Get Mystery Box with random crypto!

ወልድያ ከተማ የ'መቀመጭት' ተራራን በአቡነ ኤርምያስ ስም መሰየሙን አስታወቀ!! ወልድያ ከተማ አ | ETHIO-MEREJA®

ወልድያ ከተማ የ"መቀመጭት" ተራራን በአቡነ ኤርምያስ ስም መሰየሙን አስታወቀ!!

ወልድያ ከተማ አስተዳደር የ"መቀመጭት ተራራን" "አቡነ ኤርምያስ ተራራ" ብሎ መሰየሙን አስታውቋል። የተራራውን ስያሜ የሰጠው ከተማ አስተዳደሩ አቡነ ኤርምያስ ያደረጉትን ውለታ በማሰብ እና ለአቡኑ ተያያዥ የልማት የቤት ሥራዎች ለመስጠት መሆኑን ገልጿል።

የዕፅዋት ሳይንስ መድኃኒት ቅመማ ጋር ተያይዞ ለምርምር የሚሆኑ ሀገር በቀል ዕፅዋቶች በስፋት የሚገኙበት ተራራ በመሆኑ የጥንት መጻሕፍትን በመተርጎም የሚመራመሩ ሊቃውንትን በተራራው በማሰማራት የምርምር ማዕከል እንደሚያደርጉት ታላቅ ተስፋ ስለተጣለባቸው ስያሜው የተሰጠበት አንደኛው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ