Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131.93K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 286

2022-05-16 14:48:44
ለሰርግ ወደ አዲስ አበባ የመጣችው ሀናን


ሃናን ትባላለች የ25 አመት ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነች፣ ከእጮኛዋ ጋር ኒካ ለማሰር ስላሰቡ አዲስ አበባ በመምጣት ለሰርጋቸው የሚያስፈልጋቸው እቃዎች ለመግዛት በአንድ ሆቴል 8ኛ ፎቅ ማረፊያቸውን አደረጉ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ከታዲያስ አዲስ ጋር በነበረው ቆይታ ገልጿል።

በሆቴሉ እንዳሉ በመካከላቸው አለመግባባት ተፈጥሮ ይጨቃጨቃሉ እሱ ክፍሉን ጥሎ ወጣ ከቆይታ በኋላ የሆቴሉን ባልደረባ "እስቲ ሂድና ቼክ አድርጋት ቅድም ተበሳጭታ ነበር" ብሎ ይልከዋል፣ እሱም ሄዶ ሲመለከት ከ8ኛ ፎቅ ራሷን ወደ 3ኛ ፎቅ ወርውራ ህይወቷ እንዳለፈ ታውቋል ሲል ፖሊስ ተናግሯል።

ፖሊስም ምርመራውን መቀጠሉን ገልፇል::
#ነብስ_ይማር

T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
14.9K viewsedited  11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 14:24:29
ከ3 ሺሕ በላይ ጥይት ከነተጠርጣሪዎቹ በቀጥጥር ስር ዋለ!!

የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሔራዊ መረጃ ደኅንነት ባደረጉት ክትትል በአንድ የእንጨት ሥራ ድርጅት ውስጥ ተደብቆ የተቀመጠ ከ3 ሺሕ በላይ ጥይት ከእነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ሁለቱ ተቋማት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አዲሱ ገበያ ቀለበት መንገድ አካባቢ በሚገኝ አንድ የእንጨት ስራ ድርጅት ውስጥ ተደብቆ የተቀመጠ ጥይት ስለመኖሩ ከሕዝብ የደረሳቸውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ሲከታተሉ ቆይተው ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም በህግ አግባብ በድርጅቱ ውስጥ ባደረጉት ብርበራ በ4 ማዳበሪያ ተጠቅልሎ በድብቅ የተቀመጠ 1 ሺሕ 98 የብሬን እና 2 ሺሕ 162 የክላሽ ጥይት ተይዟል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 2 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ኅብረተሰቡ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ሊያስከትል የሚችለውን ሀገራዊ ጉዳት ተገንዝቦ የዚህ ህገ ወጥ ተግባር ተሳታፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ እየሰጠ ያለውን ጥቆማ እና መረጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
14.1K viewsedited  11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 14:05:10 "ከጦር መሳሪያ ምዝገባው በኋላ የተደራጀ ስልጠና ይሰጣል" - የአማራ ክልል

አማራን ሕዝብ ደህንነት ለማስጠበቅ ያለመ የተደራጀ ሥልጠና ሊሰጥ መሆኑ ተገልጿል!!

የጥፋት ሀይሉን ዓላማ ለማክሸፍ ከመንግሥት የጸጥታ ኀይል በተጨማሪ ማንኛውም የጦር መሳሪያ ያለው ምዝገባ ካካሔደ በኋላ የተደራጀ ሥልጠና እንዲወስድም ይደረጋል ብለዋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
13.1K viewsedited  11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 13:58:18
የአማራ ክልል ዜጎች የጦር መሳሪያ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቀረበ!!

ከግንቦት 9/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት የጦር መሳሪያ ምዝገባ እንደሚካሄድ የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል።

ከዚህ በፊት ያልተመዘገበ ማንኛውም የጦር መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በአካባቢው በሚገኙ የምዝገባ ማዕከላት በመገኘት እንዲያስመዘግብ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አሳስቧል።

የቢሮው ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው፤ የጦር መሳሪያ ምዝገባው የአማራን ሕዝብ ደኅንነት ለማስጠበቅ አጋዥ ኃይል ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል፡፡

አሸባሪው ትሕነግ የጥፋት መንገድ ተጋሪዎች የአማራን ሕዝብ አንድነት ለመሸርሸር በብሔርና በሃይማኖት ሽፋን የተለያዩ አጀንዳዎችን እየዘረጉ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው የሽብር ቡድኑ አሁንም ወደ ዳግም ጦርነት ለመግባት ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ በተጨባጭ እያሳየ ነው ብለዋል። የጥፋት ኃይሉን ዓላማ ለማክሸፍ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይል በተጨማሪ ማንኛውም የጦር መሳሪያ ያለው ምዝገባ ካካሔደ በኋላ የተደራጀ ሥልጠና እንዲወስድም ይደረጋል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
13.8K viewsedited  10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 11:21:47
የሰብአዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 85 ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸው ተገለጸ!!

የዓለም ምግብ ፕሮግራም 85 የሰብአዊ አርዳታ የጫኑ ተስከርካሪዎች ትላንት መቀሌ መድረሳቸውንና ተጨማሪ 130 የሰብአዊ እርዳታ የጫኑ ተስከርካሪዎች ወደ ትግራይ እየተጓዙ መሆናቸውን አስታወቀ፡፡

ወደ ትግራይ ክልል የሚላከው የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጸው የዓለም ምግብ ፕሮግራም የሰብአዊ እርዳታ የጫኑ ከባባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይና አፋር ክልል እየገቡ መሆናቸውንና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አካላት የማዳረስ ሥራ እየተሰራ መሆኑን አመልክቷል፡፡

ወደ አፋር እየተጓጓዘ የሚገኘው እርዳታ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናትም እስከ 36 ሺሕ ለሚደርሱ ሰዎች ድጋፉን ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል፡፡
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
15.1K viewsedited  08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 22:32:42
በሱማሊያ ማምሻውን በተካሄደው ሁለተኛ ዙር ፕሬዝዳንታዊ የምርጫ ፉክክር የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ 110 ድምጽ እና የወቅቱ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ፎርማጆ 83 ድምጽ በማግኘት በማግኘት አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው ለሦስተኛው ዙር ምርጫ አልፈዋል።

በመጀመሪያው ዙር በ65 ድምጽ በአንደኛ ደረጃ ሲመሩ የነበሩት የፑንትላንዱ ፕሬዝዳንት አብዱላሂ ደኒ እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ሐሰን ካይሬ ሦስተኛ እና አራተኛ ደረጃ በማግኘት ከፉክክሩ ውጭ ሆነዋል። ሁለተኛውን ዙር ፉክክር በቀዳሚነት ያሸነፉት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ከአሁኑ ፕሬዝዳንት ፎርማጆ በፊት አገሪቱን የመሩ ናቸው።[ዋዜማ ራዲዮ]
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
5.7K viewsedited  19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 20:58:38
"መንግሥት ከሕወሓት የሚቃጣ የትኛውንም ዓይነት ጥቃት ለመመከት በየትኛውም ጊዜ ሙሉ ዝግጁነት፣ ዐቅም እና ብቃት አለው":-የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ለገሰ ቱሉ መንግሥታቸው ከውስጥም ከውጪም የሚቃጣ የትኛውንም ዓይነት ጥቃት ለመመከት ዝግጁ ነው ብለዋል። ፖለቲካዊ ይዘት ባላቸው መገፋፋቶች ምክንያት እየጠፋ ያለን የሰው ሕይወትና የንብረት ውድመትን ለመግታት ብሎም አገራዊ አንድነትን ለማስከበር በሁሉም ክልሎች የተቀናጀ ያሉት እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ሕወሓት አሁንም የአፋር እና የአማራ ክልል ወረዳዎችን በኃይል እንደያዘ መሆኑን የገለፁት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ መንግሥት ወደ ትግራይ የሚልከውን የሰብዓዊ እርዳታ እንደማያቋርጥ አስታውቀዋል። ይሁንና በመጪው ክረምት የትግራ ሕዝብ የመኸር አዝመራ ግብዐት ካላገኘ ይበልጥ ለረሃብ ሊጋለጥ ይችላል የሚል ሥጋት በመንግሥት በኩል እንዳለ ጠቅሰው ሕወሓት ጦርነትን ከመጎሰም እንዲቆጠብ አሳስበዋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
10.4K viewsedited  17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 20:56:57
በርካታ የመኪና ግብይት አማራጭ ያሉትን ይህን ቻናል ይቀላቀሉ፣ ይጎብኙ፣ ይገበያዩ!

http://T.me/EthioCarMarket
9.5K views17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 20:44:22
Double A፣ ከአጓጊ ሽልማቶች ጋር ተመልሷል

የ“Double A QR Ethiopia” የሞባይል መተግበርያን በስልክዎ  በመጫን በትክክለኛው የ Double A  ወረቀት ካርቶን ላይ የሚገኘውን የ  QR ኮድ የሞባይል መተግበሪያውን ተጠቅመው ስካን በማድረግ ፡-
 የተለያዩ ስጦታዎችን ለምሳሌ፦ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣የውሃ ማጣሪያ፣ ማይክሮዌቭ/የምግብ ማሞቂያ ማሽን፣ የጁስ መፍጫ እና የመሳሰሉትን ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ይሸለሙ::

የ QR ነጥብ መሰብሰቢያ ፕሮግራማችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ! ደጋግመው QR ስካን ሲያርጉ ፤ ተጨማሪ ሽልማቶችን ያገኛሉ፡፡

መተግበርያውን ለማውረድ እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።

Link: https://bit.ly/3KGYCxC  Or

https://da-cloud.advanceagro.net/index.php/s/WYovIsmE4u2Kz6y

ለተጨማሪ መረጃ: https://DoubleArewards.com/Ethiopia
9.8K views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 19:08:27
ወልድያ ከተማ የ"መቀመጭት" ተራራን በአቡነ ኤርምያስ ስም መሰየሙን አስታወቀ!!

ወልድያ ከተማ አስተዳደር የ"መቀመጭት ተራራን" "አቡነ ኤርምያስ ተራራ" ብሎ መሰየሙን አስታውቋል። የተራራውን ስያሜ የሰጠው ከተማ አስተዳደሩ አቡነ ኤርምያስ ያደረጉትን ውለታ በማሰብ እና ለአቡኑ ተያያዥ የልማት የቤት ሥራዎች ለመስጠት መሆኑን ገልጿል።

የዕፅዋት ሳይንስ መድኃኒት ቅመማ ጋር ተያይዞ ለምርምር የሚሆኑ ሀገር በቀል ዕፅዋቶች በስፋት የሚገኙበት ተራራ በመሆኑ የጥንት መጻሕፍትን በመተርጎም የሚመራመሩ ሊቃውንትን በተራራው በማሰማራት የምርምር ማዕከል እንደሚያደርጉት ታላቅ ተስፋ ስለተጣለባቸው ስያሜው የተሰጠበት አንደኛው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
12.4K viewsedited  16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ