Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131.93K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 289

2022-05-13 20:32:04 የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ!!

በነዳጅ ጭማሪ ምክንያት በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ የአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ያደረገው ከሚያዝያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን ተከትሎ ነው፡፡

በዚህም መሠረት ነባር ታሪፍ በደረጃ አንድ ተሽርካሪ በአስፋልት መንገድ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 493 የነበረው በአዲሱ ታሪፍ በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 039 ጭማሪ በማድረግ በሰው በኪሎ ሜትር ብር 0 ነጥብ 532 ሆኗል ተብሏል፡፡

ደረጃ አንድ በጠጠር መንገድ በሰው በኪሎ ሜትር ታሪፍ 0 ነጥብ 548 የነበረው ወደ 0 ነጥብ 596 ከፍ ብሏል፡፡ በዚህም በኪሎ ሜትር የ 0 ነጥብ 049 ጭማሪ አድርጓል፡፡

በሌላ በኩል በደረጃ ሁለት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 457 የነበረው በአዲሱ ታሪፍ በኪሎ ሜትር የ0 ነጥብ 039 ጭማሪ በማድረግ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 496 ሆኗል፡፡

በደረጃ ሁለት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0 ነጥብ 505 የነበረው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 039 ጭማሪ በማድረግ በአዲሱ በኪሎ ሜትር 0. ነጥብ 554 ተደርጓል፡፡

ደረጃ ሦስት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 416 ይከፈልበት የነበረው 0 ነጥብ 039 በኪሎሜትር ጭማሪ በማድረግ 0 ነጥብ 455 በኪሎሜትር እንዲሆን ተወስኗል፡፡

ደረጃ ሦስት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 471 የበነረው በኪሎ ሜትር የ0 ነጥብ 049 ጭማሪ በማድረግ በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 520 ሆኗል፡፡

የተደረገው የታሪፍ ማስተካከያ በ100 ኪሎ ሜትር ሲታይ በደረጃ አንድ ተሽርካሪ ለአንድ ሰው በነባር ታሪፉ በአስፋልት መንገድ ብር 49 ነጥብ 29 ይከፈል የነበረው በአዲሱ ብር 53 ነጥብ 16 ሆኗል፡፡ ይህም በ100 ኪሎ ሜትር ጭማሪ ያደረገው የብር 3 ነጥብ 87 ነው፡፡

በደረጃ ሁለት ተሽከርካሪዎች ለአንድ ሰው በነባር ታሪፍ በ100 ኪሎ ሜትር 45 ነጥብ 70 ያስከፍል የነበረው በ100 በኪሎ ሜትር ብር 3 ነጥብ 87 በመጨመር 49 ነጥብ 58 በ100 ኪሎ ሜትር ሆኗል፡፡

በተመሳሳይ በደረጃ ሦስት ተሸርካሪ በ100 ኪሎ ሜትር ለአንድ ሰው ብር 41 ነጥብ 61 ያስከፍል የነበረው በ100 ኪሎ ሜትር የ3 ነጥብ 88 ጭማሪ በማድረግ በ100 ኪሎ ሜትር ብር 45 ነጥብ 49 ሆኗል መባሉን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
10.1K viewsedited  17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 20:14:08
Double A፣ ከአጓጊ ሽልማቶች ጋር ተመልሷል

የ“Double A QR Ethiopia” የሞባይል መተግበርያን በስልክዎ  በመጫን በትክክለኛው የ Double A  ወረቀት ካርቶን ላይ የሚገኘውን የ  QR ኮድ የሞባይል መተግበሪያውን ተጠቅመው ስካን በማድረግ ፡-
 የተለያዩ ስጦታዎችን ለምሳሌ፦ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣የውሃ ማጣሪያ፣ ማይክሮዌቭ/የምግብ ማሞቂያ ማሽን፣ የጁስ መፍጫ እና የመሳሰሉትን ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ይሸለሙ::

የ QR ነጥብ መሰብሰቢያ ፕሮግራማችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ! ደጋግመው QR ስካን ሲያርጉ ፤ ተጨማሪ ሽልማቶችን ያገኛሉ፡፡

መተግበርያውን ለማውረድ እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።

Link: https://bit.ly/3KGYCxC  Or

https://da-cloud.advanceagro.net/index.php/s/WYovIsmE4u2Kz6y

ለተጨማሪ መረጃ: https://DoubleArewards.com/Ethiopia
1.4K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 19:46:53
በርካታ የመኪና ግብይት አማራጭ ያሉትን ይህን ቻናል ይቀላቀሉ፣ ይጎብኙ፣ ይገበያዩ!

http://T.me/EthioCarMarket
3.3K views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 16:00:38
#ታሪፍ
አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ እስኪደረግ ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አካላት በነባሩ ክፍያ ታሪፍ በሙሉ አቅም እንዲሰሩ ማሳሰቢያ ተሰጠ!!

በመዲናዋ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሁሉም ተቋማት፣ የታክሲና ሀይገር ባለንብረቶች ማህበራትና ግለሰቦች አዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ይፋ እስኪደረግ ድረስ በነባሩ የክፍያ ታሪፍ መሰረት አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል፡፡

በቢሮው የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ይርጋዓለም ብርሃኔ እንደተናገሩት በመዲናዋ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሁሉም ተቋማት፣ የታክሲና ሀይገር ባለንብረቶች ማህበራትና ግለሰቦች አዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ይፋ እስኪደረግ ድረስ በነባሩ የክፍያ ታሪፍ መሰረት ልክ እንደከዚህ ቀደሙ በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ገብተው አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

ከነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ጋር ተያይዞ አገልግሎቱን በተገቢው መንገድ የማይሰጡና ህብረተሰቡን ለተለያዩ እንግልቶችና አላስፈላጊ ወጪዎች የሚዳርጉ ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት ሰጪ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ወደ ስራ እንዲገቡ፤ በማይገቡትም ላይ ቢሮው አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታና በህጋዊ መንገድ ለተቋሙ ሳያሳውቁ ከስራ ገበታቸው የወጡት የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶቡስ አገልግሎት ሰጪ ማህበራትም በገቡት ውል መሰረት መብታቸውን እየጠየቁ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ምክትል ቢሮ ኃላፊው አስጠንቅቀዋል፡፡

(አ/አ ትራንስፖርት ቢሮ)
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
3.0K viewsedited  13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 15:52:35
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለፁ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ለተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች አልጋ ወራሽ ሼክ ሞሃመድ ቢንዛይድ አል-ናህያን እንዲሁም ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ህዝብ የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን እገልጻለሁ ብለዋል።

የ73 ዓመቱ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል-ናህያን ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የፕሬዝዳንቱን ህልፈት ተከትሎ የ40 ቀን ሃዘን እንደሚታወጅ የአገሪቱ የፕሬዝዳንታዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን አባታቸውን ሼክ ዛይድ አል ናህያንን ተክተው በፈረንጆቹ 2004 ወደ ስልጣን መምጣታቸው ይታወሳል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
3.4K viewsedited  12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 13:17:42
የቶም ጋርድነር የስራ ፈቃድ ተሰረዘ!!


የዘ ኢኮኖሚስ መጽሔት ዘጋቢው ቶም ጋርድነር በኢትዮጵያ የነበረው የሥራ ፈቃድ መሰረዙን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ ለጋዜጠኛው በጻፈው ደብዳቤ ላይ እነዳስታወቀው፤ ጋዜጠኛው ከሙያ ስነ መግባር ውጭ በተደጋጋሚ ሲሰራ በመገኘቱ ተደጋጋሚ የቃል እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል።

በተጨማሪም ከጋዜጠኛው ጋር ውይይት በማድረግ ከስህተቱ እንዲታቀብ ለማድረግ ጥረት መደረጉን ባላስልጣኑ ገልጿል።

ይሁን እንጂ ቶም ጋርድነር የሙያውን ስነ ምግባር በማክበር ለመስራት ባለመቻሉ ከዛሬ ግንቦት 5 ቀን 2014ዓ ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ የነበረው የጋዜጠኝነት የስራ ፈቃድ መሰረዙንና ከዚህ በኋላ በጋዜጠኝነት ስራ በኢትዮጵያ ውስጥ መስራት እንደማይችል ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ዘ ኪኮኖሚስት በዚህ ጋዜጠኛ ምትክ ሌላ የሙያውን ሥነ ምግባር አክብሮና ገለልተኛ ሆኖ መስራት የሚችል ሰው መድቦ ማሰራት እንደሚችልም ባለስልጣኑ በዚሁ ደብዳቤ ላይ ገልጿል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
8.1K viewsedited  10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 11:41:18
በ60 ሚሊዮን ዩሮ የተገነባው ብቅል አምራች ፋብሪካ ተመረቀ!

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተገነባው ሱፍሌት ማልት ብቅል አምራች ፋብሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በዛሬው እለት ተመርቋል።

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በ60 ሚሊየን ዩሮ ወጪ የተገነባው ሱፍሌት ማልት ኢትዮጵያ የተሰኘው የብቅል ማምረቻ ፋብሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢብ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የምረቃ መርሐግብር እየተካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን አስታውቋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
4.1K viewsedited  08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 10:14:17
165 ተሽከርካሪዎች በትግራይ ክልል 3 ሺሕ ቶን ምግብ አከፋፈሉ!!

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት የእርዳታ አቅርቦት የጫኑ 165 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል ደርሰው 3 ሺሕ ቶን ምግብ ማከፋፈሉን አስታወቀ፡፡

የምግብ አቅርቦቱ 120 ሺሕ ዜጎችን ተደራሽ ማድረጉ ተጠቁሟል፡፡ 3 ሺሕ 4 መቶ ቶን የምግብ እርዳታ ደግሞ ወደ ማከፋፈያ ጣቢያዎች መላካቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም አሁን ላይ እርዳታ የጫኑ 94 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እያቀኑ ነው ተብሏል፡፡ የምግብ እርዳታ ስርጭቱ በአፋር እና በአማራ ክልልም በሂደት ላይ መሆኑን የዓለም የምግብ ፕሮግራም በማኅበራዊ የትስስር ገፁ ገልጿል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
6.9K viewsedited  07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 10:05:45
Double A፣ ከአጓጊ ሽልማቶች ጋር ተመልሷል

የ“Double A QR Ethiopia” የሞባይል መተግበርያን በስልክዎ  በመጫን በትክክለኛው የ Double A  ወረቀት ካርቶን ላይ የሚገኘውን የ  QR ኮድ የሞባይል መተግበሪያውን ተጠቅመው ስካን በማድረግ ፡-
 የተለያዩ ስጦታዎችን ለምሳሌ፦ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣የውሃ ማጣሪያ፣ ማይክሮዌቭ/የምግብ ማሞቂያ ማሽን፣ የጁስ መፍጫ እና የመሳሰሉትን ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ይሸለሙ::

የ QR ነጥብ መሰብሰቢያ ፕሮግራማችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ! ደጋግመው QR ስካን ሲያርጉ ፤ ተጨማሪ ሽልማቶችን ያገኛሉ፡፡

መተግበርያውን ለማውረድ እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።

Link: https://bit.ly/3KGYCxC  Or

https://da-cloud.advanceagro.net/index.php/s/WYovIsmE4u2Kz6y

ለተጨማሪ መረጃ: https://DoubleArewards.com/Ethiopia
6.2K views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 09:45:04
የባንክ ባለቤት በመሆን 30%-45% ማትረፍ ይፈልጋሉ?
መሉ መረጃውን ከላይ በፎቶ ተያይዞዋል ፈጥነው አክሲዮን በመግዛት አትራፊ ይሁኑ ለበለጠ መረጃ ከታች ባለው ስልክ መደወል ይችላሉ።
0913013439
0913013439

ለበለጠ መረጃ በTelegram ይቀላቀሉን:
t.me/stockBKGH or
t.me/stockEthio
6.6K views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ