል።

ኢትዮጵያ መሰረታዊ በሚባሉ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ የዝግጅት ስራዎችን በማካሄድ ላይ መሆኗንሠ ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ በበኩላቸው እንደገለጹት ጃፓን ለኮሚሽኑ ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች።(ኢዜአ)

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja
14.7K views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 12:43:13
Are you interested in becoming an AI engineer?

Join the Kifiya AI Mastery Training Program (Kifiya AIM 1) by Kifiya Financial Technology and 10 Academy. It's a 3-month intensive course beginning on April 29, 2024, focusing on Machine Learning and Data Engineering. Gain fast career advancement in AI and data science through industry-led projects, expert sessions, and explore fintech career opportunities in Addis Ababa, Ethiopia. Special consideration for women and vulnerable groups.

Eligibility criteria:

- Undergraduates (preferred) aged 22-34

- Has legal right to work in Ethiopia.

- Fluent in English (B1 CEFR level), with some background in Python, SQL, and Statistics.

- Ready to commit 30-40 hours weekly, with a strong work ethic and community spirit.

Submit your application by the deadline of April 17, 2024.

Application link: https://apply.10academy.org/login

Learn more about the program: https://10academy.org/kifiya/learn-more

For any question, contact us at kifiya_ai@10academy.org
14.8K views09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 12:06:08
የኢትዮጵያው የኦንላይን ገበያ ፣ የመረጡትን ይዘዙ!
ሊንኩን በመጫን "Join" ያድርጉ

https://t.me/AddisEka1 (join)
https://t.me/HabeshaOnlineStore

0901882392 0931448106
14.3K viewsedited  09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 10:25:17
እስራኤል በኢራን ላይ ልትወስድ ባሰበችው የአጸፋ እርምጃ አሜሪካ እንደማትተባበር ገለጸች

ኢራን ሶሪያ በሚገኘው የቆንስላ ፅህፈት ቤቷ ላይ ለተቃጣባት ጥቃት ቅዳሜ ሌሊት እስራኤል ላይ 300 ሚሳኤሎችና ድሮን ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ እስራኤል ለምትወስደው የአጸፋ እርምጃ አሜሪካ እንደማትተባበር ገልጻለች።

አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን እሁድ ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጠው ማብራሪያ ፕሬዝዳንት ጆው ባይደን እስራኤል ልትወስደው ያሰበችው የአጸፋ እርምጃን በጥንቃቄ እንድታጤነው ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ማሳሰባቸው ነው የተገለጸው።

ፕሬዝዳንት ባይደን እስራኤል ከኢራን የተቃጣባትን ጥቃት በአሸናፊነት መወጣቷን የጠቀሱ ሲሆን በዋናነት በአሜሪካና አጋሮቿ እገዛ 99 በመቶ የሚሆኑት ጥቃቶች በሚሳኤል መከላከያ መክሸፋቸውን በማሳያነት አቅርበዋል።

የአሜሪካ የብሔራዊ ጸጥታ ቃል አቀባዩ ጆን ኪርቢ በበኩላቸው አገራቸው በቀጣናው ግጭቱ እንዳይስፋፋ ለእስራኤል አቋሟን ግልፅ ስለማድረጓን ገልጸዋል።

አሜሪካ ለኢራንም በተዘዋዋሪ የዲፕሎማሲያዊ መረጀ ልውውጥ ተመሳሳይ መልዕክት እንዳስተላለፈች ነው የተነገረው። የእስራኤል የጦር ካቢኔ በኢራን ላይ ሊወሰድ ስለሚገባው የአጸፋ እርምጃ ዙሪያ ተወያይቶ ከስምምነት ላይ ሳይደርስ መበተኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja
15.7K viewsedited  07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 18:27:40
አሜሪካ በሀገሯ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ተጨማሪ የመኖሪያ ጊዜ ፈቀደች፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በነበረበት ወቅት ወደ አሜሪካ በጊዜያዊነት የገቡ ኢትዮጵያዊያን ለ18 ወራት እንዲቆዩ የመኖሪያ ፈቃድ ሰጥታ ነበር፡፡

ለአጭር ጊዜ ቪዛ አግኝተው ለጉብኝት፣ ትምህርት እና ሌሎች ምክንያቶች ወደ አሜሪካ የገቡ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እንደሚቸገሩ በወቅቱ አመልክተው ነበር፡፡አሜሪካም ከኢትዮጵያዊያኑ ሀገራችን ጦርነት እና ሌሎች የፖለቲካ ቀውስ ላይ በመሆኗ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ እንቸገራለን በሚል ለቀረበላት ጥያቄ ለ18 ወራት መኖር እንደሚሉ የመኖሪያ ፈቃድ ሰጥታ ነበር፡፡

ለነዚህ ኢትዮጵያዊያን አመልካቾች የተሰጠው የ18 ወራት ጊዜ የፊታችን ሰኔ ላይ የሚያበቃ የነበረ ሲሆን እነዚህ በጊዜያዊነት ይኖሩ የነበሩ ዜጎች ለተጨማሪ 18 ወራት እንዲኖሩ እንደተፈቀደላቸው ተገልጿል፡፡የሀገሪቱ የሀገር ውስጥ ደህንነት ቢሮ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ አሁንም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመኖራቸው ምክንያት ለአጭር ጊዜ ወደ አሜሪካ የመጡ ኢትዮጵያዊያን ለተጨማሪ 18 ወራት እንዲኖሩ እንደፈቀደ አስታውቋል፡፡

በአሜሪካ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያዊያን ከፈረንጆቹ ሰኔ 2024 እስከ ታህሳስ 2025 ድረስ የሚቆዩበት የመኖሪያ ፈቃድ እንደሚሰጡ ተቋሙ ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡የፌደራል መንግሥት ከአንድ ዓመት በፊት የክልል ልዩ ሀይሎችን "መልሼ አደራጃለሁ" የሚል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ በአማራ ክልል ግጭት ተከስቷል።

ግጭቱ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።(አልአይን)

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja
19.4K viewsedited  15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 12:05:14
ኢራን ሌሊቱን በጀመረችው ቀጥተኛ ጥቃት ወደ እስራኤል በርካታ ቁጥር ያላቸው ድሮኖችን እና ሚሳዔሎችን መተኮሷን አስታውቃለች።

ኢራን በኢምባሲዋ ላይ ለደረሰው ጥቃት እስራኤልን እንደምትበቀል ስትዝት የቆየችው ሲሆን በዛሬው እለት መጠነ ሰፊ የድሮን እና ሚሳዔል ጥቃት ወደ ቴልአቪቭ መክፈቷን አስታውቃለች።እስራኤል እንደስታወቀችው ከ300 በላይ ድሮኖች አና ሚሳዔሎች ከኢራን፣ የመን እና ኢራቅ ውስጥ ወደ እስራኤል ተተኩሰዋል።

የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ አድሚራል ዳንኤል ሀግሪ፤ ወደ እስራኤል ከተተኮሱ ከ300 በላይ ድሮኖና ሚሳኤሎች ውስጥ 99 በመቶውን ማክሸፍ እንደተቻለ ተናግረዋል።በአሜሪካ፣ በብሪታኒያ እና ፈረንሳይ እርዳታ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኢራን ድሮኖችና ሚዔሎች ድንበር ላይ ተመትተው ወድቀዋል።

እስራኤል ተከላከልኩ ትበል እንጂ የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤል አየር መከላከያዎችን ጥሰው በመግባት በርካታ ኢላማዎችን መምታታቸው መረጃዎች እየወጡ ነው።ኢራን ካህይበር የተባለው አደገኛው ሚሳዔል ወሳኝ የሆነ የእስራኤል የአየር ኃይል ጣቢያን መምታቱን የኢራን ዜና አገልግሎት አስታውቋል።

የእስራኤል መከላከያ ኃይል በኤክስ ገጽ (በቀድሞ ትዊተር ገጽ) ባወጣው መረጃ አነስተኛ ቁጥር ላቸው ቦታዎች መመታታቸውን እና በጣም አነስተኛ መጠን ያላቸው ጉዳቶች መድረሳቸውን አረጋግጠቷል።

የእስራኤል ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ ሀገራው ከኢራን የሚሰነዘርባትን ማንኛውም ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅ እንደምትቆም ገልጸው፤ “እኛን የጎዳ ሁሉ ይጎዳል” ሲሉ ዝተዋል።የኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ከህሚኒ በሰጡት አስተያየት “ጺዮናዊው አስተዳደር ይቀጣል” ሲሉ የዛቱ ሲሆን፤ በተመድ የኢራን ተወካይ በበኩላቸው አሜሪካ በዚህ ጉዳይ ጣልቃ እንዳትገባ አስጠንቅቀዋል።

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja
20.3K viewsedited  09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 11:31:11
አቶ አብነት ገብረመስቀል በቦሌ ታወርስ ላይ ያላቸውን ድርሻ ለቀው እንዲወጡ ተፈረደባቸው

አቶ አብነት በነሃሴ 2014 ዓም አቅርበውት በነበረው ክስ የቀድሞ የቅርብ ወዳጃቸው እና አጋራቸው የሆኑት ሼክ መሃመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ በቦሌ ታወር ያላቸውን ድርሻ ለቀው እንዲወጡ ወይም ድርጅቱ እንዲፈርስ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ባሳለፍነው ሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2016 የዋለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ችሎት በሰጠው ውሳኔ ቦሌ ታወርስ የተባለው እና በወሎ ሰፈር አካባቢ የህንጻ ግንባታ ያለው ድርጅት እንዳይፈርስ የወሰነ ሲሆን በተጨማሪም አቶ አብነት የሚገባቸው ድርሻ ተከፍሏቸው ከድርጅቱ ለቀው እንዲወጡ ወስኗል፡፡ቢሊየነሩ ሼክ መሃመድ በቦሌ ታወርስ ላይ የ60 በመቶ ድርሻ ያላቸው ሲሆን ቀሪው በቀድሞ አጋራቸው የተያዘ ነው።(ካፒታል)

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja
18.7K viewsedited  08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 10:38:54
የኢትዮጵያው የኦንላይን ገበያ ፣ የመረጡትን ይዘዙ!
ሊንኩን በመጫን "Join" ያድርጉ

https://t.me/AddisEka1
https://t.me/HabeshaOnlineStore

0901882392 0931448106
18.4K viewsedited  07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ