Get Mystery Box with random crypto!

በሱማሊያ ማምሻውን በተካሄደው ሁለተኛ ዙር ፕሬዝዳንታዊ የምርጫ ፉክክር የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሐሰን | ETHIO-MEREJA®

በሱማሊያ ማምሻውን በተካሄደው ሁለተኛ ዙር ፕሬዝዳንታዊ የምርጫ ፉክክር የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ 110 ድምጽ እና የወቅቱ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ፎርማጆ 83 ድምጽ በማግኘት በማግኘት አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው ለሦስተኛው ዙር ምርጫ አልፈዋል።

በመጀመሪያው ዙር በ65 ድምጽ በአንደኛ ደረጃ ሲመሩ የነበሩት የፑንትላንዱ ፕሬዝዳንት አብዱላሂ ደኒ እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ሐሰን ካይሬ ሦስተኛ እና አራተኛ ደረጃ በማግኘት ከፉክክሩ ውጭ ሆነዋል። ሁለተኛውን ዙር ፉክክር በቀዳሚነት ያሸነፉት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ከአሁኑ ፕሬዝዳንት ፎርማጆ በፊት አገሪቱን የመሩ ናቸው።[ዋዜማ ራዲዮ]
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ