Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 132.13K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2024-04-26 14:39:33
Adjustable Laptop & Tablet Stand
High Quality(ብረት የሆነ)

የቀሩት ጥቂት ናቸው!

ላፕቶፕ ጭን ላይ አስቀምጠው መጠቀም ለከፋ ጉዳት እንደሚያጋልጥ የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ ፤ ለዚህ ሁሉ መፍትሄ ተጣጣፊ የላፕቶፕ ፣ ታብሌት Holder በተመጣጣኝ ዋጋ ገዝተዉ ጤንነቶን ይጠብቁ።

ዋጋ፦  1200 ብር! Free delivery

ሱቅ ሲመጡ ና ብዛት ለምፈልጉም ቅናሽ አለን።
  0901882392    0931448106
13.4K views11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 14:19:04 በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ቦይንግ በወንጀል እንዲከሰስ ጠየቁ!

በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ከአምስት ዓመት በፊት ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ለአደጋው መንስዔ የሆነው የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሠረት የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤትን ጠየቁ።የመንገደኞቹ ቤተሰቦች በዋሽንግተን ከአሜሪካ የፍትህ ባለሥልጣናት ጋር ሚያዝያ 16/ 2016 ዓ.ም በተነጋገሩበት ወቅት የአሜሪካው ኩባንያ ቦይንግ ለፍርድ እንዲቀርብ ጠይቀዋል።

የተጎጂዎች ቤተሰቦች እና ተወካይ ጠበቆቻቸው ኩባንያው የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከሦስት ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ጥሷል ብለዋል።

የ157 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው ከኢትዮጵያው አደጋ በተጨማሪ ለ189 ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት በሆነው የኢንዶኔዥያ አየር መንገድ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ቦይንግ በወንጀል እንዲጠየቅ ለፍትህ መሥሪያ ቤቱ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው አሰቃቂ በተባለው በቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች የ346 ሰዎች ሕይወት አልፏል።በሁለቱ አውሮፕላን አደጋዎች ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦች በቅርቡ ንብረትነቱ የአሜሪካ አላስካ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በበረራ ላይ ሳለ መስኮቱ መገንጠሉ ጋር ተያይዞ አሁንም የደኅንነት እና የጥራት ችግር እንዳለበት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት በአውሮፕላንን አምራቹ ላይ ካደረገው የረዥም ጊዜ ምርመራ በኋላ ቦይንግ ለ737 ማክስ አውሮፕላኑ ፍቃድ ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ተቆጣጣሪዎችን እንዳሳሰተ ደርሸበታለሁ በሚል “አሜሪካን ለማጭበርበር በማሴር” በሚል ከሦስት ዓመት በፊት ክስ መስርቶበት ነበር።

ቦይንግ ቺካጎ በነበረው የፍርድ ሂደት በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማምቶ በምላሹም የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ለአውሮፕላን አምራቹ ከ737 ማክስ ዲዛይን ጉድለት ጋር በተያያዘ በማጭበርበር ሴራ በወንጀል እንዳይከሰስ ከለላ ሰጥቶት ነበር።የአውሮፕላን አምራቹ በአደጋው ለሞቱት ሰዎች ኃላፊነቱን እንደሚወስድ እና ተጠያቂነቱን ተቀብሎ ለአሜሪካ መንግሥት፣ አደጋ ለደረሰባቸው አየር መንገዶች እና ለተጎጂዎች የሚሆን 2.5 ቢሊዮን ዶላር የቅጣት ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል።

     T.me/ethio_mereja
       @ethio_mereja
13.4K viewsedited  11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 12:42:21
አየር መንገዱ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላትን ወደ ሥራ ሊያስገባ መሆኑን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላትን ወደ ሥራ ሊያስገባ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ገለጹ፡፡

የአፍሪካ አቪዬሽን የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ተቋማት ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ትላንት በአዲስ_አበባ ተከፍቷል፡፡

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላትን አገልግሎት ያስጀምራል፡፡

ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን አካል ክፍሎች ጥገና ኮምፕሌክስና መለዋወጫዎች ማዕከል እየገነባች ነው ያሉት አቶ መስፍን፤ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ወደ አገልግሎት ለማስገባት እየተሠራ ነው ብለዋል።

የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገናው አየር መንገዱን ጨምሮ በአፍሪካ በተለይም በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙ አየር መንገዶች አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ የአየር ፍሬም፣ ሞተርና አካል ጥገናን ጨምሮ የምሕንድስና የቁሳቁስ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ማስረዳታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

     T.me/ethio_mereja
       @ethio_mereja
14.9K viewsedited  09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 18:17:17
አቶ ታዬ ደንደአ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት' ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በጸጥታ ሀይሎች ታህሳስ 2 ቀን በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደኣ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት” ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።

በክሱ ላይ ፤ “ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው  ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ነበር” የሚል ተካቷል፡፡

አቶ ታዬ ደንደኣ በቁጥጥር ስር ሲውሉ በራሳቸው እና በቤተሰባቸው ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ገልጸው አቤቱታ በቃል አቅርበዋል። ምርመራው ታሕሳስ 24 ማለቁንና ዘግይቶ ክስ መቅረቡንም ተቃውመዋል።

ዐቃቤ ሕግ ሌሎች ምርመራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልጾ መልስ ሰጥቷል ሲል ፋና ዘግቧል።ፍርድ ቤቱም በአያያዝ ላይ ያቀረቡትን የመብት ጥያቄ በሚመለከት በጽሑፍ በዝርዝር ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጾ፤ ዋስትናውን በሚመለከት መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
19.1K viewsedited  15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 12:46:55
በኢትዮጵያ በተቋረጡ እና በቆሙ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ የ35 ቢሊዮን ብር ካሳ በተቋራጮች ተጠየቀ

የ #ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር “በፀጥታ ችግር” ምክንያት በተቋረጡ እና በቆሙ የመንገዶች ፕሮጀክቶች ላይ 34.95 ቢሊዮን ብር ካሳ በተቋራጮች መጠየቁን አስታወቀ።

አስተዳደሩ እስከ 2016 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ድረስ “በፀጥታ ችግር” ምክንያት “ሙሉ በሙሉ የኮንትራት ውላቸው የተቋረጠ” 31 የመንገድ ፕሮጀክቶች መኖራቸውንም ይፋ አድርጓል።

ከእነዚህ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል 19ኙ የሚገኙት የፋኖ ታጣቂዎች እና የፌደራል መንግሥቱ ግጭት ውስጥ በገቡበት የአማራ ክልል ነው።

ለሁለት ዓመታት ያህል ጦርነት በተካሄደበት የትግራይ ክልል ደግሞ 11 የመንገድ ፕሮጀክቶች ውላቸው ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በሚንቀሳቀስበት የኦሮሚያ ክልል ደግሞ 19 የመንገድ ፕሮጀክቶች በጊዜያዊነት ቆመዋል ብሏል።

በፀጥታ ችግር በተቋረጡ እና በቆሙ ፕሮጀክቶች ላይ የአገር ውስጥ፣ የውጭ አገር የሥራ ተቋራጮች በድምሩ 34.95 ቢሊዮን ብር ካሳ ጠይቀዋል።ከዚህ ውስጥ 87 በመቶ ወይም 30.5 ቢሊዮን ብር ካሳ የጠየቁት የአገር ውስጥ ሥራ ተቋራጮች ናቸው።
19.9K views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 14:59:53
“ሕጋዊ ያልሆኑ አስተዳደሮችን ለማፍረስ ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር ጭምር እየሠራን ነው” - አቶ ጌታቸው ረዳ

#የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ “ሕጋዊ ያልሆኑ አስተዳደሮችን ለማፍረስ ከፌደራል መንግሥቱ እና ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር ጭምር እየሠራን ነው” ሲሉ ገለጹ

አቶ ጌታቸው ረዳ ትናንት ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከ'ቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ' ጋር በነበራቸው ቆይታ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ በፕሪቶርያ ከስምምነት መደረሱን አስታውሰው “ምዕራብ ትግራይ፣ ሰሜን ምዕራብ ትግራይ እና ደቡብ ትግራይ ያሉ ሕገ-ወጥ አስተዳደሮች ፈርስው” ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የደኅንነት ማረጋገጫ መስጠን ይጨምራል ብለዋል።

ይህን ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ ረዥም ጊዜ ወስዷል የሚሉት አቶ ጌታቸው፤ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ረዥም ጊዜ መውሰድ ባይኖርበትም “ከፌደራል መንግሥቱ ጋር አብረን እየሠራን ነው። ከአማራ ክልል ጋርም ቢሆን በተወሰነ ደረጃ አብረን እየሠራን ነው” ብለዋል።

ባለፉት ሳምንታት በአማራ እና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተው የሰላም መደፍረስ ያጋጠመው በሁለቱ ክልሎች ባሉ “የሚሊሻ አባላት” የነበረ እንጂ መደበኛ ኃይሎች የተሳተፉበት ግጭት አልተካሄደም ብለዋል።

የተከሰተውን ሁኔታ ሲያስረዱም፤ “በአማራ ክልል የነበሩ ሚሊሻዎች የተለያዩ አስጊ እንቅስቃሴያዎችን ሲያደርጉ ነበር። በእኛ በኩል ያሉ የሚሊሻ አባላት ምላሽ ሰጥተዋል” ብለዋል።

ይህን ተከትሎ የአማራ ክልል ያወጣው መግለጫ “መሬት ላይ ያለውን እውነታ ያላገናዘበ” ነው ያሉት አቶ ጌታቸው፤ የፌደራል መንግሥቱ እና ህወሓት የደረሱት የሰላም ስምምነት ተፈጻሚ እንዳይሆን እያደረገ ያለው ሕጋዊ ያልሆነ የአማራ አስተዳደር ነው ብለዋል።

       @ethio_mereja
13.4K viewsedited  11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 09:43:59
በአዲስ_አበባ የመኖሪያ ህንጻ ተደርምሶ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ

በመዲናይቱ አዲስ አበባ፣ አዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12፣ ልዩ ስሙ ጠሮ መስጂድ በተባለው ቦታ የመኖሪያ ህንጻ ተደርምሶ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ።

የመንግስት መገናኛ ብዙሃ የወረዳውን ስራ አስፈፃሚ አይዳ አወልን ጠቅሶ እንደዘገበው አደጋው የተከሰተው የግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደርምሶ በጀርባ በሚገኝ ሌላ መኖሪያ ቤት ላይ በማረፉ ነው፡፡ አደጋው የደረሰው ትናንት ምሽት 5 ሰአት ላይ ነው። ዜናው ስለ ተጎጂዎች፣ ስለ አደጋው መንስኤ እና ሌሎች ጉዳቶች ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

     T.me/ethio_mereja
       @ethio_mereja
15.5K views06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 11:45:51
የካናዳ መንግሥት በኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር አለባቸው ባላቸው የተለያዩ አካባቢዎች ጉዞ እንዳያደርጉ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

በዚህም በትግራይ፣ በአማራ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሲዳማ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች መንቀሳቀስ እንደሌለባቸው አስታውቋል።

ከኤርትራ ድንበር 10 ኪሎ ሜትር፣ ከሶማሊያና ኬኒያ የሚያዋስኑ ድንበሮች 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ዙሪያ ዜጎች እንዳይንቀሳቀሱ ሲል የጉዞ መረጃዎችን በሚሰጥበት ድረገፅ አስፍሯል።

     T.me/ethio_mereja
       @ethio_mereja
19.2K viewsedited  08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 11:29:46
Lark Air Humidifier with LED Light
       High Quality

በኤሌክትሪክ የሚሰራ
ለቤት መልካም መዓዛን የሚሰጥ

Water Tank Capacity: 330ml
Operating power: 2.5W
Spray Volume 30-50ml/H
Purify the air & Beautify the Environment

Three-level ambient light
Silent humidification
Two levels of fog
Adjustable speed

  ዋጋ፦ 1,600 ብር

   0901882392
    0931448106
18.0K views08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 15:07:37
ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲመጡ ጥሪ ቀረበ

ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክሩ መድረኮች እንዲመጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ፡፡

የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ሥላሴ፤ ግጭት ሕይወትና ንብረትን ያጠፋል እንጂ ችግርን አይፈታም ሲሉ ገልጸው፤ “ታሪካዊ አጋጣሚ” በሆነው ሀገራዊ ምክክር በመሳተፍ ሐሳብን በማቅረብ መግባባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ኮሚሽነሯ አሁንም ታጣቂዎቹ ወደ ምክክሩ እንዲመጡ በመጠየቅ ሲመጡም ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አረጋግጠዋል፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን ጨምሮ ሌሎች የሲቪክ ድርጅቶች በሀገራዊ ምክክሩ ከመሳተፍ እራሳቸውን አግልለዋል።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ስራ አስፈጻሚ ኪሚቴ አባል የሆኑት ሱልጣን ቃሲም በቅርቡ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቆይታ ፓርቲያቸው የኮሚሽኑ ምስራታ ሂደት እና እያከናወነው ያለው ስራ ላይ ቅሬታ እንዳላቸው አስረድተዋል።

     T.me/ethio_mereja
       @ethio_mereja
19.8K viewsedited  12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ