Get Mystery Box with random crypto!

'መንግሥት ከሕወሓት የሚቃጣ የትኛውንም ዓይነት ጥቃት ለመመከት በየትኛውም ጊዜ ሙሉ ዝግጁነት፣ ዐቅ | ETHIO-MEREJA®

"መንግሥት ከሕወሓት የሚቃጣ የትኛውንም ዓይነት ጥቃት ለመመከት በየትኛውም ጊዜ ሙሉ ዝግጁነት፣ ዐቅም እና ብቃት አለው":-የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ለገሰ ቱሉ መንግሥታቸው ከውስጥም ከውጪም የሚቃጣ የትኛውንም ዓይነት ጥቃት ለመመከት ዝግጁ ነው ብለዋል። ፖለቲካዊ ይዘት ባላቸው መገፋፋቶች ምክንያት እየጠፋ ያለን የሰው ሕይወትና የንብረት ውድመትን ለመግታት ብሎም አገራዊ አንድነትን ለማስከበር በሁሉም ክልሎች የተቀናጀ ያሉት እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ሕወሓት አሁንም የአፋር እና የአማራ ክልል ወረዳዎችን በኃይል እንደያዘ መሆኑን የገለፁት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ መንግሥት ወደ ትግራይ የሚልከውን የሰብዓዊ እርዳታ እንደማያቋርጥ አስታውቀዋል። ይሁንና በመጪው ክረምት የትግራ ሕዝብ የመኸር አዝመራ ግብዐት ካላገኘ ይበልጥ ለረሃብ ሊጋለጥ ይችላል የሚል ሥጋት በመንግሥት በኩል እንዳለ ጠቅሰው ሕወሓት ጦርነትን ከመጎሰም እንዲቆጠብ አሳስበዋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ